መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 14 ቀን 2023

1. ሱፐርኢንተንደንት ያቀረቡትን የበጀት እቅድ ዛሬ ማታ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት የበጀት አመት 2025 የስራ ማስኬጃ በጀት እቅድ ዛሬ ምሽት 6 p.m. በኦዴሳ ሻነን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያቀርባሉ። የሚያቀርቡትን የባጀት እቅድMCPS ድረ ገጽMCPS-TV YouTube ቻነል እና MCPS-TV ቻናሎች ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል። ሱፐርኢንተንደንቷ ለቀጣዩ የበጀት አመት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች ይፋ ያደርጋሉ። 


2. ለሜሪላንድ "Seal of Biliteracy" የፈተና ቀናት ተዘጋጅተዋል 

ብቁ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዝና ያለው የሜሪላንድ "Seal of Biliteracy" ለመፈተን እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ።

ከእንግሊዘኛ የተለዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ የአገሬው ተወላጅ/ዝርያ ያላቸው ተናጋሪዎች፣ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የአለም ቋንቋዎች ትምህርቶችን እየተማሩ ያሉ እና/ወይም ከቋንቋ የተለየ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎች ለፈተና እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ። ስለ "Seal of Biliteracy" ለመጠየቅ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን የዓለም ቋንቋዎች ሪሶርስ አስተማሪዎችን ማነጋገር ይችላሉ። በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለ ፈተና ቀናት ተጨማሪ መረጃ ያንብቡ። ለበለጠ መረጃ MCPS ድረገጽ ይጎብኙ።


3. የ 2024 ሠመር ራይዝ አስተናጋጅ በመሆን ተማሪዎች የስራ ልምድ እንዲያገኙ በመርዳት ይተባበሩ።

ከ 2024-2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዝነኛ/ስኬታማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር እና ሲንየር ተማሪዎች ጋር የስራ ልምድዎን ለማካፈል ይፈልጋሉ? ለ 2024 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም እንዴት ተቀባይ/አስተናጋጅ መሆን እንደሚችሉ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ!

የፓርትነርሺፕ ዲፓርትመንት ተማሪዎች በአካል፣ በቨርቹዋል ወይም በሁለቱ ጥምር ልምድ እንዲያገኙ ቢያንስ ለ50 ሰዓታት ተቀብለው የሚያስተናግዱ የንግድ ድርጅቶችን፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ይፈልጋል። ይበልጥ ያንብቡ. 


4. ማሳሰቢያዎች እና እድሎች

የጥገና እና ኦፕሬሽን የስራ አውደርእይ ዲሴምበር 15 ይካሄዳል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጥገና እና ኦፕሬሽን ዲቪዚዮን አርብ፣ ዲሴምበር 15 የስራ አውደርዕይ ያስተናግዳል። ለቧንቧ ሥራ ባለሙያዎች፣ ለኤሌክትሪክ ቴክኒሻኖች፣ ለጥገና አናጺዎች፣ የኤሌክትሪክ ጥገና ባለሙያዎች እና HVAC-R ቴክኒሻኖች በቦታው ላይ የመቀጠር ዕድሎች ይኖራሉ።

ከጠዋቱ 7 a.m. ጀምሮ እስከ 1 p.m. እና ከ 3 p.m. እስከ 7 p.m. ድረስ ሁለት ክፍለ ጊዜዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ አውደ ርዕዩ የሚካሄድበት አድራሻ ይሄ ነው፦ Division of Maintenance and Operations offices, 8301 Turkey Thicket Drive, Building A, First Floor, Gaithersburg ስራዎች የሚገኙት ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ፈረቃዎች ነው።

ለ MCPS ወላጆች ነጻ የእንግሊዝኛ ትምህርት ይሰጣል

የማህበረሰብ ትምህርት (C2C) ድርጅት እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋ ለሆነ ሰዎች (ESL)፣ GED፣ የኮሌጅ መሰናዶ፣ እና የዲጂታል ሊተርሲ ትምህርቶችን በነጻ ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ C2C ድረ ገጽ ይጎብኙ.

መመዝገቢያ ቅጽ


5. የዚህ ሳምንት አንፀባራቂ ሁነቶች 

ተማሪዎች ችሎታቸውን "Local SkillsUSA" ውድድር ላይ ያሳያሉ

ከማስዋብና ማስጌጥ/ኮስሞቶሎጂ እና ከኤሌክትሪካል ኮንስትራክሽን ሽቦ መዘርጋት እስከ አውቶማቲክ አዲስ ገፅታ መፍጠር፣ የቶማስ ኤዲሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮውን የአካባቢ SkillsUSA ውድድር ያስተናግዳል። "SkillsUSA" የተማሪዎች የሙያ ክህሎቶቻቸውን በውድድር ለማሳየት የመጀመሪያ እድል ነው። ተማሪዎች የተማሩትን በትምህርት ክፍሎች፣ በቤተ ሙከራዎች እና በስራ ቦታዎች ላይ የትምህርት ፕሮጄክቶችን የመጠቀም እድል አላቸው። ይበልጥ ያንብቡ. 

የስቶን ሚል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ ሰማያዊ ሪባን ባንዲራ ከፍ አድርጓል

የስቶን ሚል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብሄራዊ ብሉ ሪባን ባንዲራውን ከፍ ለማድረግ ዲሴምበር 13 በትምህርት ቤቱ ስብሰባ አድርጓል። ትምህርት ቤቱ በሴፕቴምበር ወር በዩኤስ የትምህርት ዲፓርትመንት (USDE) የብሉ ሪባን አክብሮት ተሰጥቷል። የስቶን ሚል ብሔራዊ የብሉ ሪባን አሸናፊ ተብሎ ለመሰየም 43ኛው የ MCPS ትምህርት ቤት ነው ተጨማሪ ያንብቡ።

MCPS የስድስተኛ ክፍል ተማሪ መልሶ የመስጠት ወቅት 

በሞንትጎመሪ ቪሌጅ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው አናቤሌ ሊ/Annabelle Lee በዚህ የበዓል ሰሞን በአመታዊ የአሻንጉሊት መሰብሰቢያ መኪናዋ ሣቅ እና ደስታ ለመስጠት ተልእኮ ላይ ትገኛለች። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለተቸገሩ ልጆች ለመስጠት ከ "Wheaton Dance Twirl" ቡድኖች አሻንጉሊቶችን፣ ጃኬቶች፣ እና ካልሲዎችን አግኝታለች።


MCPS የዘገባ ማእከልንየቅርብ ጊዜዎቹን ዜናዎች እና መረጃዎች፣ የፎተግራፍ ክምችት/ጋለሪዎች እና ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)