የጤና ጥበቃ መረጃ
ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ስርዓት የህክምና ጤና መኮንን

ጃኑዋሪ 2, 2024


ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

አዲሱን ዓመት ስንጀምር ብዙዎቻችሁ ከጉዞ እና ከበርካታ ሰዎች ጋር ተገናኝታችሁ የምትመለሱ ስለሆነ፣ አንዳንድ የጤና አጠባበቅ ወቅታዊ መረጃዎች እና ምክሮችን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን። ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ምንም እንኳን የተሻለ ሁኔታ ላይ ብንገኝም ከከባድ ህመም ለመከላከል ተጨማሪ ወቅታዊ የጤና አዝማሚያዎችን ማወቅ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ለመማር እና ለማስተማር ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳል።

  1. የኮቪድ-19 እና የኢንፍሉዌንዛ (ፍሉ) መጠን መጨመር/ማሻቀብ ቀጥሏል፣ ይህም በከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ምክንያት ወደ ሆስፒታል መግባትን ጨምሯል።

    የቅርብ ጊዜው የኮቪድ-19 ሠብቫርያንት፣ JN.1፣ወረርሽኝ መጨመሩን በዜና ማሠራጫዎች ላይ የተነገረ ሲሆን የዚህም ምክንያት ከሌሎች የኦሚክሮን/Omicron subvariants ቫሪያንትስ የበለጠ መሠራጨቱን ያመለክታል። እስካሁን፣ የበለጠ የከፋ በሽታ እንደሚያመጣ የሚጠቁም ነገር ባይኖርም፣ የኮቪድ-19 ምርመራ፣ ህክምና እና ክትባቶች ለ JN.1 ይሰራሉ። ይሁን እንጂ ጉንፋን እና ሌሎች የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቁ ቫይረሶችም በህብረተሰቡ ውስጥ እየተሰራጩ በመሆናቸው አሁንም መጠንቀቅ በጣም አስፈላጊ ነው። በእኛ ስቴት ከኖቬምበር ወር ጀምሮ በኮቪድ-19 እና በጉንፋን በሽታ ምክንያት ወደ ሆስፒታሎች እና ሌሎች የህክምና ተቋማት፣ በተለይ ለአረጋውያን (65 ዓመት+)፣ እና ጨቅላ ህጻናት እና ትንንሽ ልጆች የድንገተኛ ክፍል ጉብኝት ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።

  2. የሜሪላንድ የጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት በመተንፈሻ አካላት ህመም ምክንያት የሚመጡ የሆስፒታል ታካሚዎችን ብዛት ከመጨመር ጋር በተያያዙ የጤና እንክብካቤ ሁኔታዎችን በተመለከተ አዲስ የጭምብል አጠቃቀም መመሪያ ሰጥቷል።

    ስለ ፊት መሸፈኛ/ጭምብል አጠቃቀም መመሪያ ከካውንቲ የጤና መምሪያ ለአጠቃላይ ህዝብም ሆነ ሌሎች ህዝብ የሚጠቀምባቸው ቦታዎች አልተለወጠም። አዲሱ የስቴት መመሪያ በጤና አጠባበቅ መመሪያ በስቴቱ የተቀናጀ የሆስፒታል ታካሚዎች ብዛት መጨመር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለብዙ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚተገበር ነው። በዶክተር ቢሮ ወይም በሆስፒታል ውስጥ ጭምብል እንዲጠቀሙ ሊጠየቁ ይችላሉ፣ እናም ጭምብሎችን መጠቀም በት/ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ የጤና ክፍል ሰራተኞችም በጥብቅ ይመከራል። በትምህርት ቤት ለሚገኙ ሰራተኞች እና ለተማሪዎች የሕክምና መከላከያ ጭምብሎች ይኖራሉ። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ድረ ገጻችንን ይመልከቱ። 

ጤናማ ልማዶች እና ወቅታዊ ክትባቶችን መውሰድ ጉንፋን እና ፍሉ ባለበት ወቅት፣ በተለይም ለከባድ በሽታ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች፣ ወይም ከማንኛውም ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ላላቸው ወሳኝ ናቸው ከፍተኛ የበሽታ አደጋ እንዳያጋጥማቸው ወሳኝነት አለው። ህመም ገና ሲጀምር መድሀኒቶች ውጤታማ ስለሚሆኑ ምልክቱ ሲጀምር ወዲያውኑ ምርመራ ማድረግ ከባድ በሽታን ለመቀነስ ይረዳል። ለኮቪድ-19 ከተጋለጡ ወይም መለስተኛ ምልክቶች ካለብዎት ከፍ ያለ ለበሽታ የመጋለጥ ስጋት ካለበት ከማንኛውም ሰው ጋር ጊዜ ከማሳለፍዎ በፊት ምርመራ ያድርጉ። ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 ፈጣን ምርመራ መሳሪያዎችን ለሰራተኞች እና ለተማሪዎች ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። 

MCPS ከካውንቲው የጤና ዲፓርትመንት እና ከሌሎች የማህበረሰብ አጋሮች ጋር የጤና ጥበቃ ሁኔታዎችን በተመለከተ በቅርበት መስራቱን ይቀጥላል። ኮቪድ-19 ከፍተኛ የህዝብ ጤና ስጋት አይደለም፣ ነገር ግን ከሌሎች የጤና ጉዳዮች ጋር ሊያያዝ ስለሚችል የጋራ ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል። ጤና ከመታመም በላይ ስለሆነ ጥሩ የጤንነት ሁኔታ ሲሰማን ለመማር፣ ለማስተማር እና ለመደጋገፍ እንችላለን። የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ ጤና የጋራ ሃላፊነት ነው። ለሰራተኞቻችን እና ለተማሪዎቻችን ጤና ለምታደርጉት ትብብር እና ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።

ከልብ

Patricia Kapunan, M.D., M.P.H.
MCPS Medical Officer

ተጨማሪ መረጃ ፦



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)