በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የት/ቤቶችን መዘጋት ተከትሎ፥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት አመት በአንድ ቀን ተራዝሟል።

ጃንዋሪ ለማህበረሰባችን ፈታኝ ወር ነበር፥ ከፍተኛ ቅዝቃዜ፣ በረዷማ የአየር ሁኔታ፣ የሚጥል በረዶ እና የሚያንሸራትት የበረዶ ሁኔታ በእለት ተእለት ተግባራችን ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች በሚጓዙበት ጊዜ ጥንቃቄ በማድረግ እና ቅዝቃዜን በመቋቋም እነዚህን አስቸጋሪ ሳምንታት በጽናት ተወጥተዋል። በመጪዎቹ ቀናት ምቹ የሙቀት ቀናት እንደሚሆኑ በጉጉት እንጠብቃለን፤ ነገር ግን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ መዘጋት ምክንያት በትምህርት ቤት ካለንደር/የቀን መቁጠሪያ ላይ አስፈላጊ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርብናል።

ሰኞ፣ ጃንዋሪ 6, 2025፣ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 7, 2025 እና ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 8, 2025 ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ተዘግተው ነበር። 2024–2025 የትምህርት አመት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር 182 የትምህርት ቀናትን ያካትታል፣ ይህም ከሜሪላንድ ስቴት 180 የትምህርት ቀናት ዝቅተኛ መስፈርት በሁለት ቀን ይበልጣል። በዚህ መሠረት ጃንዋሪ 6 እና ጃንዋሪ 7 የተዘጉት ቀናት የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያችንን አይነኩም።

ሆኖም ጃንዋሪ 8 የተዘጋበትን ቀን ለማካካስ በካለንደር ላይ ከተያዘው የመጠባበቂያ ቀናት አንዱን መጠቀም ይኖርብናል። የትምህርት አመቱ በአንድ ቀን ይራዘማል፣ ስለዚህ የተማሪዎች የመጨረሻው የትምህርት ቀን ሰኞ፣ ጁን 16, 2025 ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ይሆናል። በተጨማሪም፥ ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ተብሎ ቀን መቁጠሪያ ላይ የተያዘው አርብ፣ ጁን 13, 2025 አሁን ለተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቀን ይሆናል።

ት/ቤቶች መዘጋት ያለባቸው ተጨማሪ ቀኖች ከኖሩ፣ ተጨማሪ የት/ቤት ቀን መቁጠሪያ ማስተካከያዎች ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፣ MCPS ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት በስቴት ከተመደበው 180 የትምህርት ቀናት ጋር እንዲተካከል ሊጠይቅ ይችላል። ነገር ግን እንዲተካከል መጠየቅ የሚቻለው፣ MCPS የነበረውን የትምህርት ቀን መቁጠሪያ ማስተካከልን ጨምሮ የተጓደለውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የተደረጉትን ጥረቶች ማሳየት አለበት።

በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ወቅት የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ት/ቤቶችን እና ቢሮዎችን የመዝጋት ውሳኔዎች ይደረጋሉ። በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት እንደገና የት/ቤት ቀን መቁጠሪያ ለውጦችን በሚያስከትል ሁኔታ ት/ቤቶች የሚዘጉ ከሆነ በእኛ በኩል በፍጥነት ለማህበረሰቡ እናሳውቃለን።

የተሻሻለውን መደበኛ የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር እዚህ ይመልከቱ። ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ ለሚከተለው አርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለውጥ የለውም።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org