ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ

ተማሪዎች የግል ሞባይል መሳሪያዎችን - ሞባይል ስልኮችን፣ e-readersን፣ ስማርት ሰዓቶችን፣ ታብሌቶችን፣ በተጠቃሚው ሰውነት ላይ ሊደረግ የሚችል ቴክኖሎጂን፣ ቪዲዮ እና ድምጽ መቅጃዎችን/መቅረጫዎችን እና ጨዋታ/ጌም መጫወቻ መሳሪያዎችን ጨምሮ- በትምህርት ቤት ንብረት ላይ እና በMCPS ስፖንሰር በሚደረጉ ዝግጅቶች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የሚገልጸውን የተሻሻለው የግል የሞባይል መሳሪያዎች/Personal Mobile Devices ደንብ ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ማጋራት እንፈልጋለን ። እነዚህ ደንቦች ከ2025-2026 የትምህርት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ።

ትንሽ ጊዜ በስልክ ላይ ማሳለፍ፣ የበለጠ ጊዜ በትምህርት ማሳለፍ ማለት ነው

በትምህርት ክፍለ ጊዜ ወቅት የስልክ መጠቀምን መገደብ ተማሪዎች እንዲያተኩሩ፣ እንዲሳተፉ እና መረጃን የበለጠ መያዝ እንዲችል ይረዳል። ሌሎች ጠቀሜታዎቹ የሚያካትቱትም፦

  • አነስተኛ ትኩረት የሚሰርቁ ነገሮች = የተሻለ ትምህርት እና ተሳትፎ
  • መምህራን መቋረጦች ሳይኖሩ ማስተማር ይችላሉ
  • ስክሪን ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ መቀነስ ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነትን እንደሚያጎለብት ጥናቶች ያሳያሉ።
  • የመማሪያ ክፍሎች የበለጠ ምቹ ሆነው ይካሄዳሉ
  • ሁሉም ሰው ከተሻለ መከባበር፣ ትኩረት ካለበት አካባቢ ተጠቃሚ ይሆናል

ዋናው ነገር፦ትንሽ ጊዜ በስልክ ላይ ማሳለፍ፣ የበለጠ ጊዜ በትምህርት ማሳለፍ ማለት ነው።

ቤተሰቦች እና ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸው ነገር፦

  • ከት/ቤት በፊት እና በኋላ፦ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ያሉ ተማሪዎችን የግል ሞባይል መሳሪያዎቻቸውን የትምህርት ቀን ከመጀመሩ በፊት እና ከአለቀ በኋላ መጠቀም ይችላሉ።

  • አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች፦ በትምህርት ቀን ወቅት—የትምህርት ጊዜ፣ ምሳ ሰአት እና በክፍለ ጊዜያት መካከል ያሉትን ሽግግሮች ጨምሮ—ተማሪዎች የግል መሳሪያዎቻቸውን ማጥፋት እና ማስቀመጫ ቦታ ማድረግ አለባቸው።

  • ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፦ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የግል መሳሪያዎቻቸውን በምሳ እና በትምህርት ክፍለ ጊዜያት መካከል መጠቀም ይችላሉ፣ ትምህርት በሚሰጥበት ወቅት ግን መጠቀም አይችሉም።

  • በት/ቤት ባሶች ላይ፦ ተማሪዎች በMCPS አውቶቡሶች በሚጓጓዙበት ወቅት መሳሪያዎቻቸውን ለመጠቀም ተፈቅዶላቸዋል።

  • የተማሪዎች ሀላፊነት፦ ተማሪዎች መሳሪያዎቻቸውን ሀላፊነት ባለው መንገድ መገልገል ይጠበቅባቸውል፣ በማይፈቀድበት ወቅት በማጥፋት እና ከእይታ አርቀው በማስቀመጥ።

  • ዲሲፕሊን እና የሚጠበቁ ነገሮች፦ ተማሪዎች መሳሪያዎቻቸውን ያላግባብ ከተጠቀሙ፣ በተሻሻለው የተማሪ ስነ-ምግባር ኮድ ላይ በዝርዝር በተቀመጠው መሰረት እርምጃዎች ደረጃውን በጠበቀ አካሄድ ይከተላሉ፣ ይህም በሰመር/በጋ ወቅት ይፋ ይሆናል፣ እና የሚያተኩረውም በትምህርት እና በተጠያቂነት ላይ ነው። በ MCPS የተማሪ ስነ-ምግባር ኮድ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ከተማሪ ስነ-ምግባር የሚጠበቁ ነገሮችን ግልፅ ያደርጋሉ እና በድጋሚ ያስቀምጣሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። የሞባይል ስልክን መጠቀም ትምህርትን የሚደግፍ ከሆነ ርዕሰ መምህራን በትምህርት ጊዜ በተወሰነ መልኩ የሞባይል ስልክ መጠቀምን የመፍቀድ ስልጣን አላቸው።

  • የህክምና እና የትምህርት/የመማር ማመቻቸቶች፡የግል ተንቀሳቃሽ መሳሪያን መጠቀምን በሚፈቅደው በ 504 ወይም በግላዊ የትምህርት እቅድ (IEP) ላይ በተቀመጠው መሰረት ተማሪዎች መሳሪያዎቹን ማግኘታቸውን/መጠቀማቸውን ይቀጥላሉ።

ይህ የተሻሻለው ደንብ የሚያንፀባርቀው የMCPS የትምህርት ተሞክሮን ለመፍጠር ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነትን ነው፣ ይህም ተማሪዎች ማደግ የሚችሉበት ነው—የቴክኖሎጂን ጠቀሜታዎች በመማሪያ ክፍል ውስጥ ከሚያስፈልገው ትኩረት፣ መከባበር እና ትስስር ጋር ያመጣጥናል።

ለሁሉም ተማሪዎች መልካም እና ውጤታም ያለው የትምህርት አካባቢን ለመደገፍ ለምታደርጉት ቀጣይነት ያለው አጋርነታችሁ ምስጋና እናቀርባለን።


በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org