መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ፌብርዋሪ 15/2024

1. ሁሉም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ግብረመልስ/አስተያየት እንዲሰጡ ተጋብዘዋል

እንዴት እየሠራን እንደሆነ ከእናንተ መስማት እንፈልጋለን። MCPS ሁሉንም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች/ተንከባካቢዎች በአካዳሚክስ፣ በኮሙኒኬሽን/ግንኙነት እና ስለ ትምህርት ቤትዎ፣ ስለ ዲስትሪክቱ እና/ወይም MCPS የሥራ እንቅስቃሴ ልምድ ጋር ያላችሁን አጠቃላይ እርካታ እንዲያካፍሉን እየጋበዝን ነው። በደንብ እየሰራን ያሉትን ሥራዎችን እና ማሻሻል የሚገባንን ሁኔታዎች እንድንረዳ የእናንተ ግብአት እና ግንዛቤ ማግኘት አስፈላጊ ነው። የእርስዎ ተሳትፎ እና ማንኛውም የተለየ መረጃ ሙሉ በሙሉ በሚስጥር የሚያዝ ነው። የተሰበሰበው ግብረመልስ ውሳኔዎችን ለመስጠት እና በዲስትሪክታችን ውስጥ ላሉ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች የበለጠ አጋዥ እና ምቹ የትምህርት አካባቢ ለመፍጠር ይጠቅማል።

ስለ ዳሰሳ ጥናቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ። 

የዳሰሳ ጥናቱ እስከ ማርች 15 ድረስ ክፍት ይሆናል።

2. የትምህርት ቦርድ ሶስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፕሮግራሞችን ማሻሻያ ለማድረግ ወይም ለማስወገድ በቅድሚያ የማህበረሰብ አስተያየቶችን ለመስማት ፌብሩዋሪ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ውይይት ይካሄዳል።

የትምህርት ቦርድ MCPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች ፍላጎት ላይ ያተኮረ በኃላፊነት ስሜት የሚመራ እና ውጤታማ የስራ ማስኬጃ በጀት ለ 2025 የባጀት አመት ለማዘጋጀት በንቃት እየሰራ ነው። 

የስራው አካል በመሆኑ እና የማህበረሰብ አስተያየቶችን በስፋት ካዳመጠ በኋላ ቦርዱ የበጀት አመት FY25 ላይ ሶስት ፕሮግራሞችን ማሻሻያ ለማድረግ ወይም ለማስወገድ እያሰበ ነው።MCPS ቨርቹዋል አካዳሚ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ESSER ባጀት ተመድቦለት MCPS ኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤቶች ተነሳሽነት በአርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በሮስኮ R. ኒክስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተራዘመ የአካዳሚክ ካለንደርን እና MCPS ውስጥ ባሉ ጥቂት ትምህርት ቤቶች የሚካሄደውን በእኔ ውስጥ ያለው መሪ ፕሮግራም/The Leader in Me Programያካትታል። ይበልጥ ያንብቡ 

3. MCPS የአመቱ ምርጥ አስተማሪ ተወዳዳሪነት አራት የመጨረሻ እጩዎች ተመርጠዋል።

ለ 2024–2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህር አራት መምህራን የመጨረሻ እጩዎች ሆነው ተሰይመዋል። እነርሱም፡ Janie Earle፣ በፑልስቪል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመዋዕለ ሕፃናት መምህርት፣ ካሪ ክራይናክ፣በፍሎው ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ልማት መምህርት፣ ሞርጋን ፓቴል፣በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ መምህርት፣ እና ሜሊሳ ፖርተር ፓርክስ፣ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማዳበር መምህርት ናቸው።

ስለ መጨረሻ ዙር እጩዎች በተጨማሪ ያንብቡ

4. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና ሪሶርሶች 

MCPS ማርች 9 የልጃገረዶችን ጉባኤ ያስተናግዳል

ቅዳሜ፣ማርች 9 በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆች ስብሰባ ስለሚካሄድ ይቀላቀሉን። ይህ ዝግጅት 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ ይመዝገቡ/RSVP

የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን በሚመለከት የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም ፌብሩዋሪ 24 ይካሄዳል 

ጠንካራ የአእምሮ ጤናን ስለመጠበቅ እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን ለመከላከል የቤተሰብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 24 በስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለሚካሄድ PTSA ይቀላቀሉ። ተሳታፊዎች ስለ fentanyl፣ አልኮል፣ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች አደገኛነት ይማራሉ። የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ መረጃ፣ ትምህርት ቤት እና ማህበረሰብን መሰረት ባደረገ የዕፅ ሱሰኝነት መከላከል፣ የጉዳት ቅነሳ ህክምና ውጥኖችን ለመከወን ምን የመድን ሽፋን እንደሚያስፈልግ ውይይት ያደርጋሉ። ይመዝገቡ/RSVP

ሠመር ራይዝ 2024 የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል

ምዝገባ፦ ተማሪዎች ሠመር ራይዝ/"Summer RISE 2024" አካል በመሆን እንዲሳተፉ ምዝገባው ተጀምሯል። ሠመር ራይዝ/Summer RISE ለመጀመሪያ አመት እና ለመጨረሻ አመት ተማሪዎች ተግባራዊ፣ በሙያ ላይ የሚያተኩሩ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ ይኼውም አሰሪዎች ዝንባሌ ያላቸውን በመለየት በስልጠና እንዲያዳብሩ ይረዳል። ምዝገባው ፌብሩዋሪ 27 ይዘጋል። የበለጠ ለመረዳት እዚህ ያንብቡ

MCPS ከተፅዕኖ ፈጣሪ ልጃገረዶች ጋር በአጋርነት ይሠራል

MCPS ከ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ልጃገረዶች እና ሥርዓተ-ፆታ የሚያስፋፉ ወጣቶች ነፃ የንግድ እና የአመራር ክህሎት መርሃ ግብር ለመስጠት "Girls With Impact" ቡድን ጋር በመተባበር እየሠራ ነው። ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ መሪዎች ጋር የተገነባው ይህ 10-ሳምንት የኦንላይን ፕሮግራም ማርች 11 የሚጀምር ሲሆን ልጃገረዶች ስራ ፈጣሪዎች፣ የፈጠራ ችሎታ እንዲኖራቸው እና መሪዎች እንዲሆኑ ክህሎትን፣ እውቀትን እና በራስ መተማመንን ያስታጥቃቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ 

5. በዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ  

በቀጥታ ወደ ቁምነገሩ፡- የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በተግባር ስራ ላይ ያተኮረ የትምህርት ፕሮግራም

MCPS ተማሪዎች የሙያ ክህሎትን፣ በራስ መተማመንን እና ገንዘብ የሚያገኙበትን እውቀት እና ልምምድ የሚያካትት በተግባር ስራ ላይ የተመሰረተ የመማር እድሎችን ይሰጣል። መርሃግብሩ የብዙዎቹ የሙያ ቴክኒክ ትምህርት (CTE) MCPS ከሚቀርቡ ፕሮግራሞች ከዲስትሪክት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች እና ስለሜሪላንድ የወደፊት ዕጣ ብሉፕሪንት  አካል ነው።

ከ10 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪ ዳንሰኞች ፌብሩዋሪ 12 በተካሄደው ዓመታዊ የዳንስ ትርኢት በመሳተፍ ውዝዋዜና ዳንስ ትርኢታቸውን አሳይተዋል።እነርሱም ከሚከተሉት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ናቸው፦ ኤ.ማሪዮ ሎይደርማን፣ ኪንግስቪው እና ኋይት ኦክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና አልበርት አንስታይን፣ ቤተስዳ-ቼቪ ቼዝ፣ ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ ኖርዝውድ፣ ሮክቪል እና ከዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ዳንሰኞች ናቸው። የቀረበው ከካውንቲ አቀፍ የተሰባሰበ የዳንስ ትርኢት ነበር። የፎተግራፎችን ክምችት ይመልከቱ

ስለ MCPS የቀረበ ዘገባ፡ MCPS በመጪው አርብ ለሚካሄደው 16ኛው ዓመታዊ HBCU ትርኢት በዝግጅት ላይ ነው። 

FOX 5 DC segment ይመልከቱ



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)