1. የትምህርት ቦርድ (BOE) ቀጣይ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ እያካሄደ ነው።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጁላይ 1, 2024 ኃላፊነት የሚረከብ/የምትረከብ ቀጣዩን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ ጀምሯል። ቦርዱ የትምህርት ስርአቱን ለመምራት እና ተማሪዎችን በኮሌጅ፣በስራ እና በማህበረሰብ ውስጥ ስኬታማ እንዲሆኑ ለማዘጋጀት ባለው ቁርጠኝነት፣እጩዎቹን ለመመልመል እና ለማጣራት የሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ ድርጅት ይቀጥራል። ቦርዱ የምልመላ ድርጅቱን ሲመርጥ፣ ከአዲሱ ሱፐር ኢንተንደንት ስለሚጠበቁ በጣም አስፈላጊ ባህሪያትና ችሎታ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ማካሄድ ይጀምራል።
ቦርዱ በከተማ አዳራሾች በአካል ተገኝተው የሚካሄዱ ሶስት የማህበረሰብ ውይይቶችን ኤፕሪል የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ያስተናግዳል፦
ኤፕሪል 2–ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 6 ፒ.ኤም
ኤፕሪል 3–ሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 6 ፒ.ኤም
ኤፕሪል 4–ዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 6 ፒ.ኤም
ቨርቹዋል መድረክም እየታቀደ ነው። ቀን እና ሰዓት ገና አልተወሰነም።
የቦርድ ፕሬዘዳንት ካርላ ሲልቬስትር ያስተላለፉትን መልዕክት ይመልከቱ።
2. የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ሰኞ፣ ማርች 18 ይጀመራል
ለ 2024-2025 የትምህርት አመት የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ሰኞ፣ማርች 18 ይጀመራል። ሴፕቴምበር 1, 2024 ላይ አምስት አመት እድሜ የሚሞላቸው ልጆች ብቁ ናቸው። ከማህበረሰቡ በተገኘው ግብረመልስ መሰረት፣ በዚህ አመት የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት አቅጣጫዎችን ማስተዋወቂያ ፕሮግራሞች አይሰረዙም። ትምህርት ቤቶች መጪዎቹን የመዋለ ህፃናት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ለመቀበል ተገቢ አማራጮችን ይወስናሉ።
ምዝገባው ParentVUE ፖርታል ላይ በኦንላይን ይካሄዳል። ቤተሰብዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ከሆኑ፣ እዚህ PreentVue አካውንት መፍጠር ያስፈልግዎታል። ስለ ብቁነት እና የምዝገባ ሂደት የበለጠ መረጃ ለማግኘት MCPS የመዋለ ህፃናት ምዝገባ ድረ-ገጽ ይጎብኙ ወይም የአካባቢዎን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያነጋግሩ።
3. ከማርች 18 ጀምሮ በማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር ፕሮግራም የቨርቹዋል የውይይት ክፍለ ጊዜን ይቀላቀሉ
MCPS ስርዓተ-አቀፍ ደህንነት እና የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ቢሮ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (ዋና ስራ አስፈፃሚ) 2.0 ፕሮግራም ላይ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማህበረሰቦችን ቨርቹዋል የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጋብዛል። CEOs ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ከትምህርት ቤቶች ጋር በቀጥታ የሚሰሩ ቃለመሐላ የፈፀሙ መኮንኖች ናቸው። ይህ ክፍለ ጊዜ ስለ ፕሮግራሙ ለመማር/ለማወቅ፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ እና ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ እድል ይሰጣል። ስብሰባዎቹ የሚከናወኑት ማርች 18፣19፣ እና 20 ከቀኑ 6–7 ፒ.ኤም በዙም ነው። ለእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክላስተር በተመደቡት ቀናት በራሪ ወረቀቱን ለመመልከት እና ለክፍለ-ጊዜው እዚህ ለመመዝገብ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
4. የጥላቻ አድልኦን በተመለከተ ለማስተማር፣ ለመከላከል፣ እና ለመፍታት የዲስትሪክት አቀፍ አቀራረብ ማሻሻያ
ጥላቻ የተሞላበት አድሎአዊ ድርጊቶችን ለመዋጋት በዲስትሪክቱ መሠረት ላይ ለመገንባት MCPS ከውስጥ እና ከውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር በዲስትሪክት አቀፍ ደረጃ የጥላቻ ብያስን ለማስተማር፣ ለመከላከል፣ እና ለመፍታት የተግባር ቡድን ጋር ስብሰባ አካሂዷል። ይህ ማዕቀፍ እና የቡድኑ ስራ ማክሰኞ፣ ማርች 19 ለትምህርት ቦርድ ይቀርባል። አጭር መግለጫ የሚሰጥ የቪዲዮ መልእክት ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
5. ድምጽዎ እንዲሰማ የማድረግ እድል፡ ዲስትሪክት አቀፍ የዳሰሳ ጥናት የመጨረሻ ቀን ተራዝሟል
MCPS ሁሉንም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች/ተንከባካቢዎች በአካዳሚክ፣ በተግባቦት እና በአጠቃላይ ማመቻቸት አንጻር በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክቱ ውስጥ እና/ወይም በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የመስራት ልምድ እንዲያካፍሉ ይጋብዛል።
የዳሰሳ ጥናት የማጠናቀቂያ ቀነ-ገደብ እስከ አርብ፣ ማርች 22 ድረስ ተራዝሟል።
ለተጨማሪ መረጃ እና የዳሰሳ ጥናቱን ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የዳሰሳ ጥናቶቹን ለመሙላት በትምህርት ቀን ጊዜ ያገኛሉ።
6. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች
ማሳሰቢያ፡ ለመጪው ብሄራዊ የኮሌጅ ትርኢት ይመዝገቡ
2024 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ብሔራዊ የኮሌጅ መግቢያ ካውንስሊንግ (NACAC) ብሔራዊ የኮሌጅ ምዝገባ ትርኢት ማክሰኞ፣ እና ረቡዕ፣ ማርች 19 እና 20 Maryland SoccerPlex እና Adventist Healthcare Fieldhouse፣ Germantown, ከጠዋት 9:45 a.m.–እስከ 1 p.m. ለ 11ኛ ከፍል ተማሪዎች ይካሄዳል። አውደ ርዕዩ ማክሰኞ፣ ከ 6፡30–8፡30 ፒ.ኤም ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ክፍት ነው። ለበለጠ መረጃ እና ለመመዝገብ እዚህ ጠቅ ያድርጉ። ይበልጥ ያንብቡ
የተማሪዎች የስራ ቀን ኤፕሪል 10 ይካሄዳል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) “Grow Your Own Career” ቀን በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ9 a.m.–noon እሮብ፣ ኤፕሪል 10 ተማሪዎች ት/ቤት በማይገኙበት ቀን ያስተናግዳል። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ስለሚገኙ የስራ እድሎች እና ሙያዎች እንዲያውቁ እና በቦታው በሚደረጉ ቃለ-መጠይቆች ላይ በመሳተፍ እንዲጠቀሙ ተጋብዘዋል። እባክዎን ይመዝገቡ/RSVP እስከ ኤፕሪል 1።
በዓመቱ ውስጥ ስለሚሰጡ እድሎች የበለጠ ለማወቅ ከትምህርት-ጊዜ-ውጭ ክንዋኔ ድረገጽ ይጎብኙ።
ኤፕሪል 10 ወደ ቀጣዩ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ይምጡ
የመካከለኛ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትኩረት መስጠት አለባቸው! MCPS 3ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 13 ከጠዋቱ 8፡30 a.m.–3፡35 p.m. በቲልደን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስተናግዳል። ይበልጥ ያንብቡ
ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ ኤፕሪል 20 ይካሄዳል፤ የፅሁፍ ውድድር ማቅረቢያ ቀን ኤፕሪል 10ነው።
ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ለሁሉም የወጣት ወንድ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች የተደረገ ጥሪ! ተማሪዎን ለስፕሪንግ 2024 ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ በማስመዝገብና በማበረታታት የስኬት መንገዳቸውን ያቀጣጠሉ። ኮንፈረንሱ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 20 በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ከቀኑ 8 a.m–2 p.m. የሚካሄድ ሲሆን MCPS ከአካባቢዎ መጓጓዣ ሊያቀርብ ይችላል። ምዝገባው ረቡዕ፣ ኤፕሪል 3 ያበቃል። ያለው ቦታ ውስን ነው።
7. ስለ MCPS ዘገባዎች
ለአመቱ ምርጥ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ ሽልማት ሶስት የመጨረሻ እጩዎች ተመርጠዋል
ለ 2024 የድጋፍ አገልግሎት የአመቱ ምርጥ ሰራተኛ፤ ሶስት የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኞች የመጨረሻ እጩ ሆነዋል። የዚህ አመት አመታዊ ሽልማቶች ቻውላ ቡተርወርዝ (Chaula Butterworth) በፋርምላንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፓራኢዱካተር፣ ሮቢን ማኩ (Robin McCue)፣ የአትሌቲክስ ዲፓርትመንት ጸሐፊ III፣ እና ብሩኖ ስሚዝ ( Bruno Smith)፣ ሚል ክሪክ ታወን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ አገልግሎት አስተዳዳሪ III ።
የልጃገረዶች ስብሰባ
በሁለተኛው የልጃገረዶች ጉባኤ ከ1,000 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ከስድስተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያሉ ልጃገረዶች እና ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው በአእምሮ ጤና፣ የአካል ደህንነት፣ ጤናማ አመጋገብ፣ በራስ መተማመን፣ መዝናናት፣ የፈጠራ ጥበብ ቴራፒ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በተደረጉ አውደ ጥናቶች ላይ ተሳትፈዋል።
ቤተሰቦች STEM/Math Night የሒሳብ ምሽት ብሩክሄቨን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይሳተፋሉ
ባለፈው ሳምንት በብሩክሄቨን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት STEM እና Math Night ከ 350 በላይ ተማሪዎች እና ወላጆች ተገኝተዋል። ቤተሰቦች በእንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፈዋል፣በስብሰባው ወቅት ከቬንደሮች ጋር በመነጋገር ጠቃሚ መረጃዎችን አግኝተዋል።
MCPS እና MoCo EmpowHER ለመሪዎች ምሳ ያስተናግዳል
የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለማክበር MCPS የተማሪዎች አመራር እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ተግባራት እና MoCo EmpowHER የመጀመሪያውን EmpowHER መሪዎች ምሳ አዘጋጅተዋል። ይበልጥ ያንብቡ
ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የታሪክ ቀን ውድድር ላይ አንፀባራቂ ሆነዋል
ባለፈው ሳምንት በሞንትጎመሪ ካውንቲ የታሪክ ቀን ውድድር A. Mario Loiederman መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከ 35 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መካከለኛ ደረጃ እና ከአምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ 350 በላይ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። ይበልጥ ያንብቡ
የታኮማ ፓርክ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2024 ለልጆች በጣም ጥሩ የምግብ ዝግጅት በማድረግ በአንደኛነት አሸንፏል። ታኮማ ፓርክ በዚህ አመት ብቸኛው ተወዳዳሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት ሲሆን ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በአንደኛነት ደረጃ ሲያሸንፍ ለአምስተኛ ጊዜ ነበር።
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org