በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ "ደህንነት" ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ቤተሰቦች፣

ጤና ይስጥልኝ እኔ ማርከስ ጆንስ (Marcus Jones) እባላለሁ፣ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቡድን አባል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል። የትምህርት ስርዓቱን የተቀላቀሉት እንደ ቀድሞ የካውንቲ ፖሊስ አዛዥ ሳይሆን ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ደህንነት ለማስጠበቅና ለማሻሻል እንደ አንድ የህይወት ዘመን የደህንነት ጥበቃ ባለሙያ በመሆን ነው። የእኔ አካሄድ የትምህርት ቤቶቻችንን የተለያዩ ፍላጎቶች የሚያከብር እና ዋጋ ያለው ሲሆን የማህበረሰቡ ትብብር ለስኬታችን ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ። በሙያ ዘመኔ ሁሉ፣ ስለ ደህንነት እና አክብሮት ሙያዊ እሴቶች ጥልቅ ቁርጠኝነት ኖሮኝ የሠራሁ ስለሆነ ይህንኑ ቁርጠኝነቴን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ደህንነት ለማስጠበቅ በኦፊሰርነት ለማገልገል ወስኛለሁ።

ከፖሊስ ዲፓርትመንት ወደ ትምህርት ስርአት ተዛውሬ መሥራት የተለየ አካሄድ እንደሚያስፈልገው ተረድቻለሁ—ይህም ለትምህርት ማህበረሰባችን ልዩ ፍላጎቶች ትብብር እና ትኩረት መስጠት ላይ የሚያተኩር ነው። እውቀቴን፣ግንኙነት፣ እና ከማህበረሰባችን ጋር ያለኝን የረጅም ጊዜ ቁርኝት እየተጠቀምኩ ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ ክፍል (K-12) የትምህርት ቤት ደህንነትን በሚመለከት ሀገራዊ እና የፌዴራል ምርጥ ተሞክሮዎችን በማዋሃድ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ። 

ደህንነት የሁሉም ሰው ሃላፊነት ቢሆንም፣ የቅርብ ጊዜ የት/ቤት እና የሰራተኞች ደህንነት የዳሰሳ ውጤቶች በዲስትሪክቱ ውስጥ የደህንነት ስጋት መኖሩን ያመለክታሉ። MCPS ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አዲሱ ሱፐርኢንተንደንት ያላቸውን ራዕይ እደግፋለሁ። እና ለማየት የምንፈልጋቸውን የተማሪዎችን ባህሪያት የሚመለከቱ ፖሊሲዎችን፣ አፈጻፀሞችን እና የደህንነት ጥበቃ እርምጃዎችን እንዲሁም ድጋፎችን ለማሻሻል ከሚሰሩ የዲስትሪክታችን መሪዎች ጋር በመተባበር ለመስራት ደስተኛ ነኝ። ስለዚህ ስራ በሚቀጥሉት ሳምንታት የበለጠ ትሰማላችሁ። 

2024-2025 ዲስትሪክት አቀፍ ስትራተጂካዊ ትምህርት ቤቶች ደህንነት ስራ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ MCPS ቡድንን ለመቀላቀል አጓጊ ያደርገዋል። ታላቁን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ አባላት ጋር ለመገናኘት፣ ያላችሁን ስጋት ለማዳመጥ፣ እና ትምህርት ቤቶቻችን እያንዳንዱ ተማሪ በእውቀት የሚበለጽግባቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከእናንተ ጋር ለመስራት እጓጓለሁ።

ከልባዊ ሠላምታ ጋር

Marcus Jones
Chiefof Security and Compliance የደህንነት ጥበቃ ዋና ኃላፊ
M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org