1. ኦክቶበር 19 በሚካሄደው ቨርቹዋል የስራ ማስኬጃ በጀት መድረክ ይቀላቀሉን።
ስለ 2024–2025 የስራ ማስኬጃ በጀት የበለጠ ለማወቅ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 19 ከሠዓት በኋላ 6፡30–8 p.m. MCPS አመራርን ይቀላቀሉ። ይህ ኩነት ስለ መጪው የበጀት ሁኔታ ቨርቹዋል መድረክ እንደመሆኑ በውይይት ለመሳተፍ ልዩ ልዩ ቡድኖችን ያቀፉ ክፍለ ጊዜዎች ይኖሩታል። ይህ ዝግጅት MCPS ዋናው በይነመረብ ላይ በቀጥታ ይተላለፋል። ለመሣተፍ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
2. ለሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ ማመልከቻ እስከ ኖቬምበር 3 መቅረብ አለበት።
2ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች MCPS ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ትምህርት ቤት ማመልከቻ ፕሮግራሞች ጋር በማጣመር በሁለት የመቀበያ ጊዜያት ለሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ (MVA) ማመልከት ይችላሉ። የመጀመሪያው ዙር ከማክሰኞ፣ ኦክቶበር 10 እስከ አርብ፣ ኖቬምበር 3፣ 2023 የሚቆይ ሲሆን 2024–2025 የትምህርት አመት ለመግባት እና ለአሁኑ 2023–2024 የትምህርት አመት ለሴሚስተር 2 ተጠባባቂነት ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ይሆናል። ከጃንዋሪ 5 እስከ ፌብሩዋሪ 9, 2024 የሚቆየው ሁለተኛው ዙር ለ2024–2025 የትምህርት አመት የመጠባበቂያ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ይሆናል።
MVA የሙሉ ጊዜ ኦንላይን የመማሪያ ስልት ሲሆን ሁለቱንም የተቀናጀ (ቀጥታ) እና ያልተቀናጀ (ገለልተኛ) የመማር ማስተማር ስልት የሚጠቀም የተዋሃደ ትምህርት ሞዴል ነው። ለተጨማሪ መረጃ MVA ድረ-ገጽ ይጎብኙ።
3. ዲስትሪክት አቀፍ ዝግጅቶች እና እድሎች
ስለ ኮቪድ-19፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ እና የመተንፈሻ አካል በሽታ/RSV ክትባቶች መረጃ
ሳል እና ቅዝቃዜ ይዞ እየመጣ ላለው ወቅት ተዘጋጁ! ሴፕቴምበር 11 የጸደቀው አዲሱ የኮቪድ-19 ክትባት አሁን በአካባቢ የችርቻሮ ፋርማሲዎች እና በአንዳንድ የዶክተሮች ቢሮዎች ይሰጣል። https://www.vaccines.gov/ላይ ለኮቪድ-19 እናኢንፍሉዌንዛ ክትባቶች ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። አንዳንድ ግለሰቦች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ሽማግሌዎችን ጨምሮ፣ለመተንፈሻ አካል በሽታ/RSV ክትባት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ስለዚህ የጤና እንክብካቤ የሚያደርጉላቸውን ማማከር አለባቸው።
በዚህ ወቅት ስለሚሰጡ ክትባቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።
ከቤት ውጪ የሚሰጥ ትምህርት 60ኛ ዓመቱን ያከብራል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከቤት ውጭ የከባቢ ትምህርት ፕሮግራም 60ኛ አመቱን ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 14. ከቀኑ 10 a.m.–1 p.m. ያከብራል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከቤት ውጪ የሚከናወን የከባቢ ትምህርት መስራች ከሆነው ጆ ሃዋርድ እና በከባቢ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ከመረጡት የቀድሞ ተማሪዎች ይሰማሉ። ስለ ተፈጥሮአዊ ዓለም እና ስለ አካባቢ ጥበቃ የበለጠ ይገነዘባሉ፣ የሜሪላንድን ግብርና ያሥሳሉ፣ በደን መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ላይ ይሳተፋሉ፣ እና ወደ ቤት ለመውሰድ የዱባ ተክል ያስጌጣሉ።
ዝግጅቱ የሚካሄድበት ቦታ፦ Lathrop E. Smith Environmental Education Center at 5110 Meadowside Lane in Rockville. ለተጨማሪ መረጃ የዝግጅቱን ድረ ገጽ ይመልከቱ።
ኦክቶበር 21 በሚከተሉት ዝግጅቶች ላይ ይቀላቀሉን
STEAM ፌስቲቫል፡ በካውንቲው ውስጥ የሚገኘውን የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምህንድስና፣ የአርት/ስነጥበብ እና የሒሳብ (STEAM) ትምህርታዊ፣ ባህላዊ እና የፋይናንስ ተፅእኖን አጉልቶ ያሳያል። ቤተሰቦች በተግባራዊ እንቅስቃሴዎች፣ ንግግሮች፣ የላብራቶሪ ጉብኝቶች፣ ተፈጥሮአዊ ተሞክሮዎች፣ ኤግዚቢሽኖች እና ትርኢቶች ላይ መሳተፍ ይችላሉ። ዝግጅቱ በዊተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት - Wheaton High School, 12401 Dalewood Drive in Silver Spring. ከቀኑ 10 a.m.–1 p.m. ይካሄዳል።
የሴቶች ልጃገረዶች ስብሰባ ከቀኑ 9 a.m.–1 p.m. በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጃገረዶች በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መረጃ ሰጭ ወርክሾፖችን ያዘጋጃል። የኝኙነት መረብ የመዘርጋት ዕድል ለማግኘት ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ፥ አዝናኝ እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ፣ ጠቃሚ ክህሎቶችን ለመማር እና ለተለያዩ የሰውነት ዓይነቶች የተዘጋጁ በዋይት ሀውስ ጥቁር ገበያ በሚቀርበውን የፋሽን ትርኢት በመመልከት ይደሰታሉ! ክፍለ-ጊዜዎቹ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ የሚካሄዱ ሲሆን፣ በየክፍል ደረጃዎቻቸው የተቀናበሩ ናቸው። የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ይሰጣል። ክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኘው በዚህ አድራሻ ነው፦ 22500 Wims Road in Clarksburg.
ይመዝገቡ/RSVP
Col. Zadok Magruder ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮውን የማርች ባንድ ትርኢት 1 p.m. ላይ ያካሄዳል። ዝግጅቱ ነፃ እና ለህዝብ ክፍት ነው።አሥራ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንዶች ይሳተፋሉ፦ ክላርክስበርግ፣ ደማስከስ፣ ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ፔይንት ብራንች፣ ሴኔካ ቫሊ፣ ሮክቪል፣ ስፕሪንግብሩክ፣ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ ዋትኪንስ ሚል፣ አልበርት አንስታይን እና ማግሩደር። የማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አድራሻ፦ Magruder High School is located at 5939 Muncaster Mill Road in Rockville
አትሌቲክስ
MCPS የካውንቲ ሻምፒዮና ውድድር ወቅት ተቃርቧል! የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቲክስ በእነዚህ ኩነቶች ላይ ደጋፊዎችን ለማስተናገድ በጉጉት ይጠብቃል።
ክሮስ ካንትሪ – ኦክቶበር 21, 2023 ቦህረር ፓርክ፣ ጌትስበርግ። Meet information መረጃ Fan Focus ላይ ይገኛል።
የመስክ ገና መሰል ጨዋታ/ሆኪ - ኦክቶበር 23, 2023 ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 6 p.m ላይ ይካሄዳል።
እግር ኳስ/Soccer - ኦክቶበር 23, 2023 በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል።
ወጣት ወንዶች 5:30 p.m.
ልጃገረዶች 7:15 p.m.
የካውንቲ ሻምፒዮና ውድድር
ማዳመቅ/ቺርሊዲንግ – ኖቬምበር 1, 2023 ሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
ዲቪዝዮን III – 2 p.m.
ዲቪዝዮን II – 5 p.m.
ዲቪዝዮን I – 8 p.m.
የሴቶች ልጃገረዶች ቮሊቦል - ኦክቶበር 30, 2023 ኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 6 p.m.
4. ለብሔራዊ የአውቶቡስ ጉዞ ደህንነት ሳምንት ይዘጋጁ፣ ኦክቶበር 16–21
በሚቀጥለው ሳምንት ኦክቶበር 16–21፤ ስለ ትም/ቤት አውቶቡስ ጉዞ ደህንነት አጉልተን ስናንፀባርቅ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙትን በሙሉ በብሄራዊ የአውቶቡስ ጉዞ ደህንነት ሳምንት ምሥጋና ስለምናቀርብላቸው ከእኛ ጋር ይሳተፉ።
ወደ 2,000 የሚጠጉ የአውቶቡስ አስተናጋጆች እና የአውቶቡስ ኦፕሬተሮች ተማሪዎቻችንን በደህና ወደ 230 በላይ ትምህርት ቤቶች፣ የመስክ ጉዞዎች እና በት/ቤት ስፖንሰር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የማድረስና የማጓጓዝ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ተማሪዎቻችንን፣ ሰራተኞቻችንን እና ቤተሰቦችን ስለ ትምህርት ቤት አውቶቡስ ጉዞ ደህንነት፣ ተማሪዎች በሚሣፈሩበት እና በሚወርዱበት ጊዜ የሚጠበቅባቸውን እና እንዲሁም በትምህርት ቤት አውቶቡስ ላይ የሚጓዙ ጨምሮ ስለ አውቶቡስ ጉዞ ደህንነት ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ይህ ለሌሎች ለአሽከርካሪዎችም የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ የትምህርት ቤት አውቶቡሶች ተማሪዎችን በማጓጓዝ ላይ እያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች መቼ እና እንዴት ማቆም እንዳለባቸው እንዲያውቁ የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች የአውቶቡስ ጉዞ ህጎችን በጉልህ ለማሳየት መልካም አጋጣሚ ነው።
5. መልካም ዜና
MCPS Moment፡ MCPS Piloting Pickleball
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቲክስ በዚህ መወዳደሪያ ወቅት 11 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፒክልቦል/pickleball እንደ አዲስ ስፖርት ይጀምራሉ። MoCo Pickleball ዩ ኤስ ኤ ፒክልቦል አሰልጣኝ ሮብ ካምፕቤል፣ ለዚህ ወቅት አሰልጣኞችን ለማዘጋጀት ስልጠና ሰጥተዋል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህራን እና ሰራተኞች ሙያቸውን ለማዳበር በየጊዜው በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ በመደበኛነት ይሳተፋሉ። በዚህ ሳምንት፣የዲስትሪክቱ ሰራተኞች በሙያ ማዳበር ቀን ተማሪዎቻችን በትምህርት እንዲበለጽጉ አዳዲስ ስልቶችን በማዘጋጀት ተሳትፈዋል።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org