ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የደህንነት እና ህግ ማስከበር ዋና ኃላፊ መሾም።

ጁን 25, 2024

ውድ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ቤተሰቦች

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ማርከስ ጂ ጆንስ (Marcus G. Jones) ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የደህንነት እና ህግ የማስከበር ሥራ ሀላፊ ሆነው መሾማቸውን በአንድ ድምፅ አጽድቋል።

ጆንስ በአሁኑ ጊዜ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ አዛዥ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በፖሊስ መኮንንነት ወደ MCPD ከተቀላቀሉ በኋላ ባለፉት 38 ዓመታት ህግ በማስከበር ሥራ ቁልፍ የአመራር ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ጃኑዋሪ ላይ ከ MCPD በጡረታ የመልቀቅ ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀዋል።

"ቺፍ ጆንስ ለ MCPS ደህንነት እና ህግ የማስከበር ሀላፊነት በተግባር የተፈተነ የአመራር ብቃት እና ለህዝብ ደህንነት ያላቸውን ሰፊ ልምድ እና ቁርጠኝነት ይዘው ይመጣሉ።" የሰራተኞች ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሄንሪ ጆንሰን (Dr. Henry Johnson) እንዳሉት “ቺፍ ጆንስ በኃላፊነት መመደባቸውን የትምህርት ዲስትሪክታችንን ደህንነት ለማሻሻል ጠቃሚ እርምጃ ነው" በማለት ገልፀዋል።

ቺፍ ጆንስ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተመደቡትን አዲሱን ኃላፊነታቸውን በጁላይ ወር ይጀምራሉ። 


M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org