መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕረል 4, 2024

1. ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ደህንነት እና ዲስፕሊን ለማህበረሰብ የተላከ መልዕክት።

ከስፕሪንግ ዕረፍት በኋላ፥ በዲስትሪክቱ ውስጥ ደህንነትን እና ሠላምን ለማረጋገጥ MCPS የተማሪ የስነምግባር መመሪያን ለመተግበር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ዲስትሪክት-አቀፍ መልእክት አስተላልፏል። በተግባር፣ MCPS የተማሪ የስነምግባር ደንብ በርካታ የተከለከሉ ባህሪያትን ይዘረዝራል። የባህሪ ብልሹነትን ለማረም የሚደረግ ጣልቃገብነት ብልሹ ባህሪ የሚያስከትላቸውን መዘዞች ለማስወገድ ትምህርታዊ የተሀድሶ እርምጃዎች በፍትሃዊነት መተግበር እንዳለባቸው ይዘረዝራል። መሠረታዊው ነገር፡- ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመጠበቅ መወሰድ ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ስለሆነ ይህንን ግብ ለማሳካት ሁሉን አቀፍ እርምጃ ይተገበራል።
ሙሉውን መልእክት እዚህ ያንብቡ።


2. ለ 2024 የፀሐይ ግርዶሽ ተዘጋጁ

ሰኞ፣ ኤፕሪል 8 የሞንትጎመሪ ካውንቲ 2፡04 p.m. ጀምሮ ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ያጋጥመዋል። 3፡20 p.m. አካባቢ ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ ሊኖር ይችላል። በዚህ ጊዜ ውጭ ለመውጣት ከፈለጋችሁ ፀሐይን በቀጥታ መመልከት የዓይን ጉዳት ስለሚያስከትል የፀሐይ ግርዶሽ መነፅር ሳይኖር በቀጥታ ወደ ፀሐይ አትመልከቱ። ተማሪዎች ወደ ውጭ ወጥተው እንዲመለከቱ የሚያደርጉ ትምህርት ቤቶች የግርዶሽ ደህንነት መጠበቅ እንዳለባቸው እንዲለማመዱ ለተማሪዎች እንዲገለጽላቸው መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ ሰአት አስቀድመው የአትሌቲክስ ውድድሮችን የመጀመር እቅድ ያላቸው ከሆነ ሰአቱ እስከ 4፡45 p.m. ይዘገያል። ደህንነት የመጠበቅ ምክሮችን እና ለቤተሰብ ተስማሚ እንቅስቃሴዎችን ለመመልከት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።


3. የትምህርት ቦርድ (BOE) ስለ ቤት ስራ እና በቦርድ የሚሰየሙ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መሪዎችን በሚመለከት በሁለት ፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት መስማት ይፈልጋል።

የትምህርት ቦርድ በተሻሻለው ፖሊሲ IKB፣ ስለ ቤት ስራ እና በቦርድ የሚሰየሙ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መሪዎችን በሚመለከት አዲስ የቀረበ ፖሊሲ GEA፣ላይ አስተያየቶችን ይፈልጋል።

IKB ማሻሻያዎች ረቂቅ እና አዲስ የቀረበ ፖሊሲ GEA ከማርች 20, 2024 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት ቀርቧል። የአስተያየት መስጫው ጊዜ ኤፕሪል 24፣ 2024 ያበቃል። የቦርድ ፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ሜይ 16, 2024 ስብሰባ ላይ ከህዝብ የተሰጡ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዟል። ይበልጥ ያንብቡ 


4. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች 

ስለ ሜሪላንድ የወደፊት ብሉፕሪንት የበለጠ ይወቁ

ስለ ሜሪላንድ የወደፊት ሁኔታ ብሉፕሪንት እና በሜሪላንድ ውስጥ MCPS እና የትምህርት ስርአትን እንዴት አወንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር እንደታቀደ ለማወቅ "To the point" የተሰኘ የቅርብ ጊዜውን ተከታታይ ክፍል ይመልከቱ። የብሉፕሪንት አምስቱ አእማዶች/ምሰሶዎች የህጻናት ትምህርት፣ ከፍተኛ ጥራትና ብቃት ያላቸው የተለያዩ መምህራን፣ የኮሌጅ እና የስራ ዝግጁነት፣ ሁሉም ተማሪዎች ስኬታማ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተጨማሪ የትምህርት መርጃዎች፣ አስተዳደር እና ተጠያቂነትን ያካትታሉ። 


የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰነድ የሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ኤፕሪል 5 ነው። 240 እና ከዚያ በላይ (SSL) ሰአት ላላቸው ሲንየር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የምስጋና ሰርተፍኬት እና ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ 75-ሰዓት SSL ምረቃ መስፈርቶችን ላጠናቀቁት የሱፐርኢንተንደንት SSL ሽልማት ይሰጣል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት SSL ድረገጽ ይጎብኙ። 


RespectFest የታዳጊ ወጣቶች ጥቃት እና ግንኙነቶችን የሚመለከት አውደርእይ ያካሄዳል
RespectFest እሑድ፣ ኤፕሪል 7 በዊተን የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል በኦንላይን የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎችን እና በአካል የሚቀርብ ፌስቲቫል ያካሄዳል። RespectFest ስለ ጤናማ ግንኙነቶች ትኩረት ይሰጣል እና ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች እና ስድቦች/ማንጓጠጥን በሚመለከት ግንዛቤ ይሰጣል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ


"First REACH Urban and Sustainability Farm" የከተማ ዘላቂ እርሻን ለማንፀባረቅ "Earth Day" ዝግጅት ይካሄዳል 

ተማሪዎች ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 በኤ.ማሪዮ ሎኢደርማን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/A. Mario Loiederman Middle School ጠዋት 9፡30 a.m. ላይ በሚጀመረው "Earth Day Urban Farm and Sustainability Hub" በበጎ ፈቃደኝነት ትምህርታዊ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። 

RSVP እዚህ ይመዝገቡ

ይበልጥ ያንብቡ


ኤፕሪል 13 በሚደረገው የወጣቶች የአየር ንብረት ጉባኤ ለመሳተፍ ይምጡ

የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትኩረት መስጠት አለባቸው! MCPS 3ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 13 ከጠዋቱ 8፡30 a.m.–3፡30 p.m. በቲልደን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይስተናገዳል። ይህ ዝግጅት የተነደፈው MCPS የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ስለ አየር ንብረት ለውጥ ለማስተማር እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ፕሮጀክቶችን የሚፈጥሩበት መገልገያዎችን ለማስታጠቅ ነው። ይበልጥ ያንብቡ 

5. መልካም ዜና

የናሳ ጠፈርተኞች በሮሊንግ ቴራስ ት/ቤት በመገኘት ተማሪዎችን አስገርመዋል

የሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የስፕሪንግ ዕረፍት ከመደረጉ በፊት አንድ ትልቅ አስገራሚ ነገር አግኝተዋል። በጋላክሲያችን ውስጥ ስላላቸው ልምድ ለመነጋገር ሶስት የብሔራዊ ኤሮናውቲክስና የጠፈር አስተዳደር (ናሳ) ጠፈርተኞች/National Aeronautics and Space Administration (NASA) ትምህርት ቤቱን ጎብኝተዋል። ይበልጥ ያንብቡ 


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የወጣት ፍትሃዊነት ዝግጅት ያመለጠዎት ከሆነ፦

ለሁለት አመታት፣ MCPS ከ Epic Art Universe ጋር በመተባበር የወጣት እኩልነትና ፍትኃዊነት ስብሰባዎችን እና አነስተኛ ዝግጅቶችን በትምህርት አመቱ Kickbacks አካሂዷል። እነዚህ ዝግጅቶች ተማሪዎች ኢፍትሃዊነት የሚያስከትለውን ተፅእኖ በቀጥታ እንዲሰሙ/እንዲገነዘቡ፣ የግንኙነት መረባቸውን እንዲያሰፉ እና MCPS፣ Epic Art Universe እና ሌሎች በፍትሃዊነት ዙሪያ ስለሚሰሩት ስራ የበለጠ እንዲያውቁ እድል ይሰጣቸዋል። 



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)