1. ሱፐር ኢንተንደንቷ $3.3 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት እቅድ አቅርበዋል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ለ 2025 የበጀት ዓመት $3.3 ቢሊዮን ዶላር የስራ ማስኬጃ በጀት ዝርዝር እቅድ አቅርበዋል። የዲስትሪክቱ ትኩረት ለሁሉም ተማሪዎች የወደፊት ትምህርታቸውን በማበልፀግ ላይ ይቀጥላል።
የባጀት ድጋፉ የተማሪዎችን በሂሳብ እና ሊተርሲ ትምህርት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቁልፍ ጉዳዮችን የሚያበረታቱ ቁልፍ ኢንቨስትመንቶች፣በሰራተኞች ማህበር ስምምነቶች መሠረት በሚቀጥለው ዓመት ቢያንስ 3% የደመወዝ ጭማሪ እና በቀጣዩ አመት የሚደረግ ምልመላ እና የትምህርት ቤቶችን ደህንነት ለመደገፍ እና ትምህርት ቤቶች እና ቤተሰቦች በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ኢንቨስትመንቶች ላይ ይውላል። ይበልጥ ያንብቡ
2. ስለ መልካም እና ጤናማ በዓላት ከይምህርት ስርዓት የጤና ቢሮ የተላከ መልእክት
ለዊንተር ዕረፍት ስንዘጋጅ፣ ጉንፋን እና እንፍሉዌንዛ በከፍተኛ ሁኔታ የሚበረታበት ወቅት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል! ኮቪድ-19፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ የጉሮሮ ምርቀዛ፣ የእጅ፣ የእግር እና የአፍ በሽታ እና ሌሎች የተለመዱ ኢንፌክሽኖችን ጨምሮ በርካታ ህመሞች ምክንያት ከት/ቤቶቻችን ሰራተኞች እና ተማሪዎቻችን ከትምህርት ቤት የመቅረት ሁኔታ እየጨመረ መሄዱን ተመልክተናል።
የአካባቢ ሆስፒታሎችም የመተንፈሻ አካላት ህመም ያለባቸውን በተለይም ለከባድ በሽታ ተጋላጭ የሆኑትን ህሙማን በመንከባከብ ላይ የተጠመዱ ናቸው። ይህ ትንንሽ ሕፃናትን እና ልጆችን፣ እንዲሁም አዛውንቶችን እና አንዳንድ የጤና እክል ያለባቸው ግለሰቦችን ያጠቃልላል። መልእክቱን በሙሉ ያንብቡ፦
3. ከእረፍት በፊት የተሰጠ ማሳሰቢያ
MCPS ስድስት የክወና ሁኔታ አማራጮች አሉት፣ እነዚህም MCPS ዋናው ድረ ገጽ ላይ ለመረዳት ቀላል በሆነ መንገድ በተለያየ ቀለም መልእክቶች የሚተላለፉ ሲሆን ይህ መረጃ ከእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ድረ ገጽ ጋር የተያያዘ ነው። ይበልጥ ያንብቡ.
"Maryland Seal of Biliteracy Award" የፈተና ቀናት ሽልማት ተዘጋጅቷል
በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ታዋቂ ለሆነው "Maryland Seal of Biliteracy" ፈተና እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶች
2023 የሠመር ወቅት ለተጠናቀቀ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሠአት አገልግሎቶች ተማሪዎች ሁሉንም SSL የተግባር ማረጋገጫ ቅጾችን ጃንዋሪ 5, 2023 ድንጋጌ መሠረት ወደ SSL አስተባባሪዎቻቸው እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ።
እንዲሁም MCPS በማርቲን ሉተር ኪንግ (MLK) የአገልግሎት ሳምንት (ጃኑወሪ 13-21, 2024) የአገልግሎት እድሎችን እና ሌሎች መልካም ተግባራትን ለማስተዋወቅ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማእከል (MCVC) ጋር እየሰራ ነው። በርካታ የአገልግሎት እድሎችን ዝርዝር ለማየት MCVC ድረገጽ ይመልከቱ፤ እንዲሁም ስለ እድሎቹ እና የግዜ ገደቦች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት MCPS ድረ ገጽ ይጎብኙ።
የሠመር ራይዝ ተቀባይ/አስተናጋጅ ለመሆን ዛሬውኑ ይመዝገቡ
ከ 2024-2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስኬታማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር እና ሲንየር ተማሪዎች ጋር የስራ ልምድዎን ለማካፈል ይፈልጋሉ? ለ 2024 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም እንዴት ተቀባይ/አስተናጋጅ መሆን እንደሚችሉ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ! ይበልጥ ያንብቡ.
4. የኮሌጅ፣ የስራ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ዝግጁነት ፈለግ - ቀዳሚ ሊተርሲ
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለኮሌጅ፣ለስራ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት ዝግጁነት ላይ የመዋዕለ ሕፃናት ቀዳሚ የሊተርሲ ችሎታ መገንባት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው። ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ለምን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እና MCPS ተማሪዎችን ለማዘጋጀት ምን እየሰራ እንደሆነ ግንዛቤ ያግኙ።
5. የዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ
MCPS አጠቃላይ የወጣቶች የአእምሮ ጤና እና ራስን ማጥፋት የመከላከል አቀራረብን የማዳበር ፕሮግራም መርጧል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ The Jed Foundation (JED) እና በትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ማህበር (AASA) የተማሪዎችን የአእምሮ ጤና እና ስሜታዊ ደህንነት ለማጠናከር በአጋርነት በተፈጠረው የዲስትሪክት አጠቃላይ አቀራረብ (DCA) ላይ ለመሳተፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ የት/ቤት ዲስትሪክቶች እጩዎች መካከል ተመርጠዋል ይበልጥ ያንብቡ.
የዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፈንታኒል PSA ከሚያስከትለው አስከፊ ጉዳት ህይወት ለማዳን፣ በግልፅ የመናገር፣ውድድር አሸንፈዋል
የዋትኪንስ ሚልስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች Jabea Ewane፣ ስቲቨን ሳንቲያጎ እና ቶማስ ፔቲት PSA ባቀረቡት የቪድኦ ውድድር ከፍተኛውን ሽልማት እና የደጋፊዎችን ድምጽ አሸንፈዋል፣ Forever 16። ይበልጥ ያንብቡ.
የሮቤርቶ ክሌሜንቴ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ለህብረተሰቡ "Holiday Mall" የበአል ትርኢት ያቀርባል
ከአሻንጉሊት እስከ ቤት እቃዎች፣ የመታጠቢያ እና የሰውነት እቃዎች የሮቤርቶ ክሌሜንቴ ማህበረሰብ በዚህ ሳምንት በትምህርት ቤቱ ተገኝተው “Holiday Mall” ነጻ ስጦታዎችን እንዲቀበሉ ተጋብዘዋል። የአዲስ ኪዳን ህብረት ቤተክርስቲያን/New Covenant Fellowship Church መምህራን፣ሠራተኞች እና ምእመናን ባለፈው ጃኑዋሪ አዳዲስ እና ትንሽ ያገለገሉ ስጦታዎችን ለግሰዋል። ይበልጥ ያንብቡ.
MCPS የዘገባ ማእከልንየቅርብ ጊዜዎቹን ዜናዎች እና መረጃዎች፣ የፎተግራፍ ክምችት/ጋለሪዎች እና ቪዲዮዎችን ይመልከቱ።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org