ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የተላለፈ መልእክት፦

ደህንነቱ የተጠበቀ የሽጉጥ/ጠመንጃ ማስቀመጫ እና ደህንነት

የተወደዳችሁ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች

የተማሪዎቻችንን ደህንነት ማረጋገጥ እኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባር ነው። ይኼ የዲስትሪክታችን ቁርጠኝነት በመሆኑ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የሽጉጥ/ጠመንጃ ማስቀመጫ አስፈላጊ መሆኑን ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች ጋር መነጋገር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ መልእክት ይኼን የሚመለከተ መረጃ ያሰጣል።

ደህንነቱ የተጠበቀ የሽጉጥ/ጠመንዳጅ የሚያስፈልገው ለምንድነው?
ሽጉጥ/ጠመንጃ በህጻናት እና በታዳጊ ወጣቶች ለሚደርስ አሣዛኝ የሞት አደጋ ዋነኛው መንስኤ በመሆኑ፣ ከሽጉጥ/ጠመንጃ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከል ሁላችንም እርምጃ መውሰድ እንዳለብን መወያየት በጣም አስፈላጊ ነው። ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የጦር መሳሪያ ማስቀመጥ የምንወዳቸውን ሰዎች ካልታሰበ አደጋ ለመጠበቅ እና አደጋዎችን ወይም ሁከቶችን ለመከላከል በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ ነው።

ጠመንጃን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ጠመንጃን/ሽጉጥን በማስቀመጥ ወላጆች እና አሳዳጊዎች የትምህርት ቤቶቻችንን እና የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ ሚና መጫወት ይችላሉ።

ሽጉጥ/ጠመንጃን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዴት መጠበቅ እና ማስቀመጥ እንዲቻል
እያንዳንዱ ቤተሰብ ለአስተማማኝ የጦር መሣሪያ ማስቀመጫ ቅድሚያ እንዲሰጥ እናበረታታለን። ይህ የሚከተለውን አይነት አጠቃቀም ያካትታል፦

  • የሽጉጥ/የጠብመንጃ ካዝና ወይም መቆለፊያ ሳጥኖችን መጠቀም
  • የኬብል መቆለፊያዎችን መጠቀም
  • ቃታ መቆለፍ
  • ለጥይት የተለየ ማስቀመጫ መጠቀም

ከዚህ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦
ከዚህ በታች ደህንነቱ የተጠበቀ የጠመንጃ/የሽጉጥ ማስቀመጫ አስፈላጊነት እና ያልተፈቀደ የጦር መሣርያ ተደራሽነትን ለመከላከል ህጋዊ ግዴታዎችን የሚያብራራ መረጃ አቅርበናል።

ደህንነቱ የተጠበቀ ሽጉጥ/ጠብመንጃ ማስቀመጫ በሚመለከት ሌሎች ጠቃሚ መርጃዎች
(እነዚህ ሪሶርሶች የሚሰጡት በዩኤስ የትምህርት ዲፓርትመንት አማካይነት ነው)

የትምህርት ቤቶቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ እና የተማሪዎችንን ደህንነት ለማረጋገጥ አብረን በጋራ እንስራ።

M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org