1. ከባድ የአየር ሁኔታ ሲከሰት ውሳኔዎች እንዴት እንደሚወሰኑ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዓርብ፣ጃንዋሪ 19 ከባድ የአየር ሁኔታን በተመለከተ በትምህርት ቤቶች ስራዎች ላይ ያለውን ተጽእኖ እየተከታተለ ነው። መጥፎ የአየር ሁኔታ ሲከሰት ውሳኔዎች እንዴት እንደሚደረጉ የበለጠ ለማወቅ እና ስለተለያዩ የኦፕሬሽን ቀለም ኮዶች ጋር ለመተዋወቅ ድረ ገጻችንን ይመልከቱ።
2. ስለ ምግባችን ሃሳብዎን ይግለጹልን!
የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) የእርስዎን አስተያየት መስማት ይፈልጋል! DFNS ስለ ትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝር ምን እንደሚፈልጉ ከሰራተኞች፣ ከተማሪዎች እና ከወላጆች የበለጠ አስተያየት መስማት ይፈልጋል። እባክዎ ይህን የዳሰሳ ጥናት ለመሙላት ጥቂት ደቂቃዎች ይውሰዱ እና የእርስዎን አስተያየት ይስጡን። የዳሰሳ ውጤቱ በቀጥታ የምግብ ዝርዝር ዝግጅት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
3. የአውቶቡስ መከታተያ መተግበሪያ "Bus Tracking App" በቅርቡ ሥራ ላይ ይውላል
ለግል አገልግሎት የሚጠቀሙበት የአውቶቡስ መከታተያ መተግበሪያ በሙከራ ምዕራፍ ላይ ስለሆነ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትራንስፖርት መምሪያ ጠቃሚ ግብአቶችን እና አስተያየቶችን ከተሳታፊ ቤተሰቦች እየሰበሰበ በዲስትሪክቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሲጀመር ያሳውቃል። መተግበሪያው የት/ቤት አውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚያገኙ ተማሪዎች በየጊዜው አውቶቡስ ማቆሚያ ቦታ እና የተመደቡ የአውቶቡስ መስመሮችን መረጃ ይሰጣል።
4. በቅርቡ የሚካሄዱ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች:
ምዝገባ ይከፈታል ዓርብ፣ ጃኑዋሪ 19 ለ 16ኛው አመታዊ HBCU አውደ ርዕይ ምዝገባ ይከፈታል። ይህ በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በአካል በመገኘት በነጻ የሚሣተፉበት ዝግጅት ከ 50 በላይ ታሪካዊ የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮችን እንዲያገኙ/እንዲያነጋግሩ እድል ይሰጣቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ.
ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 23፣ MCPS፣ ከእስያውያን አሜሪካውያን የጤና ጥበቃ ኢንሽቴቭ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተዳደር ጋር በመተባበር “ፀጥ ያለ ጦርነት፡ ስለ አእምሮ ጤንነት የኤዥያውያን አሜሪካዊያን እሳቤዎችን”በፊልሙ ውስጥ ካሉት ግለሰቦች የአንዱ(ዷ)ን አስተያየት እና የፓናል ውይይት ይከታተሉ። ይበልጥ ያንብቡ
ሰኞ፣ጃንዋሪ 29 ልጅዎ ከትምህርት ቤት ሲወጣ/ስትወጣ ማድረግ የሚፈልገውን/የምትፈልገውን የሆነ ነገር ማግኘት ይፈልጋሉ?
MCPS፣ ከ NAACP የወላጆች ካውንስል እና ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ስለ ስኮላርሺፕ፣ የገንዘብ ርዳታ፣ ቃለመጠይቆች እና ሌሎችንም ማወቅ ለሚፈልጉ ማይኖሪቲ ሲንየር ተማሪዎችጁኒየር ቀን/Junior Day የኮሌጅ መሠናዶ ያዘጋጃል። አውቶቡሶች፣ ቁርስ እና ምሳ ይኖራል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ. ይመዝገቡ/Register.
ቀኑን ይቆጥቡ፡ የልጃገረዶች ስብሰባ ቅዳሜ፣ማርች 9 በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይቀላቀሉን። ይህ ዝግጅት ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጃገረዶች በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያቀርባል። የኝኙነት መረብ የመዘርጋት ዕድል ለማግኘት ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ፥ አዝናኝ እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ፣ ጠቃሚ ክህሎቶችን ለመማር እና ለተለያየ የሰውነት ቅርጽ የተዘጋጁ "White House Black Market" የሚቀርበውን የፋሽን ትርኢት በመመልከት ይደሰታሉ።
5. የዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ
ይመልከቱ፡ ፍሬ ነገሩን፡ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት
ስለ ተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት፣ ተማሪዎች እንዴት እንደሚያገኙ እና ይህ ለምን የመመረቂያ መስፈርት እንደሆነ የበለጠ ለማወቅ "ወደ ፍሬ ነገሩ" የቅርብ ጊዜ ኩነት ይመልከቱ።
ሰባት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ብሄራዊ የልህቀት ትምህርት ቤት PTAሽልማት አግኝተዋል።
የትምህርት ቦርድ አባላት ሼብራ ኢቫንስ እና ብሬንዳ ቮልፍ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትን ብሔራዊ PTA የልህቀት ትምህርት ቤት ሽልማት ሥነ ሥርዓት ለማክበር ከሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኒት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል ናታሊ ፋኒ-ጎንዛሌዝ ጋር ተገኝተዋል። የኬኔዲ ት/ቤት ይህንን ሽልማት በቅርቡ ካገኙት ሰባት ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። ይበልጥ ያንብቡ.
ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የአገልግሎት ቀን፡ጃንዋሪ 15 በተካሄደው የሞንትጎመሪ ካውንቲ MLK የአገልግሎት ቀን በደርዘን የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ተሳትፈዋል። እለቱ የተጀመረው ማህበረሰቡን ለመጥቀም በተነደፉ በአካል-የአገልግሎት ፕሮጄክቶች ላይ በነጻ ለመሳተፍ በመሰባሰብ ነው።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org