1. ስለሚቀጥለው የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት የእርስዎን ግብአት ያጋሩን።
የትምህርት ቦርድ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎቶች እና ምኞታቸውን መገንዘብ የሚችል/የምትችል ብቃት ያለው/ያላት ጥልቅ እና ግልጸኝነትን የሚያንፀባርቅ/የምታንፀባርቅ ግንዛቤ ያለው/ያላት ሱፐር ኢንተንደንት በመፈለግ ላይ ነው። እባክዎ በኦንላይን ዳሰሳለመሙላት ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ። ዳሰሳው ስለ ዲስትሪክቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ያለዎትን አስተያየት፣ሃሳብ፣እና የሚጠበቁ ነገሮችን ለማካፈል እድል ይሰጥዎታል። ይበልጥ ያንብቡ
2. ትምህርት ቤት መገኘት እና መከታተል እጅግ አስፈላጊ ነው፥ ተማሪዎን በየቀኑ ትምህርት ቤት እንዲገኝ/እንድትገኝ መርዳት ያስፈልጋል
MCPS ተማሪዎች ዘወትር በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ ለመደገፍ ከቤተሰቦች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ ነው። በአራተኛው ሩብ ክፍለጊዜ፣ ቤተሰቦች ልጃቸውን (ልጆቻቸውን) በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ የተቻለውን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ ለመርዳት MCPS የክትትል መልእክቶችን በማሳሰቢያ መተግበሪያ ይልካል። በሩብ ዓመቱ ውስጥ ተማሪ ሶስት ቀናት፣ አምስት ቀናት፣ እና አሥር ቀናት ት/ቤት በማይ(ት)ገኝበት ጊዜ ወዲያውኑ መልእክት ይላካል። መልእክቶቹ የተነደፉት መረጃ ሰጭ፣ ባህልን የጠበቁ፣ በአግባቡ ድጋፍ ሰጪ እንዲሆኑ ነው። አንድ ተማሪ ከተመዘገበ(ች)በት ጊዜ አንስቶ 10 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ከቀረ(ች) ትምህርት ላይ እንደሌለ(ች) ይቆጠራል። ያስታውሱ፥ የልጆችዎን በትምህርት ላይ ለመገኘት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ለማስወገድና ለመርዳት የትምህርት ቤት ሰራተኞች ሁል ጊዜ ዝግጁ ናቸው።
3. ለቅድመ መዋለ ህፃናት፣ መዋለ ህፃናት፣ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።
መዋለ ህፃናት፥ እስከ ሴፕቴምበር 1, 2024 አምስት (5) አመት የሚሆናቸው ልጆች መዋዕለ ህጻናት ለመመዝገብ ብቁ ናቸው።
ቅድመ መዋእለ ህጻናት እና ሄድ ስታርት፦ ሰፕተምበር 1, 2024 ወይም ከዚያ በፊት አራት (4) አመት የሞላቸው ህጻናትን ኦንላይን ወይም በአካል ቀርበው ማስመዝገብ ይችላሉ። ለማመልከት የቤተሰብ ገቢ-ብቁ መሆን አለበት። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት፦ ሪጅናል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሠመር ፕሮግራሞች በሞንትጎመሪ ብሌር፣ ሴኔካ ቫሊ፣ እና ሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአካል ተገኝተው ይማራሉ።
4. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች
"First REACH Urban and Sustainability Farm" የከተማ ዘላቂ እርሻን ለማንፀባረቅ "Earth Day" ዝግጅት ይካሄዳል
ተማሪዎች ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 ከጠዋቱ 9፡30 a.m. ላይ በማርዮ ሉደርማን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (A. Mario Loiederman Middle School) እና ዌለር ሮድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Weller Road Elementary School) ተገኝተው "Earth Day Urban Farm and Sustainability Hub" የተሰኘ የበጎ ፈቃደኝነት ትምህርት ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
ሎደርማን/Loiederman event ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ RSVP/እዚህ ይመዝገቡ።
ዌለር ሮድ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ/Weller Road event(የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች) እዚህ ይመዝገቡ/RSVP።
ቀኑን ያስታውሱ፡ ስለ ደህንነት ቀን ሜይ 11 ዝግጅት ይኖራል
የሞንትጎመሪ የትራንስፖርት መምሪያ ሁሉንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ቅዳሜ ሜይ 11 በካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማእከል (CESC) ሮክቪል የመኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ ስለ ደህንነት ቀን መታሰቢያ ላይ እንዲገኙ ይጋብዛል። በአዝናኝ እና በበዓላት አከባቢ ህብረተሰቡ ስለ ትራፊክ ደህንነት የበለጠ ለማወቅ ስለ ደህንነት ቀን ማህበረሰቡን በአንድ ላይ ያሰባስባል። አድራሻ፦ CESC is located at 850 Hungerford Drive ይበልጥ ያንብቡ
ማሳሰቢያ፦ ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፀረ አድልዎ መግለጫ ያንብቡ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና የማህበረሰብ አባላት የሚገኙበት ስፍራ ነው። የተማሪዎችን አካዴሚያዊ ስኬት እና አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ እና ማህበራዊ/ስሜታዊ ደህንነት ከፍ ለማድረግ የተነደፉትን የትምህርት እድሎች፣ ጥንካሬዎች፣ግብዓቶች እና ድጋፎችን በፍትሃዊነት ተጠቃሚ ለማድረግ በቦርዱ ጥልቅ ቁርጠኝነት የሚመራ የትምህርት ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም ሰራተኞች የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያከናውኑ ኃላፊነት እንዳለባቸው ማረጋገጥ እንፈልጋለን። ሙሉውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፀረ አድልዎ መግለጫ እዚህትንሽ ጊዜ ወስደው ይገምግሙ፤ዘወትር ለማንበብ እዚህ MCPS ድረ ገጽ ላይ ይገኛል።
5. መልካም ዜና
MCPS ለጤናማ የላቀ ማህበራዊ አገልግሎት 2024 የማግና ሽልማት አግኝቷል
ብሔራዊ የትምህርት ቤቶች ቦርድ ማኅበር በቅርቡ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የደኅንነት ማኅበራዊ ሠራተኛ ፕሮግራም የብር ማግና ሽልማት ሽልማት ሰጥቷል። ማግና ሽልማቶች/Magna Awards ለተማሪዎች እና ለሚኖሩባቸው ማህበረሰቦች ለውጥ እያመጡ ያሉ የፈጠራ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ይሰጣል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በሁለተኛው አመታዊ የቀጣዩ ትውልድ የአመራር ቀን ላይ ተገኝተዋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎች አመራር እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ክፍል ሁለተኛውን የቀጣይ ትውልድ አመራር ቀን ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 6 በዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተናግዷል። በዲስትሪክቱ ውስጥ ከሚገኙ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ 500 የሚጠጉ የአራተኛ እና የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች በአመራር ኮንፈረንሱ ላይ ተሳትፈዋል። ተማሪዎች በሰለጠኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ መሪዎች ፈጠራ የተዘጋጁ እና የሚመሩ ወርክሾፖች ላይ ተሳትፈዋል። ይበልጥ ያንብቡ
የሰራተኞች ትኩረት፦ ለዚህ አመት የኤድዋርድ ሸርሊ ሽልማት አሸናፊ እንኳን ደስ አለዎት
የአለም አቀፍ ምዝገባ እና ምደባ (IAE) ዳይሬክተር የሆኑት ማርጋሪታ ቦሆርኬዝ የዘንድሮ የዶክተር ኤድዋርድ ሸርሊ ሽልማት በትምህርት አስተዳደር እና ቁጥጥር የላቀ አገልግሎት አሸናፊ ሆነዋል። ይበልጥ ያንብቡ
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org