መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ማርች 21/2024

1. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት ምዝገባ አርብ፣ ማርች 22 ይከፈታል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት ምዝገባ አርብ፣ ማርች 22 ይጀመራል። ሪጅናል የሠመር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች በሞንትጎመሪ ብሌየር፣ ሴኔካ ቫሊ እና ሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአካል ይሰጣሉ። ትምህርቱ ጠዋት 8፡00 a.m. ይጀመራል እና 12፡30 p.m. ያበቃል። MCPS በተወሰኑ ማእከላዊ ፌርማታዎች መጓጓዣ ያቀርባል እና ምግብም ይሰጣል። ዝርዝሮቹን በሙሉ አንብቡ።


2. የተማሪዎች ዝውውር ማመልከቻ የሚቀርብበት ጊዜ ኤፕሪል 2 ይዘጋል

የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) ሂደት ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የአካባቢ ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል። COSA ጥያቄዎች በሙሉ ከማክሰኞ፣ ኤፕሪል 2 በፊት መቅረብ አለባቸው። ከኤፕሪል 2 በኋላ የሚቀርቡ COSA ጥያቄዎች ተቀባይነት የሚኖራቸው ተማሪው(ዋ) የሞንትጎመሪ ካውንቲ አዲስ ነዋሪ ከሆነ(ች) ወይም ከኤፕሪል 2 በፊት አስቀድሞ ሊታወቅ የማይችል ድንገተኛ ክስተት ካጋጠመ ብቻ ነው። ጥያቄ ለማቅረብ ሁለት የተለያዩ መንገዶችን ጨምሮ ስለ COSA ሂደት መረጃ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል። 

ጥያቄዎችን ለማቅረብ የተማሪ ፐርሶኔል እና የትምህርት ክትትል አገልግሎት ክፍል 240-740-5620 ይደውሉ። 

ይበልጥ ያንብቡ 


የእርስዎን አስተያየት ለማጋራት በመጪው የሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ መድረክ ላይ ይሳተፉ 

የትምህርት ቦርድ ቀጣዩን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ለማፈላለግ እና ለመምረጥ የእርስዎ ጠቃሚ አስተያየት ግብአት ያስፈልጋል። ቦርዱ በከተማ አዳራሾች በአካል ተገኝተው የሚካሄዱ ሶስት የማህበረሰብ ውይይቶችን ኤፕሪል የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ያስተናግዳል፦

  • ኤፕሪል 2–ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 6 ፒ.ኤም
  • ኤፕሪል 3–ሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 6 ፒ.ኤም
  • ኤፕሪል 4–ዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 6 ፒ.ኤም

መድረኮቹ ከአዲሱ ሱፐርኢንተንደንት በጣም አስፈላጊ ናቸው ብለው ባመኑዋቸው ባህሪያት እና ብቃት በሚመለከት በሚቀርቡ አስተያየቶች ላይ ቅድሚያ ትኩረት ይሰጣሉ   ተማሪዎችን፣ አስተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰቡን በተሻለ ለማገልገል። 

እንዲሁም አጠቃላይ የግብረመልስ ቅጽ እና የሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ ዳሰሳ መሙላት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ የፍለጋ ድረገጽ እዚህ ይጎብኙ። 

እዚህ ይበልጥ ያንብቡ


4. ስለ ኮቪድ-19  

ወደ ስፕሪንግ ዕረፍት ስንሄድ፣ እባክዎን MCPS የኮቪድ-19 ሁኔታዎች በይፋ እንዳልተቀየሩ ልብ ይበሉ። ኮቪድ፣ ጉንፋን፣ እና ኖሮቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም እየተሰራጩ ናቸው፤ ስለዚህ በእረፍት ጊዜ ሲጓዙ እና ብዙ ሰዎች ባሉበት ስትሰባሰቡ የጤና አጠባበቅ ልማዶችን ያስታውሱ። MCPS ለኮቪድ-19 የሚሰጠውን የአምስት ቀን የማግለል ጊዜ መከተሉን የሚቀጥል ሲሆን የተሻሻሉ ሂደቶችን ከእረፍት በኋላ ከኤፕሪል 15 ጀምሮ ያሳውቃል።


5. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች 

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) የሚሰጥበት ሰነድ የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ኤፕሪል 5 ነው። 240 እና ከዚያ በላይ (SSL) ሰአት ላላቸው ሲንየር ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምስጋና ሰርተፍኬት ለማግኘት እና ለመጀመሪያ ጊዜ 75-ሰዓት SSL ምረቃ መስፈርት ላጠናቀቁ ተማሪዎች ማንኛውም የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሱፐርኢንተንደንት SSL ሽልማት ለማግኘት። የበለጠ መረጃ ለማግኘት SSL ድረገጽ ይጎብኙ። 


RespectFest የታዳጊ ወጣቶች ጥቃት እና ግንኙነቶችን የሚመለከት አውደርእይ ያካሄዳል
RespectFest እሑድ፣ ኤፕሪል 7 በዊተን የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል/ Wheaton Community Recreation Center በኦንላይን የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎችን እና በአካል የሚቀርብ ፌስቲቫል ያካሄዳል። RespectFest ስለ ጤናማ ግንኙነቶች ትኩረት ይሰጣል እና ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች እና ስድቦች/ማንጓጠጥን በሚመለከት ግንዛቤ ይሰጣል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ


ከትምህርት-ቤት ውጭ የሚከናወኑ ሁለት መጪ ዕድሎች 

MCPS ተማሪዎች ትምህርት ቤት በሌላቸው ቀን ኤፕሪል 10 ከጠዋቱ 9 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ “Grow Your Own” የተሰኘ መርኃግብር በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ያስተናግዳል።  RSVP/ይመዝገቡ እስከ ኤፕሪል 1

ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 ከጠዋቱ 9፡30 a.m. ላይ በሚጀመረው "Earth Day Urban Farm and Sustainability Hub" ተማሪዎች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። RSVPእዚህይመዝገቡ። ይበልጥ ያንብቡ


ኤፕሪል 13 ወደ ቀጣዩ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ይምጡ

የመካከለኛ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትኩረት መስጠት አለባቸው! MCPS 3ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 13 ከጠዋቱ 8፡30 a.m.–3፡35 p.m. በቲልደን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስተናግዳል። ይህ ዝግጅት የተነደፈው MCPS የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ስለ አየር ንብረት ለውጥ ለማስተማር እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ፕሮጀክቶችን የሚፈጥሩበት መገልገያዎችን ለማስታጠቅ ነው። ይበልጥ ያንብቡ 


ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ ኤፕሪል 20 ይካሄዳል፤ የፅሁፍ ውድድር ማቅረቢያ ቀን ኤፕሪል 10ነው።

ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ወጣት ወንድ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ የተደረገ ጥሪ! ተማሪዎን ለስፕሪንግ 2024 ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ በማስመዝገብና በማበረታታት የስኬት መንገዳቸውን ያቀጣጠሉ። ኮንፈረንሱ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 20 በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ከጠዋቱ 8 a.m.–2 p.m. ይካሄዳል። ምዝገባው የሚዘጋው ረቡዕ፣ ኤፕሪል 3 ነው። ያለው ቦታ ውስን ነው።

እዚህ ይመዝገቡ። 

ይበልጥ ያንብቡ 


6. መልካም ዜና 

2023–2024 የዊንተር ወቅት የስቴት አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የስቴት ስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማቶችን ላሸነፉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና አሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ። ዝርዝሩን ያንብቡ 


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ መሪዎች በቅርቡ ከህግ አውጭዎች እና ዩ. ኤስ. ሴኔተሮች ጋር የማቀንቀን ስብሰባዎች ላይ ተሳትፈዋል። ቤን ካርዲን እና ክሪስ ቫን ሆለን፣ እና ዩ.ኤስ የህዝብ ተወካዮች ጄሚ ራስኪን እና ዴቪድ ትሮን ተማሪዎቹ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሪጅናል የተማሪዎች ጎቨርንመንት አሶሴሼን/ Montgomery County Regional Student Government Association (SGA)፣ የካውንቲ አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት SGA አካል ናቸው።  ተሳታፊዎች ድምፃቸውን ለማሰማት እና ወሳኝ በሆኑ ርዕሶች ላይ ወጣቶችን ያማከለ ክፍያዎችን በሚመለከት አሁን በሥራ ላይ ያለውን ህግ መርምረዋል። 


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች “Heads Up, Phones Down” ተማሪዎች በሚያሽከረክሩበት እና በሚራመዱበት ወቅት ሞባይል ስልክ እንዳያዘናጋቸው የሚበረታታ ቪዲዮ እንዲያዘጋጁ የተጠየቁበትን የቪዲዮ ውድድር ያሸነፋችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! የዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Anjolaoluwa Adeleke የግለሰብ ሽልማት አሸናፊ ነበር። የአሸናፊዎችን ዝርዝር ያንብቡ 


በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ማርች 19-20 በተካሄደው "Montgomery County National Association for College Admission Counseling (NACAC)" ብሔራዊ የኮሌጅ ትርኢት ላይ ተሳትፈተዋል። በዚህ የነጻ ዝግጅት ከ 275 በላይ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች ተገኝተዋል። የፎተግራፍ ክምችቱን/ጋለሪውን ይመልከቱ። 



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)