ከኦክቶበር 21 እስከ 26 የሚካሄድ የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት

MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች የሳይኮሎጂስቶች ማህበር ለወጣቶች እና ለቤተሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እንዲሰሙ እድል ለመስጠት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ከኦክቶበር 21 እስከ 26 ያስተናግዳሉ። የአእምሮ ጤና ሪሶርስ አውደ ርእይ እና የተማሪዎች መድረክ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 26 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 2 p.m. ይካሄዳል። አድራሻው በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ Seneca Valley High School,19401 Crystal Rock Drive in Germantown። ይህ ዝግጅት ነጻ ስለሆነ፤ ከበርካታ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መጓጓዣ ይኖራል። 

ዝግጅቱ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን። እና ሰራተኞችን ያካተተ ሲሆን፤ MCPS እና የማህበረሰብ አጋሮች ስለአእምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃዎችን መለዋወጥ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ወጣቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ በተማሪዎች-የሚመራ መድረክም ይካሄዳል። በሪሶርስ (መገልገያዎች) አውደ ርእይ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ሊመዘገብላቸው ይችላል። ለበለጠ መረጃ፣የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት ድረ ገጽ ይጎብኙ።

ዋና ተናጋሪው ቨርጂኒያ የዲስትሪክት አስተዳዳሪ የሆኑ ዶ/ር ቻርልስ ኤ. ባረት/Charles A. Barrett፣Ph.D., NCSP ሲሆኑ ቀደም ሲል በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 13 ዓመታት የት/ቤት ሳይኮሎጂስት በመሆን ማገልገላቸው ይታወቃል። በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የወደፊት የትምህርት ቤት የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን/ሳይኮሎጂስቶችን በማሠልጠን በተባባሪ ሌክቸረርነት ያገለግላሉ። የዋናው ተናጋሪ መልእክት እና የተማሪዎች መድረክ ከጠዋቱ 10:30 a.m. እስከ 12:30 p.m. ይካሄዳል።

2024 የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት


በዚህ የኢሜል አድራሻASKMCPS@mcpsmd.org ይላኩልን፦