1. መጪው የስራ ማስኬጃ የበጀት ውይይት መድረኮች ኦክቶበር 19፣ ኦክቶበር 25፣ እና ኖቬምበር 14 ይካሄዳሉ
ስለ 2024–2025 የስራ ማስኬጃ በጀት ሂደት የበለጠ ለማወቅ MCPS ተከታታይ የውይይት መድረኮችን ያስተናግዳል። ከMCPS አመራር ጋር ለመወያየት እና በቡድን የውይይት ክፍለ ጊዜዎች የመሳተፍ እድል ለማግኘት ይቀላቀሉን። ዝግጅቶቹ በሚከተሉት ቀናት ይከናወናሉ፦
ዛሬ ምሽት፣ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 19፣ 6፡30–8 p.m., ቨርቹዋል የውይይት መድረክ። ለመሣተፍ እዚህ ጠቅ ያድርጉ። ይህ ዝግጅት MCPS ዋናው በይነመረብ ላይ በቀጥታ ይተላለፋል። ይመዝገቡ/RSVP.
እሮብ፣ ኦክቶበር 25, 6:30–8 p.m., በደማስከር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Damascus High School, 25921 Ridge Road in Damascus. ይመዝገቡ/RSVP.
ማክሰኞ፣ ኖቬምበር 14፣ ሠዓቱ ወደፊት ይወሰናል፣ በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቤተዝዳ/Walter Johnson High School, 6400 Rock Spring Drive in Bethesda. ይመዝገቡ/RSVP.
2. ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ማመልከቻ
የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ParentVUE ውስጥ የሚገኘውን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት common application በመጠቀም ለሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም፣ 9-11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ መለዋወጥ ክፍለ ጊዜዎች የሚኖሩ ስለሆነ ሁሉንም ቀናት ልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ያገኛሉ።
ማመልከቻዎች እስከ አርብ፣ ኖቬምበር 3 ድረስ ተጠናቀው መቅረብ አለባቸው። ፕሮግራሞቹ-በጨረፍታ፣ ብቁነት፣ ዘወትር የሚቀርቡ ጥያቄዎች እና ኦክቶበር open house dates በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።
በዚህ አመት አዲስየተጀመረ፡ የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ( Walt Whitman High School) የአመራር አካዳሚ ለማህበራዊ ፍትህ (LASJ) ለሁሉም 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች ክፍት ነው። ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ
3. ቦርዱ በፖሊሲ IJA ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፈልጋል
የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ IJA፣ በትምህርት ቤት ካውንስሊንግ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ማሻሻያ ላይ አስተያየት ይፈልጋል። የፖሊሲ IJA ማሻሻያ ረቂቅ ከአፕሪል 26, 2023 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት የቀረበ ሲሆን የአስተያየት መስጫው ጊዜ ኖቬምበር 6, 2023 ላይ ይዘጋል። የተደረጉት ለውጦች መግለጫ፣ ረቂቅ ለውጦች እና የህዝብ አስተያየት መስጫ ቅጾች የህዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ፖሊሲ ድረገጽ ላይ ይገኛል። የቋንቋ ትርጉሞች ይኖራሉ።
4. ዲስትሪክት አቀፍ ዝግጅቶች እና እድሎች
ቅዳሜ ኦክቶበር 21፡
STEAM ፌስቲቫልሲልቨርስፕሪንግ በሚገኘው ዊተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከቀኑ 10 a.m.–1 p.m. ይካሄዳል። Wheaton High School, 12401 Dalewood Drive in Silver Spring.
የልጃገረዶች ጉባኤ በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 9 a.m.–1 p.m. ይካሄዳል። Clarksburg High School, 22500 Wims Road in Clarksburg. ይመዝገቡ/RSVP
Col. Zadok Magruder ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 5939 Muncaster Mill Road in Rockvilleሮክቪል በሚገኘው የሙዚቃ ማርሽ ባንድ ማሳያ 1 p.m., ትርኢት ያቀርባል።እባክዎን ያስተውሉ፡ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት፣ ዝግጅቱ ከተሰረዘ MCPS ድረ ገጽ ላይ 9፡30 am መልዕክት ይለጠፋል።
ስለ አእምሮ ጤንነት የግንዛቤ ሳምንት ከኦክቶበር 30 እስከ ኖቬምበር 4
ከ 6–8 p.m. እሮብ፣ ኖቬምበር 1 በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Richard Montgomery High School) የቀድሞው ፕሮፌሽናል ፉትቦል ተጫዋች አሁን የአእምሮ ጤና ባለሙያ እና አቀንቃኝ ዶክተር ጄይ ባርነት/Dr. Jay Barnett ስለ አእምሯዊ ጤንነት አስፈላጊነት፣ መገለልን ስለማስወገድ እና እርዳታ መጠየቅ ለተማሪዎች ንግግር ያደርጋል። የሚሳተፉ ተማሪዎች SSL ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ስለ አእምሮ ጤንነት የግንዛቤ ሳምንት ዝግጅቶች የበለጠ ያንብቡ።
ከትምህርት-ቤት ውጭ የሚከናወኑ ዝግጅቶች ጊዜ፣ SSL ሰዓት ያገኛሉ
ሁሉንም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን የሚመለከት ጥሪ፡ ኖቬምበር 1 የከባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ የበጎ ፈቃደኞች ቀን በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለሚካሄድ መጥታችሁ ተሳተፉ፣ ቦታው፦ Gaithersburg High School, 101 Education Blvd /በጌትስበርግ።
PSA በቪዲዮ ውድድር ላይ በመሣተፍ SSL ሰዓት ያግኙ
$1,000 የማሸነፍ እድል፡ ተናገር/ሪ፣ ህይወት አድን PSA ውድድር
5. የዚህ ሳምንት ጉልህ ጉዳዮች
ኦክቶበር ብሔራዊ የርእሰ መምህራን ወር ነው. ለሁሉም ርእሰ መምህራን ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ስለሚያደርጉት በጎ ነገር ሁሉ እናመሰግናለን።
በኔልስቪል መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ለሆኑት ሚስ ባርባራ ኢስኮባር እንኳን ደስ አለዎት። ኤስኮባር በቅርቡ በተካሄደው "Hispanic Leadership Awards Gala" የዓመቱ ምርጥ የሂስፓኒክ አስተማሪ ሽልማቶች አግኝታለች።
የላቲና ሌጋሲ ኮንፈረንስ ከ300 የሚበልጡ ምሁራንን በአካዳሚክ እና በግል ሕይወታቸው ስኬታማ ለማድረግ ያሉትን እድሎች እና ግብዓቶች እንዲማሩ አሰባስቧል።
ቤተሰቦች፣ MCPS የቀድሞ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት 60ኛውን ከቤት ውጪ የከባቢ ተፈጥሮ አጠባበቅ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለማክበር እንድትገኙ ተጋብዛችኋል። እነዚህ ፕሮግራሞች ለሁሉም MCPS ተማሪዎች ተግባራዊ የሳይንስ ትምህርት ይሰጣሉ።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org