ስለ ተማሪዎች ንግግር እና አገላለጽ የተሻሻለ መመሪያ

ሰፕቴምበር 27, 2024

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች እና ተማሪዎች

ስለ ትምህርት አመቱ ጥሩ ጅማሮ እናመሰግናለን!

ማህበረሰባችን በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ፈታኝ የሆኑ ስሜታዊ ውይይቶች የሚነሱበት ሁኔታ ውስጥ እየገባን ስለሆነ መላው ማህበረሰባችን—ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣እና ሰራተኞች—እነዚህን ጊዜታት በአንድነት ለመቃኘት የሚያስችለን መመሪያ እና ስልት እንዳላቸው ማረጋገጥ እንፈልጋለን። ስለ መጪው ሀገራዊ ምርጫ፣ ኦክቶበር 7 የተፈፀመው ጥቃት የመጀመሪያው አመት፣ እና በመካሄድ ላይ ስላሉት ግጭቶች፣ሊነሱ ስለሚችሉ በዚህ ምክንያት ለሚንፀባረቁ ንግግሮች እና ስሜቶች ምላሽ ለመስጠት ከወዲሁ መዘጋጀታችን አስፈላጊ ነው። 

በትምህርት ቤቶቻችን ለተማሪዎቻችን ምርጥ የመማር ማስተማር ምህዳር ለመፍጠር፥ የመማሪያ አካባቢያቸው ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹ እና ሁሉን ያካተተ/አቃፊ መሆን አለበት። የትምህርት ባለሙያዎች እንደመሆናችን መጠን፥ በተለይም በአስቸጋሪ ጊዜያት ተማሪዎቻችን በጥልቀት የሚያገናዝቡ እና አወንታዊ አገላለጾችን በመጠቀም ተማሪዎችን በአክብሮት፣በመረጃ ላይ የተመሰረተ ንግግር ላይ እንዲያተኩሩ ለማበረታታት እንጥራለን።

የጥላቻ እና የተዛባ አመለካከት ክስተቶች ሲያጋጥሙ ምላሽ ስለመስጠት አዲሶቹ የመገናኛ/የኮሙኒኬሽን ዘይቤዎች የተተለሙት ከመረጃ ልውውጥ ዘመቻ ጋር ተያይዞ ከማህበረሰባችን አባላት የተገኙ አስተያየቶችንና እና ግብአቶችን መሠረት በማድረግ የተቀረጹ ናቸው። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የተማሪዎችን ንግግር እና አገላለጽ በመምራት ረገድ ሁላችንም የምንከተለው ወጥነት ያለው ተመሳሳይ መመሪያ መሆኑን ለማረጋገጥ የትምህርት ቤት ሰራተኞች እና አመራሮች እነዚህ ተመሳሳይ ግብዓቶች ደርሷቸዋል።  

ትምህርት ቤቶቻችንን ለሁሉም ሰው የሚሆን ምቹ እና ሁሉን አቀፍ ቦታ ለማድረግ ስለሚያደርጉት ትብብር እናመሰግናለን።

ከአክብሮት ጋር

Thomas W. Taylor, Ed.D., M.B.A.
Superintendent

ማወቅ ያለብዎት የተማሪዎች ንግግር እና አገላለጽ መመሪያ።

የጥላቻ እና የተንጋደደ አመለካከትን ለመቀነስ እና ለመፍታት የሚረዱ መገልገያዎች

ከፍተኛ ጥራት ያለው ሥርዓተ ትምህርት/ከሪኩለም


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org