1. የትምህርት ቦርድ የ2024–2025 የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር አጽድቋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቦርድ የ 2024-2025 የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር አጽድቋል። የቀን መቁጠሪያው የትምህርት መስተጓጎሎችን ውስን በማድረግ እና የትምህርት ስርአቱ በሰራተኞቻችን የሙያ ማዳበር የትምህርት ቀናት ላይ ቀጣይነት ያለው መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ከማህበረሰቡ ለተገኘው ግብአት ምላሽ ይሰጣል። ቁልፍ የሆኑ ቀናትን ያንብቡ።
2. ዓመታዊ ሪፖርት እና የትምህርት ቤት መግለጫዎች ዳሽቦርድ አሁን ተዘጋጅቷል
የዲስትሪክቱ መስተጋብራዊ ኦንላይን 2022-2023 አመታዊ ሪፖርት ለማህበረሰቡ እና አዲሱ የትምህርት ቤቶች መግለጫዎች ዳሽቦርድ አሁን ተዘጋጅቷል።
አመታዊ ሪፖርቱ ስለ ዲስትሪክቱ፣ ስለ ተማሪዎች አፈጻጸም፣ የተግባር አፈጻጸም መረጃ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ራዕይ እና ተልዕኮውን ለማሳካት የተወሰዱ እርምጃዎችን ለህብረተሰቡ ያቀርባል።
የትምህርት ቤት መግለጫዎች ዳሽቦርድ በጨረፍታ የትምህትይ ቤቶችን ሪፖርት የሚገልፅ ሲሆን ከፀረ-ዘረኝነት ስርዓት የድርጊት መርሃ ግብር ጋር በማጣጣም ስለ ዲስትሪክቱ እና የትምህርት ቤቶችን ደረጃ መረጃ ግልፅ ግንዛቤ ይሰጣል። ይበልጥ ያንብቡ.
3. ዲሴምበር 14 ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርበውን የበጀት እቅድ የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ለበጀት አመት 2025 ያዘጋጁትን የስራ ማስኬጃ በጀት ዲሴምበር 14 ከቀኑ 6 p.m. ላይ በኦዴሳ ሻነን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያቀርባሉ። ማህበረሰቡ የሚቀርበውን የባጀት ዝርዝር MCPS ድረ ገጽ፣ MCPS-TV YouTube ቻነል እና MCPS-TV ቻናሎች አይ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ስለሚተላለፍ በቀጥታ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል።
4. የዊንተር ወቅት እና የጤና አጠባበቅ ማሳሰቢያዎች
አስከፊ የአየር ሁኔታ ወቅት
ወደ ክረምት የአየር ሁኔታ ስንሸጋገር፣ MCPS ከአስከፊ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ምክኛት የት/ቤቶችን ዘግይቶ መጀመር፣ ት/ቤቶችን መዝጋት እና ተማሪዎችን ከመደበኛው ሠዓት አስቀድሞ ማሰናበትን በተመለከተ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ እንዲደርስዎት ለማድረግ ጥረት ያደርጋል።
MCPS ስድስት የክወና ሁኔታ አማራጮች አሉት፣ እነዚህም MCPS ዋናው ድረ ገጽ ላይ ለመረዳት ቀላል በሆነ መንገድ በተለያየ ቀለም መልእክቶች የሚተላለፉ ሲሆን ይህ መረጃ ከእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ድረ ገጽ ጋር የተያያዘ ነው። ይበልጥ ያንብቡ.
በሌላ ዜና፣ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ MCPS ባስተላለፈው InteliSwab COVID-19 ፈጣን መመርመሪያ መሳሪያዎች ላይ አገልግሎቱ የሚያበቃበትን ቀንFDA ሌላ ስድስት ወራት አራዝሟል። የመመርመሪያ እቃዎቹ የአገልግሎት ጊዚያቸው ያበቃል ተብሎ ከታተመበት ከአሁን ጀምሮ ለ15 ወራት ምርመራ ለማድረግ ጥሩ ናቸው።
በህመም ጊዜ በቤት ውስጥ የመቆየት የጤና መመሪያ፡ ሲታመሙ ቤት መቆየት የትምህርት ቤታችንን ማህበረሰብ ጤንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ወደ ትምህርት ቤት ከመሄድ የሚከለክል መታመም ማለት ምን ያህል ህመም ነው? መቼ ከት/ቤት መቅረት አስፈላጊ እንደሆነ ለማወቅ እንዲረዳዎት ከብሔራዊ የትምህርት ቤት ነርሶች ማህበር የተዘጋጀውንይህን መመሪያ ይመልከት።
5. የዚህ ሳምንት አንፀባራቂ ሁነቶች
ለማማ ዋይልድካት አክብሮት
የዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ሰራተኞች ለታላቋ ዋይልድካት ያላቸውን አድናቆት አሳይተዋል፣ ጡረታ ለወጡት ርዕሰ መምህርት ጄኒፈር ቤከር፣ ኖቬምበር 30 ጡረታ በወጡበት ትምህርት ቤት በአስገራሚ ጭብጨባ አክብሮት ሰጥተዋቸዋል። ተጨማሪ ያንብቡ።
የ MCPS ስርዓት አቀፍ የአትሌቲክስ ዳይሬክተር የ MPSSAA ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል
የ MCPS ስርዓት አቀፍ አትሌቲክስ ዳይሬክተር ዶክተር ጄፍ ሱሊቫን የሜሪላንድ ፐብሊክ ስኩልስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አትሌቲክስ ማህበር (MPSSAA) ፕሬዝዳንት ሆነው በአንድ ድምፅ ተመርጠዋል። MPSSAA በስቴቱ ውስጥ ባሉት 24 ፐብሊክ ስኩልስ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አትሌቲክስን ይቆጣጠራሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
ተማሪዎች በምግብ ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱ ምግቦችን ቅምሻ አድርገዋል
የሬድላንድ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን እርካታ ለመለካት በቅርብ ጊዜ የተዘጋጁ ሁለት የምግብ አይነቶችን ለመቅመስ እድል አግኝተዋል። ተማሪዎች ቬጋን ፓስታ እና የድንች ምግቦችን ቅምሻ አድርገዋል፣ ምግቦቹ በትምህርት ቤት ምሳ ዝርዝር ውስጥ መካተት አለበት ወይ? በሚለው ላይ አስተያየት ሰጥተዋል። የምግብ እና የተመጣጠነ አመጋገብ አገልግሎት ክፍል በውሳኔ አሰጣጡ ሂደት ውስጥ ድምፃቸው መወከሉን ለማረጋገጥ በተማሪ-ተኮር የጣዕም ሙከራ እድሎችን መስጠት ይቀጥላል።
MCPS የዘገባ ማእከልንየቅርብ ጊዜዎቹን ዜናዎች እና መረጃዎች፣ የፎተግራፍ ክምችት/ጋለሪዎች እና ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org