መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኦገስት 31 2023

1. MCPS ለአፍታ፡ 2023–2024 የትምህርት መጀመሪያ ሳምንት

MCPS ሰኞ፣ ኦገስት 28 ቀን ከ 162,000 በላይ ተማሪዎችን ለ 2023–2024 የትምህርት አመት በመቀበል የመግቢያ በሩን ከፍቷል። MCPS ውስጥ 211ኛው ትምህርት ቤት የሆነውን የካቢን ብራንች አንደኛ ደረጃ ትምህርትን (Cabin Branch Elementary School) በማስተዋወቅ እና በካውንቲው ውስጥ እድሳት የተደረገባቸው አራት አዳዲስ የትምህርት ቤት ሕንፃዎችን ስናስተዋውቅ በጣም ደስታ ይሰማናል።

ከመጀመሪያው ቀን የማጠቃለያ እና ፎተግራፍ ማህደር ምስሎችን ይመልከቱ።


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች "Implement Remind" የተሰኘ አዲስ የግንኙነት መተግበሪያ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች "Implement Remind" የተሠኘ አዲስ የግንኙነት መሳሪያ

2. "Remind App" መተግበሪያ ምንድን ነው?
"Remind" በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች፣በመምህራን፣በተማሪዎች እና በወላጆች መካከል ለኝኙነት የሚያገለግል የመልእክት ማስተላለፊያ ነው። የት/ቤት ሰራተኞች፣ የማእከላዊ ቢሮ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና ወላጆች የጽሁፍ መልእክት፣ ኢሜል ወይም የስልክ ጥሪ እና በመረጡት ቋንቋ ተመራጭ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም መልዕክቶችን እንዲልኩ እና/ወይም እንዲቀበሉ ለማስቻል ሁሉም "Remind" አካውንት ይኖራቸዋል።

የእኔ ትምህርት ቤት የሚጠቀምበት መቼ እና እንዴት ነው?
በዊንተር ዕረፍት፥ ትምህርት ቤቶች "Remind app" መተግበሪያን በመደበኛነት ወደመጠቀም ይሸጋገራሉ። ትምህርት ቤትዎ ይህንን መተግበሪያ ለመጠቀም ሽግግር ሲያደርግ፣ ወላጆች እና ትልልቅ ተማሪዎች ከመምህር(ራን) የጽሁፍ መልእክት ወይም የኢሜይል ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

ለወላጆች
ወላጆች በኢንተርኔት ወይም "Remind app" መተግበሪያ በመጠቀም "Remind" አካውንታቸውን መክፈት/መግባት ይችላሉ።

ለተማሪዎች
ዕድሜያቸው 13 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከአስተማሪዎች ለሚደርሳቸው መልእክት ምላሽ መስጠት ይችላሉ። ሁሉም ተማሪዎች "Log in to Google option, which uses their MCPS Google apps credentials" የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጉግል አፕሊኬሽኖቻቸውን በመጠቀም "Remind" አካውንታቸውን/መለያቸውን መክፈት/መግባት ይችላሉ። ዕድሜያቸው 13 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሞባይል ያላቸው ተማሪዎች "Remind app" መተግበሪያ አውርደው “Log in to Google” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም መግባት/መክፈት ይችላሉ።


የስቴት ምዘና/ፈተና በተመለከተ ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ጠቃሚ መልክት

3. ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የስቴት ምዘና/ፈተና በተመለከተ ጠቃሚ መልክት

ከዚህ የትምህርት አመት ጀምሮ ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች (2027 ክፍል)፣ ለባዮሎጂ እና ስነመንግስት ኮርስ የሜሪላንድ አጠቃላይ ምዘና/ፈተና በእያንዳንዱ ኮርስ ከተማሪው የመጨረሻ ክፍል 20 በመቶ ተሰልቶ ይመዘገብላቸዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጋራት ቨርቹዋል የወላጆች ምሽት በዚህ ፎል ይዘጋጃል።


4. ከፎል የስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት መክፈቻ ምሽት በፊት ስለደህንነት የሚተገበሩ የማሻሻያ እርምጃዎች

MCPS ተማሪ-አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ ተመልካቾች እና ማህበረሰባችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ አካባቢን ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው። MCPS የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ ለሁሉም ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የሆነ አካባቢን ለመጠበቅ የአትሌቲክስ ዝግጅት ስራዎችን እና ሂደቶችን ማንቀሳቀስ ይቀጥላል። ይበልጥ ያንብቡ.


ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ዝግጅቶችን የሚያስተናግዱ ትምህርት ቤቶች

ወደ ትምህርት ቤት የተመመለስ ዝግጅቶችን የሚያስተናግዱ ትምህርት ቤቶች

የዋትኪንስ ሚልስ ክላስተር ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 14 ቀን 6–8 p.m. ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት የመጀመሪያ ዝግጅቱን በማከናወን “Back to School Block Party” ይቀላቀላል። ይህ ከአሁን ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር ወር ከሚከናወኑት ለተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅቶች አንዱ ብቻ ነው። ዝግጅቱ የሚካሄደው ሞንትጎመሪ ቪሌጅ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣Montgomery Village Middle School, 19300 Watkins Mill Road in Montgomery Village ነው

ስለ ትምህርት ቤትዎ የዚህ አመት ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ምሽት ቀን እና ሰዓት ከተማሪዎ ትምህርት ቤት ጋር መነጋገርዎን ያረጋግጡ።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች አመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ላይ ተገኝተዋል

በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ላይ ተገኝተዋል

በሺዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት 2023-2024 የትምህርት አመትን "Back-to-School Fair"/ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ ለመጀመር ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 የትምህርት ቤት ሰራተኞችን እና የማህበረሰብ አጋሮችን ተቀላቅለዋል። የአውደ ርዕይ ፎቶዎችን ይመልከቱ


ስለ MCPS የተላለፉ ዘገባዎች



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)