መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ኖቨምበር 02 2023

1. ትምህርት ቤቶች ለአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት እውቅና ይሰጣሉ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሙሉ የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከማህበረሰቡ ጋር የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ጀምረዋል። በዚህ ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 4 ከጠዋቱ 11፡30 ጠዋት 11:30 a.m.–1 p.m. ያለው የቨርቹዋል ዝግጅት እና የፓናል ውይይት ስለ MCPS የአእምሮ ጤና ድጋፍ አቅራቢዎች እና የማህበረሰብ አጋሮችን በሚመለከት ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው መረጃ ይሰጣል።


2. ከእርስዎ ለመስማት እንፈልጋለን! ኖቬምበር 2 እና ኖቬምበር 14 በሚካሄዱት ስለ ስራ ማስኬጃ በጀት የውይይት መድረኮች ይቀላቀሉን

የእርስዎ ድምጽ አስፈላጊ ነው፤ እና የእርስዎን ግንዛቤ ለመስማት እንጓጓለን! ለቀጣዩ የቨርቹዋል የሥራ ማስኬጃ ባጀት የውይይት መድረክ ይቀላቀሉን። የትምህርት ቦርድ አባላት እና የMCPS አመራር ባቀረቡልዎት የትብብር ተነሳሽነት ጥሪ ይሳተፉ።

እንደሚገኙ ለማወቅ እንድንችል ይመዝገቡ/RSVP

በተጨማሪም እሮብ፣ ኖቬምበር 8 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ብቻ ክፍት የሆነ መድረክ ነው።


3. ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ማመልከቻ የሚቀርብበት ቀነ-ገደብ እስከ ኖቬምበር 8 ድረስ ተራዝሟል።

የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ParentVUE ውስጥ የሚገኘውን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት common application በመጠቀም ለሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም፣ 9-11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች ይኖራሉ። ሁሉም ቀኖች ልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ይኖራሉ።

ማመልከቻዎች እስከ እሮብ፣ ህዳር 8 ድረስ ተጠናቀው መቅረብ አለባቸው። የፕሮግራሞች ዝርዝር-በጨረፍታ፣ስለ ብቁነት፣ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና ኦፕን ሃውስ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

2024-2025 ትምህርት ቤት ለመግባት ሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ (MVA) ማመልከቻዎች አርብ፣ ኖቬምበር 3 መድረስ አለባቸው። 2023-2024 ዓመት የቨርቹዋል አካዳሚ 2ኛ ሴሚስተር የተጠባባቂ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ማመልከቻዎች እንዲሁ በኖቬምበር ላይ ይቀርባሉ። 3. ከኖቬምበር 3, 2023 በኋላ የሚቀርብ ማመልከቻ ግን ፌብሩዋሪ 9, 2024፣ላይ ወደ 2024-2025 የተጠባባቂዎች ዝርዝር ውስጥ ይቀመጣል። ለበለጠ መረጃ የMVA ድረገጽ ይጎብኙ።


4. ዝግጅቶች እና ልዩ ልዩ እድሎች

የትራንስፖርት/የመጓጓዣ ቡድናችንን ይቀላቀሉ

MCPS ለአውቶቡስ ሾፌሮች፣ የአውቶቡስ ረዳቶች እና ለመካኒኮች የስራ እድል የሚገኝበት አውደ ርእይ አርብ፣ ኖቬምበር 3. ከጠዋቱ 10 a.m.–1 p.m. የሚካሄድ እያዘጋጀ ነው። አውደ ርዕዩ የሚካሄድበት ቦታ ሮክቪል፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville. ነው። ይበልጥ ያንብቡ.

ለMCPS ወላጆች ነጻ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ይሰጣል

የማህበረሰብ ትምህርት (C2C) ድርጅት እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋ ለሆነ ሰዎች (ESL)፣ GED፣ የኮሌጅ መሰናዶ፣ እና የዲጂታል ሊተርሲ ትምህርቶችን በነጻ ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ C2C ድረ ገጽ ይጎብኙ

መመዝገቢያ ቅጽ

ጥሬ ገንዘብ እና SSL ሰዓቶችን የማግኘት ዕድል

የተጠራጠሩትን በግልጽ ይናገሩ፣የህይወት ማዳን PSA ውድድር ላይ ይሳተፉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የስቴት አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ታዳጊ ወጣቶች የኦፒዮይድ አላግባብ መጠቀምን ወይም ከመጠን በላይ መውሰድ እና ፌንታኒል በወጣቶች ላይ የሚያስከትለውን አደጋ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታዳጊ ወጣቶች ኦሪጅናል ቪዲዮ ፈጥረው አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ውድድር እየተዘጋጀ ነው።


5. የዚህ ሳምንት አንፀባራቂ ሁነቶች

ተማሪዎች እንዴት አቀናብረው እንደሚጽፉ እና የትምህርት ቦርድ ምስክርነትን እንደሚያቀርቡ ይማራሉ

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዴት አቀናብረው መጻፍ እንደሚችሉ ለመማር የአንድ ቀን አውደ ጥናት ይካፈላሉ፣ እና ስለ ትምህርት ቦርድ (BOE) ምስክርነት በቦርድ አባላት ፊት በማቅረብ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ ማየት ስለሚፈልጓቸው ለውጦች በብቃት የማቀንቀን ተግባር ያከናውናሉ። ይበልጥ ያንብቡ.

የፎል ወቅት የካውንቲ ሻምፒዮና በዚህ ሳምንት ተጠናቋል። ከፍተኛ ደረጃ ላይ የወጡትን ቡድኖች ዝርዝር ይመልከቱ።

MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የአካባቢ ጥበቃ ዲፓርትመንት (DEP) ጋር በመተባበር የተማሪዎች አካባቢ ጥበቃ የበጎ ፈቃደኞች ቀን ኖቬምበር 1 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተናግዷል። ይበልጥ ያንብቡ.

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ጁንየር ካውንስል (MCJC) የዓመቱ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ወደ 200 የሚጠጉ የመለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ተሳትፈዋል። በዚህ የትምህርት አመት የመጀመሪያው የካውንቲ ጠቅላላ ጉባኤ። ትምህርት ቤቶቻቸውን ወክለው ድምፃቸው እንዲሰማ ለማድረግ። ስለ ተማሪዎች የአመራር እድሎች የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)