ማክሰኞ፣ ጁን 10, 2025፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ MCPS የወደፊት ዝግጁነትየተሰኘውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2025–2030 ስትራቴጂክ እቅድ በአንድ ድምፅ ተቀብሏል። የስትራቴጂክ እቅዱ ስለ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ስኬት ግልፅ ራዕይ ያለው አስፈላጊ የሆነ አዲስ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል። MCPS መሪ እንጂ ተከታይ መሆን የለበትም።
ስልታዊ እቅዱ ተማሪዎች ለወደፊታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እውቀት፣ ክህሎት፣ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው በዲስትሪክቱ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። የዲስትሪክቱ አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ MCPS የት መሆን እንዳለበት እና እንዴት እዚያ እንደሚደርስ ግልጽ የሆነ ፍኖተ ካርታ/አቅጣጫ ይጠቁማል። እቅዱ ለስኬታማ የትምህርት ሥርዓት አራት ዓላማዎችን ያነገበ ሲሆን፥ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ የእድገት ክንውንን ለመከታተል የሚያስችሉ መለኪያዎችንም ይዟል። የስትራቴጂክ ዕቅዱ ተማሪዎች ለወደፊታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ክህሎቶች የሚገልጽ የተማሪዎች የወደፊት ዝግጁነት ማዕቀፍ ከማዘጋጀቱም በላይ እነዚህ ችሎታዎች የሚገነቡት ጥልቅ አስተሳሰብን በማዳበር፣ የግንኙነት ችሎታን ማበልፀግ፣ ተባብሮ በመሥራት፣ በፈጠራ፣ በማህበረሰባዊ አስተዋጽኦ እና ደህንነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።
የአካዳሚክ ምጡቅነት – ሁሉም ተማሪዎች ከፍተኛ የትምህርት ስኬት እና እድገት ይኖራቸዋል።
የተዘጋጁ የወደፊት ተመራቂዎች – ሁሉም ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ ትርጉም ያለው ውጤት እንደሚኖራቸው ያረጋግጣል።
አዎንታዊነት፣ ደህንነት፣ እና ውጤታማነት – በአዎንታዊ የትምህርት አውድ እና በውጤታማ ስራዎች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹ፣ እና አካታች የትምህርት እና የስራ አካባቢ በመፍጠር ላይ ያተኩራል።
ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ ብዝሃነት ያለው የሥራ ግብረ ኃይል – ሁሉም ሰራተኞች ውጤማ እንዲሆኑ መደገፍ እና መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች በሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ሪፖርት ካርድ ላይ አራት ኮከቦችን ወይም ከዚያ በላይ ሲያገኙ 100% ስኬታማ መሆናችንን እናረጋግጣለን።
በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ካሉ ተማሪዎች፣ ብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን የሚያገኙ ተማሪዎች፣ የሂስፓኒክ/ላቲኖ ተማሪዎች፣ እና ጥቁር/አፍሪካዊ አሜሪካውያን ተማሪዎች መካከል የተማሪዎች የብቃት ደረጃ 50% ያድጋል/ይጨምራል።
በሁሉም የሪፖርት ማቅረቢያ ምድቦች በየዘመኑ በሚለዋወጠው አለም ውስጥ ብቁ ሆነው ለመገኘት የሚያስፈልጉትን ዕውቀት፣ ክህሎት፣ እና ልምዶችን በመቅሰም በዓመት እስከ 95% የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ይመረቃሉ።
ይህ እቅድ በሁለት ደረጃዎች ይከፈላል። ይህን እቅድ በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት እና የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ሴፕተምበር ላይ ተጨማሪ የአተገባበር ስልቶችን እና እርምጃዎችን እናጋራለን።
ለተማሪዎች ስኬት ቤተሰቦች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፤ ስለሆነም በዚህ ጉዞ ላይ እርስዎንም ማሳተፍ እና መረጃዎችን በማጋራት እንቀጥላለን።
እያንዳንዱ ልጅ ለወደፊት ዝግጁ እንዲሆን ለመርዳት አጋራችን ስለሆኑ እናመሰግናለን።
መርጃዎች/ሪሶርሶች፦ ስለ"MCPS Future Ready" የተሰኘ የ 2025–2030 ስትራቴጂክ እቅድ የበለጠ ለማንበብ በስላይድ ተቀርጾየቀረበውን ይመልከቱ።
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org