መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕረል 25, 2024

1. ማሻሻያዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በአዲስ የዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ ላይ ወቅታዊ መረጃዎች ይቀርባሉ 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሞንትጎመሪ ካውንቲ ኢንስፔክተር ጀነራል (OIG) ተለይተው የታወቁትን የአሠራር ጉድለቶች ለማስተካከል አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን ለማህበረሰቡ ለማሳወቅ አዲስ ድረ-ገጽ ጀምሯል። የማስተካከያ እርምጃዎች ግስጋሴ ሪፖርት ድረ-ገጽላይ OIG ግኝቶችን እና ምክረሃሳቦችን፣እንዲሁም የዲስትሪክቱን ምላሽ ሰጪ እርምጃዎች፣የስራ ሁኔታ ጭምር ይቀርባል። እንዲሁም በትምህርት ቦርድ የፖሊሲ ስራ እና ከማህበረሰብ የተግባር ስራ ቡድን የተሰጡ ምክረሃሳቦችንና አስተያየቶችን ያቀርባል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማንኛውንም አይነት ቅሬታዎች በተለይም ከጉልበተኝነት፣ ትንኮሳ እና የፆታ ብልግና ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን በአግባቡ ለመፍታት ቁርጠኛ ነው።

ድረ-ገጹን እዚህ መጎብኘት ወይም MCPS ድረገጽ ላይ የተወሰደ የማስተካከያ እርምጃ መፈለግ ይችላሉ። 


2. ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ የኦንላይን ዳሰሳ አርብ፣ ኤፕሪል 26 ይዘጋል

ሁሉም ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት ኤፕሪል 26 አጭር የኦንላይን ዳሰሳ ለመሙላት ጥቂት ደቂቃዎችን እንዲወስዱ እናበረታታለን። በዳሰሳ የተሰበሰበው ግብረመልስ ከሌሎች የህዝብ ተሳትፎ አስተያየቶች ጋር በማጣመር የአመራር ክህሎት መገለጫ ለማዘጋጀት ይረዳናል። ቦርዱ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትነት እጩዎችን በሚያወዳድርበት ጊዜ ተፈላጊውን የአመራር ክህሎት መገለጫ ይጠቀማል። ጥናቱ ስፓኒሽኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ኮሪያንኛ፣ ቬትናምኛ እና አማርኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል።

ስለ ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ የተዘጋጀውን ድረ-ገጽ በመጎብኘት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ቦርዱን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ በመከታተል ስለ ሂደቱ ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።


3. ተማሪዎችን ለኮሌጅ፣ ለስራ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ማዘጋጀት

ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች የተማሪን ስኬት ለማረጋገጥ አብረው እንዲሰሩ ስለመመሪያው ለማወቅ የቅርብ ጊዜውን "To the Point" ይመልከቱ። የኮሌጅ፣ የስራ እና የማህበረሰብ ዝግጁነት መንገድ እያንዳንዱ ተማሪ የሚፈልገውን ድጋፍ ማግኘቱ(ቷ)ን ለማረጋገጥ የተማሪዎችን ጥንካሬዎች እና ማሻሻል ያለባቸውን ለመለየት ይረዳል። ስልቱ ተማሪዎች በተወሰኑ የክፍል ደረጃዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ተከታታይ ምእራፎች እና ዋና ዋና ብቃቶች አሉት። 


4. ሜይ ወር ላይ በሚካሄዱት መጪዎቹ ዝግጅቶች ላይ ለመሳተፍ ቀኖችን ይቆጥቡ 

ሜይ 1 የዚህ አመት ሻምፒዮና የህፃናት ክብረ በዓል ይከታተሉ!

እሮብ፣ ሜይ 1 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህር እና የአመቱ ምርጥ የአገልግሎት ሰራተኛ ማስታወቂያዎችን ለማግኘት ስለ ዘንድሮው ዝግጅት የቀጥታ ስርጭት ከእኛ ጋር ይከታተሉ። በዓሉ ሌሎች ልዩ መምህራንን፣ አስተዳዳሪዎችን እና የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኞችን እውቅና ይሰጣል። ይበልጥ ያንብቡ 

የዘንድሮው በዓል ከቀኑ 6፡30 p.m. ስለሚሠራጭ MCPS ድረገጽላይ ይከታተሉ። የቀጥታ ስርጭቱን እዚህ መመልከት ይችላሉ።

ይበልጥ ያንብቡ 


ቤተሰቦች የልዩ ትምህርት መርጃ አውደ ርእይ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል

ቅዳሜ፣ ሜይ 11 በሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዚህ አመት የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ አውደ ርዕይ እንዳያመልጥዎት። የነጻ ዝግጅቱ የሚካሄደው ከጠዋቱ 10፡00 a.m. እስከ 1፡00 p.m., ሲሆን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወላጆች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። አውደ ርዕዩ ከተለያዩ የማህበረሰብ ግብዓቶች እና አቅራቢዎች የተውጣጡ ጠቃሚ ግብአቶችን እና አዝናኝ የልጆች እንቅስቃሴዎችን፣ ጨረቃ መውጫ፣ ሙዚቃ፣ ስነ ጥበባትን እና የባሉን/ፊኛ አርቲስቶችን ያካትታል።


የቤተሰብ መዝናኛ፣ እና የትራፊክ እና የእግረኛ ደህንነት መረጃ የሚሠራጭበት የደህንነት ቀን 

ሁሉም ቤተሰቦች ቅዳሜ ሜይ 11 በሮክቪል ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማእከል (CESC) የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ በሚካሄደው የደህንነት ቀን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። "በደህንነት ቀን" ህብረተሰቡ በመዝናናት እና በበዓል ቀናት ስለ ትራፊክ ደህንነት የበለጠ ጥንቃቄ ስለማድረግ ለማወቅና መረጃ ለማሠራጨት በአንድ ላይ ይሰበሰባል። ይበልጥ ያንብቡ 


ተማሪዎች "Out-of-School Time Co-Ed Football Clinic" ሜይ 14 ከትምህርት ውጪ ነፃ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል

ከ1ኛክፍል እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ማክሰኞ፣ ሜይ 14 ከትምህርት ቀርተው ወደ ነፃ "coed football clinic" እንዲመጡ ተጋብዘዋል። ክሊኒኩ 480 ክለብ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር ከትምህርት ሰዓት ውጭ ፕሮግራም "Laytonia Turf Field in Gaithersburg" ከጠዋቱ 10፡30 a.m. እና 3፡30 p.m. ይስተናገዳል። ተጨማሪ ያንብቡ። 

ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እዚህ ይመዝገቡ/RSVP here

ለመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች እዚህ ይመዝገቡ/RSVP here


የጌትስበርግ መፅሀፍት ፌስቲቫል/አውደርዕይ ሜይ 18 እንዳያመልጥዎት ያስታውሱ

የጌትስበርግ መፅሀፍት ፌስቲቫል/አውደርዕይ ፣ የመፅሀፍት፣ የፀሀፊዎች እና የስነ-ፅሁፍ ልህቀት ክብረ በአል፣ቅዳሜ፣ ሜይ 18 ከጠዋት 10 a.m. እስከ ከሰአት 6 p.m. ይካሄዳል። አድራሻው፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue, Gaithersburg  ይበልጥ ያንብቡ


5. መልካም ዜና

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና የካውንቲ መሪዎች፣ የማህበረሰብ እና የንግድ ድርጅት አጋሮች Earth Day ለአዲሱ REACH Hub urban farm/የከተማ እርሻበ አ.ማሪዮ ሎደርማን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተደረገው የበጎ ፈቃደኞች ዝግጅት ላይ በመገኘት ተሳትፈዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ. የፎቶ ክምችት ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ። 


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፎል 2024 የውድድር ዘመን ከባልቲሞር ሬቨንስ እና አንደር አርሟር ጋር በመተባበር የልጃገረዶች እግር ኳስ "pilot girls’ flag football" ግጥሚያ ያደርጋል። ትብብሩ 25 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መገልገያዎች እና ትጥቅ ዩኒፎርሞችን ጨምሮ ለፓይለት መርሃ ግብሩ የድጎማ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። ይበልጥ ያንብቡ 


ዶ/ር ዛዲያ ጋድስደን፣ የታኮማ ፓርክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት፣ የዚህ አመት የዋሽንግተን ፖስት የአመቱ ምርጥ ርዕሰ መምህርነትት ተሰይመዋል። ዶ/ር ጋድስደን በልዩ ሥራቸው እና ለተማሪዎች ባደረጉት ትጋት ከተመረጡት የመጨረሻ እጩዎች 16 ርእሰ መምህራን አንዱ ነናቸው።ዋሽንግተን ፖስት የረዥም ጊዜ የዊንስተን ቸርችል የማህበራዊ ጥናት መምህርን ክሪስ ፎርኒ የአመቱ ምርጥ አስተማሪ መሆናቸውን እውቅና ሰጥቷቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ 


በደርዘን የሚቆጠሩ ወጣት ወንድ ተማሪዎች ኤፕሪል 20 ስፕሪንግ ወቅት በተካሄደው ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ተገኝተዋል። የዘንድሮው የስፕሪንግ ኮንፈረንስ ተማሪዎች እራሳቸውን የተወዳዳሪነት/የተፎካካሪነት ብቃት እንደሚኖራቸው እንዲያጤኑ/እንዲገነዘቡ አበረታቷቸዋል፣ይህም ጠንክሮ መሥራትና ጥረት ማድረግ፣ ብልህ መሆን እና በጥሩ ብቃት የመጫወት ህልማቸውን ግብ እንዲያደርሱ ያደርጋል። 


በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ስቴፋኒ ጎመር የሜሪላንድ ታሪክ ቀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዓመቱ ምርጥ መምህር በመሆን ተሰይመዋል። የእርሳቸውን የሜሪላንድ ሰብአዊነት ባህሪ ያንብቡ።. ሜይ 4 በሜሪላንድ የታሪክ ቀን በስቴት አቀፍ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ አክብሮት ተሰጥቷቸዋል።


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በዘገባዎች ላይ፦ 



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)