እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/Español / 中文 / ፈረንሳይኛ/Français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
ውድ ቤተሰቦች እና አሳዳጊዎች፣
መላው ዲስትሪክታችን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ሁኔታዎችን ሲያስተካክል፣ MCPS በተለመደው የመንገድ ትራፊክ መጨናነቅ እና ነገር ግን በጣም በጥቂቱ በአንዳንድ የትምህርት ቤት አውቶቡስ መስመሮች ላይ መዘግየት ሊያጋጥም እንደሚችል ለቤተሰቦች ማስታወስ እንፈልጋለን። ይህ ሁኔታ በተለይም ፐርፕል የባቡር መስመር ግንባታ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ሊከሰት ይችላል። ከትራንስፖርት ስርዓታችን ስፋት እና ትስስር የተነሳ በግንባታው አቅራቢያ ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች ባሻገር ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል እንገምታለን። ምንም እንኳን በተለየ ሁኔታ መዘግየቶች የሚከሰቱ ቢሆንም፣ በተለይም በአካባቢያችን ያለው የትራፊክ ፍሰት አንዳንድ ጊዜ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል እናውቃለን።
ድጋፍ ያስፈልጋል?
በአውቶቡስ መዘግየት ምክንያት የሚከሰቱ ማናቸውንም ስጋቶች ወይም ችግሮችን ለመቅረፍ፣ MCPS የሚጠቀምበትን ክፍት የትራንስፖርት ስልክ መስመር ማሳወቅ እንፈልጋለን። ይህ አገልግሎት ሰኞ፣ ኦገስት 26 ከጠዋቱ 6:00 am ጀምሮ እስከ 5:00 pm ጥሪዎችን የሚቀበል ስለሆነ በመጀመሪያው የትምህርት ሳምንት ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። ስጋቶች ወይም በአውቶቡስ ላይ ወይም በአውቶቡስ ማቆሚያዎች ላይ ችግሮች ካሉና መፍትሄ ለመሻት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ሲኖሩ MCPS የትራንስፖርት ሰራተኞች ቤተሰቦችን ለመርዳት ዝግጁ ናቸው። ይህንን አገልግሎት ለማግኘት 240-740-7790 ይደውሉ።
(ስልክ ቁጥሮችን ጨምሮ) በቀጥታ ከት/ቤት አውቶቡስ መናኸሪያ/ዴፖ ጋር መገናኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን መመሪያ ይከተሉ።
የእርስዎን አካባቢ ከሚያገለግለው ዴፖ ጋር ለማገናኘት የአውቶቡስ መስመሮች ቁጥር አላቸው። ወደ ዴፖ በቀጥታ መደወል ይችላሉ።
|
ከሚፈልጉት የአውቶቡስ መናኸሪያ ጋር ከተገናኙ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር እና ቤተሰብዎን ለመደገፍ ዝግጁ ናቸው።
መልካም የትምህርት አመት እንዲሆንል ከሁሉም ቤተሰባችን ጋር አብረን ለመስራት በጉጉት እንጠባበቃለን።
M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools
መገልገያዎች
ስለ ደህንነት እና የትምህርት ቤት አውቶቡስ አጠቃቀም ህጎች ለቤተሰቦች እና ለአሽከርካሪዎች ምክር
እባክዎን 2024-2025 የትምህርት አመት ስንጀምር፤ ስለትምህርት ቤት አውቶቡስ የጉዞ ደህንነት አስፈላጊነት ህዝቡን ማስተማር የምንቀጥል ስለሆነ ይህንን መረጃ ለቤተሰቦችዎም ያካፍሉ።
"Zeal’s" የአውቶቡስ ደህንነት ምክሮች
"Zeal" የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (MCDOT) የትራፊክ ደህንነት ዜብራ፣ ከተወሰኑ የት/ቤት አውቶቡስ ደህንነት ምክሮች ጋር እዚህ ያገኛሉ! ይህ ቪዲኦ የተሠራው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ነው። ሁሉም ተሳፍረዋል!
ደህንነቱ የተጠበቀ ወደ ትምህርት ቤቶች የሚያደርስ የጉዞ መስመር (MCDOT)
ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (MCDOT) ደህንነቱ የተጠበቀ ወደ ትምህርት ቤት የማጓጓዝ መርሃ ግብር የበለጠ ለማወቅ ወይም ወደ ትምህርት ቤት በእግር ወይም በብስክሌት ለሚጓዙ ተማሪዎች የመጓጓዣ ደህንነትን በማሻሻል ላይ ያተኩራል።
ለት/ቤት አውቶቡስ ቅድሚያ መስጠትን ያክብሩ
የልጆችን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲረዳ ስለ አውቶቡስ ካሜራዎች ከ MCPS ይማሩ!
ቀይ ሲያበራ ያቁሙ - ለትምህርት ቤት አውቶቡሶች መቼ ማቆም እንዳለብዎት ማወቅ - የሜሪላንድ ራዕይ በመኪና አደጋ ምንም ልጅ እንዳይሞት ነው/Zero Deaths Maryland & Vision Zero
በትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓዝ ለትምህርት ቤት ልጆች በጣም ደህንነቱ የተጠበቀ የመጓጓዣ ዘዴ ቢሆንም፣ የት/ቤት አውቶብስን ለማለፍ ክፍት የሚሆነው መቼ እንደሆነ እና እንዳልሆነ እውነቱን እንወቅ፣ መቼ ፍጥነት መቀነስ እንዳለብዎት፣እና ከአውቶቡሱ ምን ያህል ርቀው ማቆም አለብዎት ይወቁ።
የሜሪላንድ የትምህርት ቤት አውቶቡስ ህጎች እና ደህንነትን የሚመለከቱ ምክሮች
ለልጆች ወደ ትምህርት ቤት ለመድረስ የትምህርት ቤት አውቶቡሶች በጣም አስተማማኝ መንገድ ናቸው። ቢሆንም ህጻናት በተለይ ከአውቶብስ ሲወጡ እና ሲወርዱ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። በሜሪላንድ፣ ህጻናት የሚሻገሩባቸውን መንገዶች በደህና እንዲሄዱ ለመርዳት አሽከርካሪዎች የአውቶቡስ ደህንነትን እንዲጠብቁ ህጎች ተዘጋጅተዋል።
የሚያሽከረክቱትን መኪና አቁመው ለትምህርት ቤት አውቶቡሶች ቅድሚያ ይስጡ፡ በሜሪላንድ ውስጥ ያሉት ህጎች ምንድን ይላሉ?
የሜሪላንድ ስቴት ፖሊስ እና የሜሪላንድ የትምህርት ቤት ደህንነት ማእከል አሽከርካሪዎች ለትምህርት ቤት አውቶቡሶች ቅድሚያ በመስጠት እንዲቆሙ ያሳስባሉ።
በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ትኩረት ይስጡ፣ በተለይም በትምህርት ቤት ዞኖች በትምህርት ቀናት የትምህርት ቤት አውቶቡሶች በመንገድ ላይ ይሆናሉ።
አውቶቡስ ሲቆም እርስዎም ተሽከርካሪዎን ያቁሙ። የት/ቤት አውቶቡስ ቀይ መብራቶቹ ብልጭ ድርግም እያሉ በሚያበሩበት ጊዜ አቋርጦ ማለፍ ህገወጥ ነው።
የትምህርት ቤት አውቶቡስ ቢጫ መብራቶችን በሚያበራበት ጊዜ ለማቆም ይዘጋጁ እና በእነዚህ ጊዜያት ተማሪዎች ወደ አውቶቡሱ መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ይጠንቀቁ
በሁሉም እድሜ ያሉ ተማሪዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ ይገባሉ ስለዚህ፣ ላልተጠበቁ ክስተቶች ይዘጋጁ እና ሁልጊዜ ከትምህርት አውቶቡሶች ተገቢውን ርቀት ይጠብቁ።
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org