መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 25, 2024

1. እርስዎን እና ተማሪዎን በሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ ያለዎትን ሀሳብ ይግለጹልን 

በማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (CEO) ፕሮግራም ላይ አስተያየትዎን ያጋሩን 

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት (MCPD) የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (CEO) ፕሮግራም ላይ ያለዎትን አስተያየት ለማጋራት ይህንን የአምስት ደቂቃ ዳሰሳ ይሙሉ። CEOs በቀጥታ ከትምህርት ቤቶቻችን ጋር አብረው ለመሥራት ከ MCPD የተመደቡ ቃለ መሐላ የፈፀሙ መኮንኖች ናቸው። ነባር ፕሮግራሞችን ለመገምገም እና ስርዓተ-አቀፍ ደህንነትን ለማሻሻል በምንሰራበት ጊዜ እርስዎ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ/ግብአት ለሱፐርኢንተንደንት እና ለትምህርት ቦርድ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን በመስጠት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። CEO የዳሰሳ ጥናት እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 9 ክፍት ይሆናል።

ከባድ የአየር ሁኔታ ግንኙነት እና የማካካሻ ቀናት 

በትምህርት ቤቶች ስራዎች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር በሚችል አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ዙሪያ ስለሚከናወን ግንኙነት እባክዎ የእርስዎን ግብረመልስ/አስተያየት ያቅርቡ። እንዲሁም MCPS በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የተጓደለ የትምህርት ማካካሻ ቀናትን እንዴት ማከናወን እንዳለበት የእርስዎን አማራጭ ሃሳብ መስማት እንፈልጋለን። 

ስለ ምግቦቻችን ሃሳብዎን ይግለጹልን

የምግብ እና የተመጣጠነ አመጋገብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) አሁንም በትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝሮች ላይ ተጨማሪ እንዲካተት የሚፈልጉትን ግብረ መልስ እየሰበሰበ ነው። እባክዎ ይህን የዳሰሳ ጥናት ለመሙላት ጥቂት ደቂቃዎች ይውሰዱ እና የእርስዎን አስተያየት ይስጡን። የዳሰሳ ውጤቱ በቀጥታ የምግብ ዝርዝር ዝግጅት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።


2. የተማሪዎች ዝውውር ማመልከቻ ወቅት ፌብሩዋሪ 1 ይጀመራል 

የ 2024-2025 የት/ቤት ምደባ ዝውውር (COSA) የቅያሬ ወቅት ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 1 ይከፈታል። COSA ሂደቱ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የአካባቢ ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ት/ቤት እንዲዛወሩ ጥያቄ ማቅረብ ያስችላቸዋል። ሁሉም COSA ጥያቄ የሚያቀርቡ ማመልከቻዎች ከማክሰኞ፣ ኤፕሪል 2 በፊት መቅረብ አለባቸው። ዝርዝሮቹን በሙሉ አንብቡ።


3. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች: 

በአመታዊው HBCU አውደ ርዕይ ላይ ለመገኘት ዛሬውኑ ይመዝገቡ

ምዝገባ፡16ኛው ዓመታዊ HBCU አውደ ርዕይ ላይ ለመገኘት ምዝገባ ክፍት ነው። ይህ በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በአካል በመገኘት በነጻ የሚሣተፉበት ዝግጅት ከ 50 በላይ ታሪካዊ የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮችን እንዲያገኙ/እንዲያነጋግሩ እድል ይሰጣቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ.

ሠመር ራይዝ 2024 የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል

ተማሪዎች የሠመር ራይዝ Summer RISE 2024 ምዝገባ አካል እንዲሆኑ ክፍት ነው። Summer RISE ለመጀመሪያ አመት እና ለመጨረሻ አመት ተማሪዎች ተግባራዊ፣ በሙያ ላይ የሚያተኩሩ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ ይኼውም አሰሪዎች ዝንባሌ ያላቸውን በመለየት በስልጠና እንዲያዳብሩ ይረዳል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.

MCPS ማርች 9 የሴቶችን ስብሰባ ስለሚያስተናግድ ቀኑን ይቆጥቡ።

ቅዳሜ፣ማርች 9 በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆች ስብሰባ ስለሚካሄድ ይቀላቀሉን። ይህ ዝግጅት 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ

ይመዝገቡ/RSVP


4. የሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ማክኒት በቅርቡ OIG ሪፖርት ላይ የሰጡት መግለጫ

ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ እንስፔክተር ጀነራል ጽ/ቤት/Montgomery County Office of the Inspector General (OIG) ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 25 ለወጣው ሪፖርት ምላሽ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል።

“የሞንትጎመሪ ካውንቲ ኢንስፔክተር ጄኔራል ሜጋን ዴቪ ሊማርዚ/Megan Davey Limarzi እና ቡድናቸው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆዩ እና ሥርዓት አቀፍ ጉዳዮችን በተመለከተ ላደረጉት ጥልቅ እና ጥብቅ ምርመራ/ግምገማ በጣም አመሰግናለሁ። መግለጫውን በሙሉ ያንብቡ። 


5. በዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ  

አስራ ሶስት ሲንየር ተማሪዎች QuestBridge ሙሉ የትምህርት ስኮላርሺፕ አሸንፈዋል

ከዘጠኝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ 13 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሲንየር ተማሪዎች ለአራት አመት ሙሉ የትምህርት እድል QuestBridge፣ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና ከፍተኛ የትምህርት ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ከ 50 በላይ ከፍተኛ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ከሚያገናኝ ብሔራዊ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ስኮላርሽፕ አግኝተዋል። 

ሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሜሪላንድ/ዲሲ የሪጅናል ሳይንስ ቦውል ሻምፒዮና አሸንፏል

የሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 2024 ብሔራዊ የሳይንስ ቦውል (NSB) ሪጅናል ውድድር አሸናፊ ስለሆነ በዚህ የስፕሪንግ ወቅት NSB ብሄራዊ የፍጻሜ ውድድር ላይ ይሳተፋል/ይወዳደራል። ይበልጥ ያንብቡ



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)