1. የተማሪዎች የዝውውር ማመልከቻ የሚቀርብበት ጊዜ እስከ ኤፕሪል 2 ድረስ ክፍት ነው።
2024-2025 የት/ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) የዝውውር ጥያቄ ማቅረቢያ ወቅት ተጀምሯል። COSA የአሠራር ሂደቱ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። ሁሉም COSA የዝውውር ጥያቄ ማመልከቻዎች እስከ ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 2 ድረስ መቅረብ አለባቸው። ዝርዝሮቹን በሙሉ አንብቡ።
2. ስለ የመተንፈሻ አካል ቫይረስ ወቅታዊ የ CDC መመሪያ
የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) ማርች 1 የኮቪድ-19 መመሪያ ላይ ጉልህ ለውጦች አድርጓል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎች እና የሰራተኞችን ጤና አጠባበቅን በሚመለከት ከተሻሻለው የኮቪድ-19 መመሪያ ጋር ለማሣለጥ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ጋር እየሰራ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት ተጨማሪ መረጃ ይገለጻል። የሜሪላንድ የጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት ተጨማሪ ምክሮችን ሲያወጣ ተጨማሪ ማስተካከያዎች ሊደረጉ ይችላሉ።
3. ስለ ትምህርት ቤትዎ እና/ወይም ስለ MCPS ያላችሁን ተሞክሮ እና አስተያየት እስከ ማርች 15 ድረስ አካፍሉን።
እንዴት እየሠራን እንደሆነ ከእናንተ መስማት እንፈልጋለን። MCPS ሁሉንም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች/ተንከባካቢዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በመሥራት ያላቸውን ልምድ እና አስተያየታቸውን ስለ አካዳሚክስ፣ ግንኙነት፣ እና አጠቃላይ እርካታ እንዲያካፍሉ ተጋብዘዋል። በደንብ እየተሠራ ያለውን እና መሻሻል ያለበትን እንድንረዳ እርስዎ የሚሰጡን አስተያየት ግብአት እና ግንዛቤ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። የእርስዎ ተሳትፎ እና ማንኛውም የሚያጋሩት የተለየ መረጃ እና ማንነት በሚስጥር የሚጠበቅ ነው። የሚሰበሰበው ግብረመልስ መተግበር ያለባቸውን ውሳኔዎች ለማሳወቅ እና በዲስትሪክታችን ለሚገኙ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ቤተሰቦች የበለጠ አጋዥ እና ትምህርትን የሚያበለጽግ አካባቢ ለመፍጠር ይጠቅማል።
ስለ ዳሰሳ ጥናቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ። የዳሰሳ ጥናቱ አርብ፣ ማርች 15 ይዘጋል።
4. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች
ለትምህርት ቦርድ (BOE) የህዝባዊ ትምህርት አገልግሎት ሽልማቶች እጩዎችን እስከ ዓርብ፣ማርች 8 ድረስ መጠቆም ያስፈልጋል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 27ኛው የህዝባዊ ትምህርት የላቀ አገልግሎት አመታዊ ሽልማቶች ጥቆማዎችን መቀበል ይፈልጋል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ህዝባዊ ትምህርት ላይ አርአያነት ያለው አስተዋጾ ላደረጉ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች እውቅና ለመስጠት እና አድናቆት ለማሳየት ሽልማቶቹ በቦርዱ የተደገፉ ናቸው። ይበልጥ ያንብቡ
የተማሪዎች የስራ ቀን ኤፕሪል 10 ይካሄዳል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) “Grow Your Own Career” ቀን በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ9 a.m.–noon እሮብ፣ ኤፕሪል 10 ተማሪዎች ት/ቤት በማይገኙበት ቀን ያስተናግዳል። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ስለሚገኙ የስራ እድሎች እና ሙያዎች እንዲያውቁ እና በቦታው በሚደረጉ ቃለ-መጠይቆች ላይ በመሳተፍ እንዲጠቀሙ ተጋብዘዋል። እባክዎ RSVPእስከ ኤፕሪል 1 ይመዝገቡ።
በዓመቱ ውስጥ ስለሚኖሩት እድሎች የበለጠ ለማወቅ Out-School-Time website/ከትምህርት ቤት ውጪ-ክፍለጊዜ ድረ ገጽ ይጎብኙ።
በቀጣዩ Pregúntale MCPS በማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር ፕሮግራም ላይ
ቀጣዩን MCPS በማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር ፕሮግራም እሮብ፣ ማርች 13 ከቀኑ 6፡30 p.m. ላይ “Pregúntale a MCPS” on the Community Engagement Officer program የተሰኘ ፕሮግራም ማዳመጥዎን እርግጠኛ ይሁኑ። ይህ የውይይት ክፍለ ጊዜ በስፓንሽኛ MCPS en Español Facebook ገጽ ላይ በቀጥታ ይተላለፋል። ኦፊሰሮች ትምህርት ቤቶችን እንዴት እንደሚረዱ ለማወቅ እና ስለ ፕሮግራሙ ያለዎትን ማንኛውንም ጥያቄ ለማቅረብ ፕሮግራሙን ይከታተሉ።
2024 ሠመር ራይዝ በመቀበል ተማሪዎች የስራ ልምድ እንዲያገኙ ይርዱ/ይተባበሩ
ከ 2024-2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስኬታማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር እና ሲንየር ተማሪዎች ጋር የስራ ልምድዎን ለማካፈል ይፈልጋሉ? ለ 2024 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም እንዴት ተቀባይ/አስተናጋጅ መሆን እንደሚችሉ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ! የፓርትነርሺፕ ዲፓርትመንት ተማሪዎች በአካል፣ በቨርቹዋል ወይም በሁለቱ ጥምር ልምድ እንዲያገኙ ቢያንስ ለ50 ሰዓታት ተቀብለው የሚያስተናግዱ የንግድ ድርጅቶችን፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ይፈልጋል። ይበልጥ ያንብቡ.
5. MCPS ዘገባዎች
ሁለት MCPS የሚዲያ ስፔሻሊስቶች ለስቴት ሽልማት የመጨረሻ እጩ ሆነው ተሰይመዋል
ሊሳ ሃክ ከሲልቨር ስፕሪንግ ኢንተርናሽናል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና ሜሊሳ ኪንግ ከፍላወር ሂል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት 2024 የሜሪላንድ ት/ቤቶች የዓመቱ የላይብረሪያን ሽልማት የመጨረሻ እጩዎች ናቸው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
ብሔራዊ የትምህርት ቤት ቁርስ ሳምንትን ማክበር
መልካም ብሔራዊ የትምህርት ቤት ቁርስ ሳምንት! በዚህ ሳምንት፣ በየእለቱ እንዲማሩ የሚደግፋቸው በመሆኑ በመላው MCPS ለተማሪዎች የሚቀርበውን የአልሚ ምግብ ቁርስ ሣምንት እናከብራለን። የምግብ እና የተመጣጠነ አመጋገብ አገልግሎት ክፍል ከካኖን ሮድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በዚህ ሳምንት የቁርስ ቅምሻ አዘጋጅቷል። ከ100 በላይ ተማሪዎች የቁርስ ሳንድዊች እና የብሉቤሪ-ሮማን ባርን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቁርስ ምግቦችን እንዲቀምሱ ተጋብዘዋል። ይበልጥ ያንብቡ
የመጀመሪያው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወጣቶች የፀረ-ዘረኛነት ፊልም ፌስቲቫል ሶስት ምርጥ አሸናፊዎች
የመጀመሪያው የወጣቶች የፀረ-ዘረኝነት ፊልም ፌስቲቫል የተከናወነው በአስደናቂ ስኬት ነበር። ይህ በማይኖሪቲ ምሁራን ፕሮግራም የተስተናገደው ዝግጅት የተከናወነው ፌብሩዋሪ 24 ቀን AFI ሲልቨር ቲያትር እና የባህል ማዕከል ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለዘረኝነት ምንም ቦታ እንደማይኖረው የሚገልጹ ኃይለኛ መልዕክቶችን የያዙ ዶክመንተሪዎችን አቅርበዋል። ይበልጥ ያንብቡ
ስለ MCPS የተላለፉ ዘገባዎች:
ጆን ኤፍ ኬኔዲ አለም በአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ወርቅ አሸንፏል
ከ My MC ሚዲያ ይበልጥ ያንብቡ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች Moco360's በሞንትጎመሪ ካውንቲ 10 የሚደነቁ ታዳጊ ወጣቶች በመባል ቀርበዋል።
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org