ቀኑን ያስታውሱ!

የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን የድንበር ጥናት በሚመለከት በመጪዎቹ ጊዜያት የማህበረሰብ የመረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ይደረጋሉ
ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ
የቻርለስ ዊ. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመክፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የድንበር ጥናቶችን በሚመለከት ከማህበረሰቡ ጋር በሚደረጉ የመረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
በነዚህ የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜዎች ስለ ድንበር ጥናት ወሰን፣ የአፈጻፀም ሂደት፣ እና የወደፊት የሕብረተሰብ ተሳትፎ እድሎችን በሚመለከት ጠቃሚ መግለጫዎች ይሰጣሉ።
የቻርለስ ዊ. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመክፈት የድንበር ጥናት

  • ቨርቹዋል ክፍለጊዜ: እሮብ፣ ኤፕሪል 2, 2025 | 6:00 – 8:00 PM
    (የስብሰባው ክፍለ ጊዜ አገናኝ/ሊንክ– ሪኮርድ ተደርጎ/ተመዝግቦ ለህዝብ ይቀርባል።)
  • በአካል የሚካሄደው ክፍለ ጊዜ: ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 8, 2025 | 6:00 – 8:00 PM በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኦዲቶሪየም ላይ ይደረጋል

የክራወን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈቻ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የወሰን ጥናት

  • ቨርቹዋል ክፍለ ጊዜ: ሰኞ፣ ኤፕሪል 7, 2025 | 6:00 – 8:00 PM
    (የስብሰባ አገናኝ/ሊንክ – ክፍለ ጊዜ ሪኮርድ ተደርጎ/ተመዝግቦ ለህዝብ ይቀርባል።)
  • በአካል የሚደረግ ክፍለ ጊዜ: እሮብ፣ ኤፕሪል 9, 2025 | 6:00 – 8:00 PM በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኦዲቶሪየም ላይ ይደረጋል

በነዚህ የማህበረሰብ ውይይት ክፍለ ጊዜዎች የሚከተሉትን ጉዳዮች የሚመለከቱ መረጃዎች ይሰጣሉ፦

  • የድንበር ጥናቶ ወሰን እና የጊዜ ገደብ
  • አፈጻፀም ሂደት እና ከትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች ጋር ማጣጣም
  • በሂደቱ ላይ የተሳትፎ እድሎች እንዴት እንደሚከናወኑ
  • የመረጃ ምንጮች/መገልገያዎች እና ተደራሽነት
  • ወደፊት የማህበረሰብ ግብአት እድሎች

ምዝገባ አስፈላጊ ባይሆንም፤ ለመዘጋጀት እንዲረዳን የእርስዎን ምላሽ RSVP ቢልኩልን እናደንቃለን። [RSVP Link]
የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ ይህንን በይነመረብ ይጎብኙ፦ MCPS የድንበር ጥናቶች ድረ-ገጽ/MCPS Boundary Studies Webpage
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org