1. የኮርስ የመጨረሻ ፈተና ማሳሰቢያ፣ የውጤት አሠጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ ደንብ ማሻሻያ
ለማስታወስ ያህል፣ የሜሪላንድ አጠቃላይ ምዘና ፕሮግራም (MCAP) በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች (2027 ለሚያጠናቅቁ) የኮርስ ማብቂያ (EOC) የሳይንስ እና ስነመንግስት ትምህርት ፈተናዎች (NSL) ከዚህ የስፕሪንግ ወቅት ጀምሮ የመጨረሻው ውጤት 20% ሃያ በመቶ ይቆጠራል። ይህ የሆነው ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) በተሰጠው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ መስፈርቶች ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ነው። ሙሉውን ዝርዝር ያንብቡ
2. እርስዎን እና ተማሪዎን በሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ ያለዎትን ሀሳብ ይግለጹልን
በማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (CEO) ፕሮግራም ላይ አስተያየትዎን ያጋሩን
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት (MCPD) የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (CEO) ፕሮግራም ላይ ያለዎትን አስተያየት ለማጋራት ይህንን የአምስት ደቂቃ ዳሰሳ ይሙሉ።
ከባድ የአየር ሁኔታ ማስታወቂያ/ኮሙኒኬሽን እና የማካካሻ ቀናት
በትምህርት ቤቶች ስራዎች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር በሚችል አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ዙሪያ ስለሚከናወን ግንኙነት እባክዎ የእርስዎን ግብረመልስ/አስተያየት ያቅርቡ። MCPS በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሚስተጓጎሉ የትምህርት ቀናትን ማሟያ ቀናት አጠቃቀምን በሚመለክት እንዴት መካሄድ እንዳለበት የእርስዎን ምርጫዎች መስማት እንፈልጋለን።
ስለ ምግቦቻችን ሃሳብዎን ይግለጹልን
የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) በትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝሮች ላይ እንዲሻሻል የሚፈልጉትን አስተያየት እየሰበሰበ ነው። እባክዎ ይህን የዳሰሳ ጥናት ለመሙላት ጥቂት ደቂቃዎች ይውሰዱ። የዳሰሳ ውጤቱ በቀጥታ የምግብ ዝርዝር ዝግጅት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
3. የተማሪ ዝውውር ጥያቄ ማቅረቢያ ወቅት አሁን ክፍት ነው።
2024-2025 የት/ቤት ምደባ ለውጥ ለማድረግ (COSA) የዝውውር ወቅቱ አሁን ክፍት ነው። COSA የአሠራር ሂደቱ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። ሁሉም COSA ጥያቄ የሚያቀርቡ ማመልከቻዎች ከማክሰኞ፣ ኤፕሪል 2 በፊት መቅረብ አለባቸው። ዝርዝሮቹን በሙሉ አንብቡ።
4. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች
MCPS ማርች 9 የወጣት ሴቶችን ስብሰባ ያካሄዳል
ቅዳሜ፣ማርች 9 በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆች ስብሰባ ስለሚካሄድ ይቀላቀሉን። ይህ ዝግጅት 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ
ይመዝገቡ/RSVP
አክብሮትን መምረጥ/Choose Respect Video የቪዲዮ ውድድር አሁን ክፍት ነው!
ፈጠራዎን ለማሳየት እና የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ለማግኘት እድሉን ይፈልጋሉ? "አክብሮትን መምረጥ" የቪዲዮ ውድድር ክፍት ነው!
አመታዊ HBCU የኮሌጅ ትርኢት ላይ ለመገኘት ዛሬ ይመዝገቡ
ምዝገባ፡ ለ16ኛው ዓመታዊ HBCU የኮሌጅ ትርኢት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው። ይህ በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በአካል በመገኘት በነጻ የሚሣተፉበት ዝግጅት ከ 50 በላይ ታሪካዊ የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮችን እንዲያገኙ/እንዲያነጋግሩ እድል ይሰጣቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ.
ሠመር ራይዝ 2024 የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል
ምዝገባ፡ ተማሪዎች "Summer RISE 2024" አካል በመሆን እንዲሳተፉ ምዝገባው ተጀምሯል። Summer RISE ለመጀመሪያ አመት እና ለመጨረሻ አመት ተማሪዎች ተግባራዊ፣ በሙያ ላይ የሚያተኩሩ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ ይኼውም አሰሪዎች ዝንባሌ ያላቸውን በመለየት በስልጠና እንዲያዳብሩ ይረዳል። ምዝገባው ፌብሩዋሪ 27 ይዘጋል። የበለጠ ለመረዳት እዚህ ያንብቡ።
5. በዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ
ይመልከቱ፦ የስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በበርንት ሚልስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Coding በማስተማር ተማሪዎችን ረድተዋል
የማይክሮቢትስ ማስተርስ ፕሮግራም/Microbits Masters Program የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪዎች ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ እንዲያስተምሩ ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያመጣቸዋል።
አምስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሚዲያ ስፔሻሊስቶች ለሜሪላንድ የዓመቱ ምርጥ የቤተመጻሕፍት ባለሙያነት ተመርጠዋል
አምስት MCPS የሚዲያ ስፔሻሊስቶች 2024 የሜሪላንድ ት/ቤቶች የዓመቱ የቤተ መፃህፍት ሽልማት እጩዎች ናቸው፣ ይህም የት/ቤት የቤተ-መጻህፍት ባለሙያዎች ምሣሌያዊ አገልግሎት እና በት/ቤት ቤተመፃህፍት ሚዲያ መስክ የላቀ ስኬቶችን ያጎናጽፋል። ይበልጥ ያንብቡ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ለዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የወጣቶች ፕሮግራም ተመርጣለች
የሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪ አንጀሊና ሹ/Angelina Xu በማርች ወር በዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የወጣቶች ፕሮግራም ላይ በዋሽንግተን ሳምንት ሜሪላንድን ትወክላለች። በአሁኑ ጊዜ የሜሪላንድ የተማሪዎች ካውንስል ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን የምታገለግለው Xu፣ 104 ተማሪዎች ለሚወከሉበት የሴኔት ወጣቶች ፕሮግራም ከስቴቱ ከፍተኛ የተማሪ መሪዎች መካከል ተመርጣለች።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ጊዜ ውጪ በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፋሉ
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው የጁኒየር ቀን በደርዘን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከ10 በላይ የኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮችን አግኝተዋል/አነጋግረዋል። ዝግጅቱ ዝቅተኛ ውክልና ያላቸው የአናሳ ማህበረሰብ ሲንየር ተማሪዎች ክፍት ነበር። የእረፍት ክፍለ ጊዜዎች ኮሌጆችን ለማሰስ፣ የኮሌጅ ጉብኝት ለማድረግ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ስኮላርሺፕ ለማፈላለግ እና ከሲንየር አመት በፊት ውጤታማ የሆነ የሠመር ወቅት ውይይቶችን ማድረግ አካተዋል።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org