መጪዎቹ የተማሪዎች እና የቤተሰብ ዝግጅቶች እንዳያመልጥዎት
ስለ እያንዳንዱ ዝግጅት የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሉትን ርዕሶች ጠቅ ያድርጉ።
ሃያ ሁለት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ብሄራዊ የሜሪት ስኮላርሺፕ አሸናፊዎች ሆነዋል
ከስምንት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 22 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በብሔራዊ የሜሬት ስኮላርሺፕ ኮርፖሬሽን የገንዘብ ድጋፍ ለእያንዳንዳቸው $2,500 የብሔራዊ ሽልማት ስኮላርሺፕ ተሰጥቷቸዋል። ተማሪዎቹ በሜሪላንድ ውስጥ ካሉት 43 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየሮች መካከል በቅርቡ የብሔራዊ ሜሪት ሽልማት ካገኙት መካከል የተመረጡ ናቸው። ምሁራኑ የተመረጡት ከ15,000 በላይ የመጨረሻ እጩዎች መካከል ሲሆን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የአንድ ጊዜ የ2,500 ዶላር ሽልማት ያገኛሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
የብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የጋዜጠኝነት ፕሮግራምን ለመደገፍ $5,000 ዶላር ያልታሰበ አድናቆት አግኝተዋል
ብሄራዊ የመምህራን የምስጋና ሳምንት ለማክበር ሰኞ ሲጀመር ሶስት የሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ከብሔራዊ ትምህርት ማህበር (NEA) እና ከብሄራዊ PTA በተገኘ $5,000 ያልታሰበ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። ጄረሚ ስቴልዝነር፣ ማሪያ ዩጄኒያ ታኖስ እና ሚሼል ኤሊ (Jeremy Stelzner, Maria Eugenia Tanos and Michelle Elie) የብሌርን በአገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘ እና የተሸለመውን የተማሪዎች ጋዜጣ ሲልቨር ቺፕስ በአርታዒነት ክትትል ያደርጋሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
ለሪጅናል እና ሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ የሠመር ትምህርት የመጀመሪያው ዙር ምዝገባ ሜይ 31 ይዘጋል
ከሁለቱም የሪጅናል የሠመር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም(በአካል) እና የሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ፕሮግራም (ቨርቹዋል) የመጀመሪያው የምዝገባ ክፍለጊዜ አርብ፣ ሜይ 31 ይዘጋል። በሁለቱም ፕሮግራሞች ውስጥ የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ከጁን 26 እስከ ጁላይ 16 (ጁላይ 4 ትምህርት የለም) ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ከጁላይ 18 እስከ ኦገስት 6. የሚካሄድ ሲሆን የሁለተኛው ክፍለጊዜ ምዝገባ እሁድ፣ ጁን 30 ይዘጋል። ወላጆች ተማሪዎቻቸውን ParentVue አካውንታቸው ላይ ማስመዝገብ ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
2024 የምረቃ መርሃ ግብር በይነመረብ ላይ ይገኛል
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመክፈቻ ስነስርዓቶች እሮብ፣ ሜይ 29 እና እሮብ፣ ጁን 12 መካከል ይከናወናሉ። በተናጠል የሚደረጉት የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካምፓሶች፣ በዋሽንግተን ዲሲ DAR ኮንስቲትዩሽን አዳራሽ፣ እና በማውንት ሴንት ሜሪ ዩንቨርስቲ ካምፓስ፣ እንዲሁም በዩንቨርስቲ ኦቭ ሜሪላንድ ባልቲሞር ካውንቲ ይካሄዳሉ።
ለእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ቀን፣ ቦታ፣እና ሰዓት ለማወቅ እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
ሜይ ወር የእስያ ፓሲፊክ የአሜሪካውያን ቅርስ እና የአይሁድ አሜሪካውያን ቅርስ የሚዘከርበት ወር ነው።
MCPS የእስያ ፓስፊክ አሜሪካውያንን ታሪክ እና ቅርስ እውቅና ይሰጣል፣ ያከብራል። ዲስትሪክቱ ይህንን ታሪክ በስርዓተ-ትምህርት ውስጥ በማካተት የእስያ ፓስፊክ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ግንዛቤን፣ መተሳሰብን፣ እና መደጋገፍን ለማጎልበት ቁርጠኛ ነው።
ማክሰኞ፣ ሜይ 21
ሰአት፣ 6-7:30 p.m.
ቦታ፣Zoom
ለምዝገባ እዚህ ጠቅ ያድርጉ
የዝግጅቱን በራሪ ወረቀት/ፍላየር ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ
ብሄራዊ የአይሁድ አሜሪካውያን ቅርስ በሚዘከርበት ወር ሁሉም አይሁዳውያን አሜሪካውያን ለአሜሪካ ታሪክ፣ ባህል እና ማህበረሰብ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡበት እና የሚያከብሩበት ጊዜ ነው። MCPS ተማሪዎችን ስለ አይሁዶች አሜሪካውያን ታሪክ ለማስተማር እና በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ የፀረ ሴሚቲዝም አመለካከትን ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ ነው።
MCPS የማህበራዊ ጥናት ቡድን የአይሁዶች ታሪክ በአንደኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት ላይ እንዴት እንደተካተተ ያብራራሉ። ለመሣተፍ ይመዝገቡ። ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ተንከባካቢዎች መምጣት እና መሣተፍ ይችላሉ።
ማክስኞ፣ ሜይ 23
ሠዓት፡ 6:30 - 7:30 p.m.
ቦታ፣Zoom
ለምዝገባ እዚህ ጠቅ ያድርጉ
የዝግጅቱን በራሪ ወረቀት/ፍላየር ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ
ለቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እና ለመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ክፍት ነው።
በሴፕቴምበር 1, 2024 ወይም ከዚያ በፊት 4 አመት የሆናቸው ልጆች በኦንላይን ወይም በአካል በመቅረብ ለቅድመ መዋዕለ ህጻናት እና ለሄድ ስታርት ፕሮግራሞች መመዝገብ ይችላሉ። ለማመልከት ቤተሰቦች በገቢ አንጻር-ብቁ መሆን አለባቸው።
በሴፕቴምበር 1፣2024 ልጆች 5 ዓመት የሞላቸው ከሆነ መዋዕለ ሕፃናት ለመመዝገብ ብቁ ናቸው።
በብሔራዊ የምስክርነት ቦርድ ሥነ ሥርዓት ላይ መምህራን እውቅና አግኝተዋል።
2023 ለሙያዊ ትምህርት ከብሔራዊ ቦርድ የላቀ ደረጃ(NBPTS) የምስክር ወረቀት ላገኛችሁ 152 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህራን እንኳን ደስ አላችሁ! ሌሎች 73 ደግሞ በተሳካ ሁኔታ ሰርተፍኬታቸውን አግኝተዋል።
ቦርዱ 2024 ዓ.ም የክብር አገልግሎት ሽልማት ለተጎናፀፉት እውቅና ሰጥቷል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቦርድ 12 ተሸላሚዎችን እውቅና የሰጠው በህዝባዊ ትምህርት የላቀ አገልግሎት 27ተኛው አመታዊ የሽልማት ፕሮግራም ወቅት ሜይ 7 ላይ ነው። ሽልማቶቹ በቦርዱ የተቋቋሙት ለህዝባዊ ትምህርት እና ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አርአያነት ያለው አስተዋጾ ላደረጉት የትምህርት ባለሙያዎች እውቅና ለመስጠት እና ምስጋና ለማቅረብ ነው። በዝግጅቱ ላይ የነበሩትን ፎተግራፎች ይመልከቱ።
MCPS አራት አዲስ አረንጓዴ ትምህርት ቤቶችን፣ 26 ትምህርት ቤቶች፣ እና አንድ ማእከል እንደገና ማረጋገጫ በመስጠት ጨምሯል።
ዶ/ር ቻርለስ R. ድሩው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የካቢን ጆን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣ እና አልበርት አንስታይን እና ጀምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች 2024 የሜሪላንድ ግሪን ት/ቤቶች ተብለው ተሰይመዋል፣ ይህም MCPS በአጠቃላይ 101 አድርሷል ማለት ነው። ይበልጥ ያንብቡ
ተማሪዎች በብሔራዊ ወደ ትምህርት ቤት የብስክሌት ጉዞ ቀን በብስክሌት ይጓዛሉ
የበሪቺ ፓርክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የቢስክሌት ጉዞ ቀንን ሜይ 8 ካከበሩት በደርዘን የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች መካከል ናቸው፣ ይህም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት በእግር፣ በብስክሌት፣ ወይም በስኩተር እንዲሄዱ የሚያበረታታ ዝግት ነው።
ስለ ብስክሌት ጉዞ ደህንነት ምክር ለማግኘት የMCDOT ወደ ትምህርት ቤቶች ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ድረገጽ ይጎብኙ።
መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦
ሜይ 11 የልዩ ትምህርት መርጃ/ሪሶርስ አውደ ርእይ እና የደህንነት ቀን
ሜይ 14 ፕራይመሪ የምርጫ ቀን—ት/ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው
ሜይ 18 ጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል
ሜይ 23 የትምህርት ቦርድ የሥራ/ቢዝነስ ስብሰባ
ሜይ 24 ለተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን (ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች ብቻ)
ሜይ 27 ሜሞሪያል ዴይ — ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው
ጁን 1 የኩሩ ማህበረሰብ ቀን/Pride Community Day
ጁን 13 ለተማሪዎች የመጨረሻ የትምህርት ቀን፣ ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)
ጁን 14* ውጤት መስጠት እና የተርሙ ማብቂያ እቅድ ማዘጋጀት
ጁን 19 ስርዓት አቀፍ ት/ቤቶች ዝግ የሚሆኑበት ቀን—ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ይሆናሉ
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org