መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኦክቶበር, 05 2023

ከኦክቶበር 9 ጀምሮ ለሁሉም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጪ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ

1. ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ማመልከቻ ለማቅረብ በቅርቡ ይከፈታል

ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 10 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ParentVUE ማመልከቻ በመጠቀም ለሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች የማመልከት እድል ይኖራቸዋል። በተጨማሪም፣ 9-11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ መለዋወጥ ክፍለ ጊዜዎች የሚኖሩ ስለሆነ ሁሉንም ቀናት ልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ያገኛሉ።

ማመልከቻዎች እስከ አርብ፣ ኖቬምበር 3 ድረስ ተጠናቀው መቅረብ አለባቸው። ፕሮግራሞቹ-በጨረፍታ፣ ብቁነት፣ ዘወትር የሚቀርቡ ጥያቄዎች እና ኦክቶበር open house dates በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።


የአእምሮ ጤንነት ግንዛቤ ሳምንት ከኦክቶበር 30 እስከ ኖቬምበር 4

2. የአእምሮ ጤንነት ግንዛቤ ሳምንት ከኦክቶበር 30 እስከ ኖቬምበር 4

ኦክቶበር 30 እስከ ኖቬምበር ባሉት ሳምንታት ውስጥ MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር (MCSPA) በነፃ ዝግጅቶችን ያቀርባሉ። 4 ወጣቶች እና ቤተሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እንዲሰሙ እድል ለመስጠት። ወሳኝ የቨርቹዋል ሪሶርስ ትርኢት እና የባለሙያዎች ፓነል ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 4 ይካሄዳል።

እሮብ፣ ኖቬምበር 1 ቀን 6–8 p.m. በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአይምሮ ጤና ኤክስፐርት እና አቀንቃኝ የሆኑት የቀድሞ ባለሙያ የእግር ኳስ ተጫዋች ዶ/ር ጄይ ባርኔት ስለ አእምሮ ጤና አስፈላጊነት፣ መገለልን ስለማስወገድ እና እርዳታ ስለመፈለግ በአካል ተገኝተው ለተማሪዎች ንግግር ያደርጋሉ። ይበልጥ ያንብቡ.


3. ለመጪዎቹ የዲስትሪክት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እና እድሎች ቀኖችን ይቆጥቡ

በጌትስበርግ የጤንነት ትርኢት

በጌትስበርግ የዌልነስ ትርኢት፡ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 7 ቤተሰቦች 1-4 p.m. በሚደረግ ነጻ የጤና ትርኢት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።   ጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት። ትርኢቱ የሚስተናገደው በጌትስበርግ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ነው። የቤተሰብ መዝናኛ፣ የጤና ጥበቃ ሪሶርሶች፣ ዮጋ፣ የፊት ሥዕል መሣል እና ሌሎችም አዝናኝ ቆይታ ይቀላቀሉን! ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡ The high school is located at 101 Education Blvd. /in Gaithersburg።

ከትምህርት-ቤት ውጭ የሚኮንበት ሰዓት ኦክቶበር 9፡ ተማሪዎ ኦክቶበር 9 ከትምህርት ቤት ሲወጣ/ስትወጣ የሚሄድበት/የምትሄድበት ቦታ ከፈለጉ፣ KID Museum እና MCPS ለመርዳት ዝግጁ ናቸው። 2ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ቀኑን በሙዚየሙ ቤተስዳ ሜትሮ ሴንተር ወይም በዴቪስ ቤተ መፃህፍት 9 a.m.–4 p.m. ማሳለፍ ይችላሉ። ክፍያው $5 ነው።

ሁለተኛው ዓመታዊ የላቲን ሌጋሲ ኮንፈረንስ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 14 በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ታኮማ ፓርክ/ሲልቨር ስፕሪንግ ካምፓስ 9 a.m.-3 p.m. ይካሄዳል። ይህ በነፃ የሚከናወን ዝግጅት የላቲኖ ሴት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ያነቃቃል እና ያበረታታል። ለመመዝገብ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እስከ ሰኞ፣ ኦክቶበር 9 ድረስ የትምህርት ቤታቸውን ተወካይ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ ማግኘት አለባቸው።

ብሄራዊ የሂስፓኒክ ኮሌጅ ትርኢት አርብ ኦክቶበር 13 ጌትስበርግ በሚገኘው የቦህሬር ፓርክ የማህበረሰብ ማእከል 9:30 a.m. እስከ 12:30 p.m. ይካሄዳል። ተማሪዎች እስከ ረቡዕ፣ ኦክቶበር 11 ድረስ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው የኮሌጅ እና የስራ መረጃ አስተባባሪ ዘንድ መመዝገብ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ


ተናገሩ፣ ህይወት አድኑ፣ የተማሪዎች PSA ውድድር/Speak Up, Save a Life PSA Contest for Students

4. ተናገሩ፣ ህይወት አድኑ፣ የተማሪዎች PSA ውድድር

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የስቴት አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ታዳጊ ወጣቶች የኦፒዮይድ አላግባብ መጠቀምን ወይም ከመጠን በላይ መውሰድ እና ፌንታኒል በወጣቶች ላይ የሚያስከትለውን አደጋ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታዳጊ ወጣቶች ኦሪጅናል ቪዲዮ ፈጥረው አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ውድድር እየተዘጋጀ ነው። ውድድሩ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ክፍት ነው። ከፍተኛው ሽልማት $1,000፣ ሁለተኛ ደረጃ $750፣ ሶስተኛ ደረጃ እና በደጋፊዎች ተመራጭ የሆኑ አሸናፊዎች $500 ያገኛሉ። በህገ ወጥ fentanyl ህይወታቸውን ላጡ ሁለት ወጣቶች መታሰቢያነት የማግኖሊያ ፕሉምቢንግ ሽልማት ይበረከታል። ተማሪዎች እስከ 10 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ የውድድሩን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።


5. የዚህ ሳምንት መልካም ዜና

የአመራር ማሰልጠኛ ተቋም 30ኛ አመት ሞላው

ለሦስት አስርት ዓመታት፣ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲግኔቸር ፕሮግራም፣ የአመራር ማሰልጠኛ ተቋም (LTI)፣ ተማሪዎችን በጠንካራ ኢንተርዲሲፕሊን የልምድ ትምህርት፣ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች እና የአመራር ንድፈ ሃሳብ እና አተገባበርን ሲያሰለጥንና ሲያበረታታ ቆይቷል። ይህ ፕሮግራም ህይወትን እንዴት እየቀየረ እንደሚገኝ ከአሁኑ እና ካለፉት ተማሪዎች ያዳምጡ።

ስቶን ሚል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብሄራዊ ሰማያዊ ሪባን አሸንፏል

በቅርብ ጊዜ ስለተሰጠው እውቅና ከርዕሰ መምህሩ እና ከዲስትሪክቱ መሪዎች ይስሙ።

ወደ ትምህርት ቤት የእግር ጉዞ የሚደረግበት ቀን/Walk to School Day

ወደ ትምህርት ቤት የእግር ጉዞ የሚደረግበት ቀን/Walk to School Day

ተማሪዎች እሮብ፣ ኦክቶበር 4 በብሩክ ግሮቭ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሀገር አቀፍ የእግር ጉዞ እና ወደ ትምህርት ቤት የተሣካ የእግር ጉዞ አድርገዋል! እነዚህ ልጆች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ቪዥን ዜሮ የትራፊክ አደጋዎችን እና ጉዳቶችን የመቀነስ ግብ እና ለጤናማ ፕላኔት አስተዋፅዖ ለማድረግ እየረዱ ናቸው።

ወደ ትምህርት ቤት የእግር ጉዞ የሚደረግበት ቀን/Walk to School Day

ክላርክስበርግ፣ ዋልት ዊትማን ሃይ ኮረስ ተማሪዎች በአለም የባህል ፌስቲቫል ላይ የሙዚቃ ትርኢት አሳይተዋል

ሴፕቴምበር 29፣ 250 ከክላርክስበርግ እና ከዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መዘምራን ተማሪዎች 2023 የአለም ባህል ፌስቲቫል ላይ ትርኢት አሳይተዋል። በናሽናል ሞል ለሶስት ቀናት በተካሄደው የአንድነት፣ የብዝሃነት እና የሰላም በዓል180 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተሳታፊ ሆነዋል።



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)