ስለ አደገኛ "ቲክቶክ ክሮምቡክ" አጠቃቀም ተግዳሮት - ከልጅዎ ጋር ይነጋገሩ

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ይህን ማሳሰቢያ የጻፍንልዎት በመላ አገሪቱ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው የማህበራዊ ሚድያ በዋነኛነት TikTok፣ Chromebooks እያስከተለ ስላለው አደገኛ አዝማሚያ ለማስገንዘብ ነው። "TikTok Chromebook Challenge" በመባል የሚታወቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያተሠራጨ የሚገኝ አዝማሚያ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት የተሰጣቸውብ ክሮምቡክስ/"Chromebooks" አላግባብ እንዲጠቀሙ ወይም ሆን ብለው እንዲያበላሹ ያበረታታቸዋል። ይህ “Chromebook Challenge” ድርጊቱ ተማሪዎች ሆን ብለው ብረት ነክ ነገር ወይም እርሳስ ባትሪ መሰኪያው ላይ ወይም USB ማስገቢያ ላይ በመክተት ለትምህርታቸው የሚገለገሉበትን ክሮምቡክ እንዲበላሽ ወይም እንዲቃጠል እንዲያደርጉ ያበረታታል።

ክሮምቡክስ/Chromebooks ለማስጠገን የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ መሆኑን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። የሀብት (የበጀት)-ውስንነት ባለበት ወቅት፣ እያንዳንዱ ዶላር ትርጉም ይኖረዋል። ስለዚህ፣ የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ይህንን መረጃ ለእርስዎ ማጋራት እና ትብብርዎን መጠየቅ አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማናል። ስለ ቲክቶክ ክሮምቡክ ቻለንጅ "TikTok Chromebook Challenge" ከልጅዎ ጋር ግልጽ እና ጥብቅ ውይይት በማድረግ ጥንቃቄ የጎደለው የክሮምቡክ አጠቃቀም ስለሚያስከትለው ጉዳት እንዲያስረዱ እናበረታታዎታለን። እባክዎን ለልጆዎ የሚከተለውን ያስታው(ሷ)ሱት፦

  • ከትምህርት ቤት የተሰጡ Chromebooks ፋይዳቢስ መሳሪያዎች አለመሆናቸውን እና ለልጅዎ ትምህርት ጉልህ አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ጠቃሚ የትምህርት መሳሪያዎች መሆናቸውን፥ በጥንቃቄ መያዝና መጠቀም በጣም አስፈላጊ መሆኑን፥
  • ጎጂ በሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶች ላይ መሳተፍ ደህንነቱ ያልተጠበቀ እና ከባድ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል መንገር በጣም አስፈላጊ ነው።
  • የትምህርት ቤትን ንብረት፣ እኩዮችን እና የትምህርት ቦታዎችን በአክብሮት መያዝና መጠቀም የግለሰብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም የሚመለከት እና በጥንቃቄ ልንጠብቀው የሚገባ የጋራ ኃላፊነት ነው።
  • ሁሉም የክሮምቡክ "Chromebook" ብልሽት በጥልቀት ይመረመራል፣እና የሚያስከትለው መዘዝ ካለ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎች ስነምግባር ደንብ መሰረት ተገቢ እርምጃ ይወሰዳል። እባኮትን ለተማሪ የተሰጡ የትምህርት መርጃዎች ሆን ተብሎ ከተበላሹ ቤተሰቦች ለጥገና ወይም የመተኪያ ወጪዎችን ለመሸፈን ሃላፊነት የሚወስዱ መሆኑን ልብ ይበሉ።

ለተማሪዎቻችን በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጭ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ኃላፊነት የተሞላበት፣ እና አክብሮት የሠፈነበት ባህሪ እንዲኖራቸው ለማበረታታት አብረን እንድንሰራ የሚያደርጉትን እገዛ እናደንቃለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ


በዚህ አድራሻ ኢሜል አድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org