1. ዲሴምበር 14 ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርበውን የበጀት እቅድ የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ለበጀት አመት 2025 ያዘጋጁትን የስራ ማስኬጃ በጀት ዲሴምበር 14 ከቀኑ 6 p.m. ላይ በኦዴሳ ሻነን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያቀርባሉ። ማህበረሰቡ የሚቀርበውን የባጀት ዝርዝር MCPS ድረ ገጽ፣ MCPS-TV YouTube ቻነል እና MCPS-TV ቻናሎች አይ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ስለሚተላለፍ በቀጥታ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል።
2. ማሳሰቢያዎች፦ በከባድ የአየር ሁኔታ ወቅት ከ MCPS ጋር ይገናኙ
የክረምቱ የአየር ሁኔታ በቅርብ ርቀት ላይ እያለ፣ MCPS መጥፎ የአየር ሁኔታ ሲኖር ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት፣ ዘግይቶ ስለመክፈት፣ እና ተማሪዎችን ከመደበኛው ሰአት በቅድሚያ ስለማሰናበት ለማሳወቅ ብዙ መንገዶችን እንደሚጠቀም ያስታውሱ። ስለ ከባድ የአየር ሁኔታ ውሳኔዎች እንዴት እንደሚደረጉ እና ስለማንኛውም ለውጦች እንዴት መረጃ እንደሚያገኙ የበለጠ ይወቁ።
3. ስለ ዊንተር/ክረምት የስፖርት ተመልካቾች ደህንነት
የክረምቱን ወቅት ለመጀመር፣ MCPS አትሌቲክስ የተነቃቃ ስፖርታዊ ጨዋነት እና የተመልካች ደህንነት ሳምንት ከዲሴምበር 5-9 ይካሄዳል። MCPS ለተማሪ-አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ ተመልካቾች እና ማህበረሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹና ሠላማዊ አካባቢን ለማመቻቸት ቁርጠኛ ነው። የአትሌቲክስ ክንውኖች እና ሂደቶች የሚመሩበትን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ መመልከትዎን ያረጋግጡ። የዊንተር/የክረምት ወቅት የመክፈቻ ምሽት ማክሰኞ ዲሴምበር 5 ነው።
4. ዝግጅቶች እና ልዩ ልዩ እድሎች
የሠመር ራይዝ ተቀባይ አስተናጋጆች/Summer RISE 2024 Hosts
ቀጣዩን ትውልድ ለስራ ሃይል ለማዘጋጀት እና ችሎታቸውን ለመገንባት ፍላጎት አለዎት? የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ሲንየር ተማሪዎች የሠመር ራይዝ 2024 ፕሮግራም አካል በመሆን ስለ ስራ ቦታዎ እና የስራ መስክዎ እንዲያውቁ እርዷቸው። ይበልጥ ያንብቡ.
የሽልማት መስጫ ወቅት በመካሄድ ላይ ስለሆነ ዛሬውኑ እጩዎችን ይጠቁሙ!
እውቅና ሊሰጠው/ሊሰጣት የሚገባ ሰራተኛ፣ አስተዳዳሪ ወይም አስተማሪ አለ? ልዩ ብቃት ያላቸው ሰራተኞችን፣ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን እውቅና ለመስጠት እጩዎችን ለበርካታ ሽልማቶች ለመጠቆም ክፍት ነው።
5. የዚህ ሳምንት አንፀባራቂ ሁነቶች
MCPS ቲቪ የሚያቀርባቸው፡ በደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምሳ ሰአት ጉዞ
በ MCPS በአስተማሪነት 30 ዓመታት ካገለገለ በኋላ፣የደማስከስ ርእሰመምህር ኬቨን ያትስ አሁንም ለተማሪዎቹ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት አለው። በየቀኑ በክፍት የምሳ ሠዓት በካምፓሱ ዙሪያ እና በህብረተሰቡ አካባቢ ብስክሌቱን እየነዳ፣ ጁንየሮችን እና ሲንየር ተማሪዎችን ሰላምታ በመስጠት ደህንነታቸውን እንዲጠብቁ እና ንቁ እንዲሆኑ ያበረታታል።
የሴኔካ ቫሊ ሲኒየር ለአንድ ቀን የካውንስል አባልነት ውድድር አሸንፋለች
በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪ ፎላሻዴ ኢፔቢኑ/Folashade Epebinu በሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ዊል ጃዋንዶ/Will Jawando አስተናጋጅነት የተካሄደውን የዘንድሮ ለአንድ ቀን የካውንስል አባልነት ውድድር አሸንፋለች። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች ዛፎችን በመትከል ለመርዳት ከካውንቲው ጋር ይተባበራሉ
S. Christa McAuliffe አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ሰራተኞች ዛፎችን ለመትከል እና የሜሪላንድ አምስት ሚሊዮን ዛፎችን የመትከል ተነሳሽነትንለማክበር ኖቬምበር 30 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአካባቢ ጥበቃ መምሪያን ተቀላቅለዋል።
MCPS የዘገባ ማእከልንየቅርብ ጊዜዎቹን ዜናዎች እና መረጃዎች፣ የፎተግራፍ ክምችት/ጋለሪዎች እና ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org