መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሃሙስ ጃንዋሪ 11፣2024

1. በቅርብ ቀን፡ MCPS የአውቶቡስ ክትትል የሚደረግበት መተግበሪያ (Bus Tracking App) በሥራ ላይ ያውላል።

MCPS በዚህ ሴሚስተር ለቤተሰቦች ለየራስ አገልግሎት የሚሰጥ የአውቶቡስ ክትትል ማድረግያ መተግበሪያ ሥራ ያስጀምራል። የመከታተያ አፕሊኬሽኑ ተጠቃሚዎች የትምህርት ቤት አውቶብስ የት እንዳለ ቀጥታ መረጃዎችን እንዲያገኙ፣ አስፈላጊ የሆነ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲኖር ለማስቻል እና ተማሪዎች አውቶቡስ ሲጠብቁ እና ሲሳፈሩ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚረዳ ነው።

የ MCPS የትራንስፖርት ዲፓርትመንት በአሁኑ ጊዜ ይህንኑ መተግበሪያ በሥራ ላይ ለማዋል በ 10 ት/ቤቶች ከሚገኙ ቤተሰቦች እና ተማሪዎች ጋር በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዲስትሪክቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር በምንዘጋጅበት ጊዜ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን።


2. ክረምት/ዊንተር 2024 የወላጅ አካዳሚ ቱ ጎ/Parent Academy TO GO አውደጥናቶች አሁን ይካሄዳሉ 

በዚህ ክረምት ቨርቹዋል የወላጅ አካዳሚ ክፍለ ጊዜዎችን በመጠቀም መረጃዎችን ለማግኘት እና የተማሪዎን ትምህርት በሚመለከት አቀንቃኝ በመሆን አጋር እንዲሆኑ እናበረታታለን። የወላጅ አካዳሚ/Parent Academy TO GO  ወርክሾፖች ቤተሰቦች የልጆቻቸውን አካዳሚያዊ እና ስሜታዊ ደህንነትን ለመደገፍ እንዲሁም ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁ እንዲሆኑ ለመርዳት ጠቃሚ መረጃዎችን እና ግብዓቶችን ይሰጣሉ። 

የዚህ ወር መጪዎቹ ክፍለ ጊዜዎች እና ርዕሶች፡

የጠዋት ውዥንብር እና የመኝታ ሠአት ትግልን መቋቋም

ጃኑዋሪ 17፣ ከሠዓት በኋላ 6-7 p.m.

ለህጻናት እና ለታዳጊዎች ኦንላይን የደህንነት ምክሮች

ጃኑዋሪ 24፣ ከሠዓት በኋላ 6-7 p.m.

ሙሉ መርሐግብሩን ለመመልከት እና ለመመዝገብ የወላጅ አካዳሚ ድረገጽ ይጎብኙ።



3. መጪ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች

  • ጃኑዋሪ 23 በኤዥያን አሜሪካዊያን ማህበረሰብ ውስጥ የአእምሮ ጤናን በሚመለከት የማጣራት እና የፓነል ውይይት ይካሄዳል 

ጃንዋሪ 23፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)፣ከሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተዳደር እና ከ "Asian American Health Initiative" ጋር በመተባበር “ የኤዥያን አሜሪካዊያን የአእምሮ "ፀጥ ያለ ጦርነት"በሚመለከት ፣ የፊልም ተዋናይ ከነበሩት ግለሰቦች የአንዱ(ዷ)ን አስተያየት እና የፓናል ውይይት ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ

  • ጃኑዋሪ 29 ሁለት ከትምህርት-ቤት ሰዓት ውጭ እንቅስቃሴዎች ይካሄዳሉ 

ትምህርት ቤት በማይኖርበት ጊዜ ተማሪዎ ማድረግ ያለበትን ነገር ማወቅ/ማግኘት ይፈልጋሉ? MCPS ሰኞ፣ ጃኑዋሪ 29 ቀን ከትምህርት-ቤት ሠዓት ውጭ በሚሆን ጊዜ ሁለት ዝግጅቶችን ያቀርባል። 

ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ሰኞ፣ ጃኑዋሪ 29 ቀን በሚካሄድ STEAM ትርኢት ላይ በነጻ እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል። 

መጓጓዣ, መክሰስ እና ሽልማቶች ይሰጣሉ። እስከ ጃንዋሪ 16 የመጨረሻ ቀነገደብ መመዝገብዎን ያረጋግጡ። 

MCPS፣ ከ NAACP የወላጆች ካውንስል እና ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ እንዲሁም Junior Day የኮሌጅ ዝግጅት ለጁንየር እና ለሲንየር ማይኖሪቲ ተማሪዎች ስለ ስኮላርሺፕ፣ የገንዘብ እርዳታ፣ ቃለመጠይቆች እና ሌሎችንም አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያውቁ መግለጫዎችን ይሰጣል/ያስተናግዳል። አውቶቡሶች፣ ቁርስ እና ምሳ ይኖራል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

ይመዝገቡ/Register. 

  • ይመልከቱ፦ የወላጅ ማህበረሰብ አስተባባሪዎች (PCCs) እርስዎን እንዴት እንደሚረዱዎት ይወቁ/ይመልከቱ


4. ስለ ESSER ፈንድ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ ስላለው ተጽእኖ የበለጠ ይወቁ

የአንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርጃ ፈንድ (ESSER) በወረርሽኙ ማገገሚያ ትምህርት ቤቶችን ለመደገፍ የተሰጠ የፌዴራል ድጎማ ገንዘብ ነው። እነዚህ የድጎማ ገንዘቦች አሁን እየተጠናቁቁ ሲሆን፣ ነገር ግን ሲደጉሟቸው የነበሩት አብዛኛዎቹ ፍላጎቶች አሁን ድረስ እንዳሉ ናቸው። ዲስትሪክቱ እንዴት እያተስተካከለ እንደሆነ ከ MCPS የፋይናንስ ቢሮ ያዳምጡ። 


5. የዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ  

ተማሪዎች ከዓመታዊው HBCU ትርኢት ከመደረጉ በፊት በስኮላርሺፕ ሚሊዮኖችን አግኝተዋል 

በዚህ አመት በቦታው ላይ ለሚደረጉ የመግቢያ እድሎችን ለማግኘት እስካሁን በተደረጉት ወደ 500 የሚጠጉ ቃለመጠይቆች ላይ ከ300 በላይ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። ተማሪዎች 460 ስኮላርሺፖችን አግኝተዋል፣ይህም በአጠቃላይ ወደ $3 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው።   

16ኛው አመታዊ ታሪካዊ የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች (HBCU) ትርኢት ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 16 ይካሄዳል።ለዚህ አመት ትርኢት ምን እንደሚዘጋጅ የበለጠ ለማወቅ"fair website" ድረገጽ ይጎብኙ። 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) የሚመለከቱ ዘገባዎች ላይ

16 estudiantes del condado Montgomery ganan becas universitarias

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች የጣምራ ምዝገባ እንዲመርጡ ተጨማሪ ተማሪዎችን ያበረታታሉ

በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ የስነጥበብ፣ የስነ ፅሁፍ፣ እና የቪዲዮ ውድድሮች ለተማሪዎች ክፍት ናቸው

ቴራፕቲስት አሁን ያይዎታል — ብቻ ይምጡ



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)