የ MCPS ሱፐርኢንተንደንት—የመጀመሪያ ሳምንት

የዶ/ር ቶማስ ቴይለር መልእክት

ጁላይ 3, 2024

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትነት ሥራዬን ከጀመርኩ ዛሬ ረቡዕ ሦስተኛ ቀኔ ነው። ሰኞ እለት፣ በመጀመሪያው የሥራ ቀኔ የተመለከትኩትን በማንፀባረቅ ለ MCPS ሰራተኞች ገልጬ ነበር፣ ዛሬ ደግሞ ከጁላይ 4 የበዓል ቀን በፊት፣ ለሁላችሁም መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ይህ ዘወትር ሳልመው የነበረ ስራ ነው ብዬ ስናገር ሰምታችሁ ሊሆን ይችላል፣ እና ነውም። ያደግኩበት፣ የተማርኩበት፣ እና አሁን ወደ ማገለግልበት ማህበረሰብ መመለስ አስደሳች እና የሚክስ ሙያ ነው። ጥቂት ትምህርት ቤቶችን የመጎብኘት እድል አግኝቻለሁ፣የሠመር ትምህርት ሲሰጥ እና ሠራተኞች ለመጪው አዲሱ የትምህርት አመት ዝግጅት ጠንክረው ሲሰሩ ለማየት ችያለሁ። 

ጁን 12 በላክንላችሁ የሱፐርኢንተንደንት ዳሰሳ ጉዳይን በተመለከተ ብዙዎቻችሁ ያካፈላችሁትን ግብረ መልስ እያነበብኩ ነበር። በጣም ብዙ ቢሆንም፣ ነገር ግን የሚያሳስብ ነገር ወይም ጥሩ ሀሳብ ያጋራችሁ ስለሆነ፣ በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ የእኔን ውሳኔ አሰጣጥ እና አመራር ስለሚደግፍ ሁሉንም የቀረቡትን ሀሳቦች እንደምንመለከታቸው አረጋግጥላችኋለሁ። ይህ የእርስዎ የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት እንደመሆኑ እርስዎ የሚሉት ሀሳብ ለእኔ አስፈላጊ ነው!

በዚህ መሠረት፣ እስካሁን ድረስ ሀሳብዎን ካላካፈሉ ከእርስዎ ለመስማት እፈልጋለሁ። የግብረ መልስ ቅጹን ለመሙላት እስከ አርብ፣ ጁላይ 5 ቀን ከሰአት በኋላ 4 p.m. ድረስ ክፍት ስለሚሆን ሃሳባችሁን ለማካፈል አሁንም ጊዜ አለ። የቅጹ አገናኝ (ሊንክ) እዚህ ይገኛል ግልጽነት ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነው፣ ስለዚህ ያገኘነውን ግብረመልስ እነሆ እያጋራሁ ነው። እንደአስፈላጊነቱ የትምህርት ቤቶችን፣ የሰራተኞችን፣ የተማሪዎችን ወይም የቤተሰቦችን አድራሻዎች ወይም ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ ቋንቋዎችን ወይም የማንነት መረጃዎችን የሚያመለክት ማንኛውንም መረጃ አስወግደናል። የተሰጡትን ምላሾች፣ ስጋቶችን እና ጥያቄዎችን ማጋራት ግልፅነትን ለማስፈን ጠቃሚ ጥረት እንደሆነ በፅኑ አምናለሁ። 

አላማዬ የሞንትጎመሪ ካውንቲ እና የትምህርት ቤቶችን ስርአት አንድ ላይ ስናንቀሳቅስ በመካከላችን ያሉት የግንኙነት መስመሮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ ነው።

ማዳመጥ አስፈላጊ እና ጠቃሚ በመሆኑ፣መደረግ ያለበት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ተግባራዊ እርምጃም እንዲሁ አስፈላጊ ነው። ለዚህም ነው ስለ Ask MCPS የስልክ መስመር (240-740-3000) እና ስለ MCPS ስፓንሽኛ የስልክ መስመር (240-740-2845) ላስታውሳችሁ የምፈልገው። በእነዚህ መስመሮች ላይ የሚደርሱንን ጥሪዎች እና ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች እንደሆኑ እንዲገነዘቡት ሰራተኞቻችንን ጠይቄያቸዋለሁ። ስጋትዎን ለማስወገድ በምንሰራበት ጊዜ በ 72 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ ማግኘት ይችላሉ።

አዲስ ሱፐርኢንተንደንት እንደመሆኔ መጠን፣ ስለ መጪው የትምህርት ዘመን እና የወደፊት ጊዜያችን ብሩህ ተስፋ አለኝ። ከእናንተ ጋር፣ ከአስደናቂ ሰራተኞቻችን ጋር፣ እንዲሁም ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር ለልጆቻችን ስኬት የሚጠቅም ታላቅ ነገርን ለመስራት እጓጓለሁ። እናንተን ለማገልገል ስለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ!

መልካም እና አስደሳች የነጻነት ቀን በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ከልባዊ ሠላምታ ጋር

Thomas W. Taylor, Ed.D., M.B.A.
MCPS Superintendent of Schools


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org