አመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ ኦገስት 24 ይካሄዳል
MCPS ዓመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ቅዳሜ፣ ኦገስት 24 ቀን 10፡00 a.m. እስከ 1 p.m. በዊተን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ያስተናግዳል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤት ስርዓት እና ስለ ካውንቲ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በቤተሰብ እንቅስቃሴዎች፣ በሙዚቃ፣ በመዝናኛ ዝግጅቶች ይደሰታሉ፤ስጦታዎችን ያገኛሉ። የዚህ አመት አዘጋጆች KID ሙዚየም፣ ግሌንስቶን ሙዚየም፣ ኢማጅኔሽን ስቴጅ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ እና ሌሎችንም ያካትታል። የልጆች ክትባት የሚሰጥበት ክሊኒክ ይኖራል
ከጠዋቱ 9፡00 a.m. ጀምሮ ከስድስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግጅቱ ወደሚካሄድበት ቦታ ድረስ MCPS ነጻ መጓጓዣዎችን ያቀርባል። ዊተን የሚገኘው ዌስትፊልድ አድራሻ የሚከተለው ነው፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የሚቆሙባቸውን ቦታዎች እና የመነሻ እና የመድረሻ ጊዜዎችን ለማየት የአውደ ርዕይ ዝግጅት ድረ-ገጽ ይጎብኙ።
ለነፃ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች (FARMS) ለማመልከት አሁን ክፍት ነው
ለ 2024–2025 የትምህርት አመት የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች (FARMS) ማመልከቻ አሁን ማቅረብ ይቻላል።
በማህበረሰብ ብቁነት አቅርቦት (CEP) የሚሳተፉ በትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች ነጻ ምግብ ለማግኘት ብቁ ስለሆኑ አሁን FARMS ማመልከት አያስፈልጋቸውም። CEP ያልታቀፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በቤተሰብ ብዛት እና የገቢ መጠን ላይ በመመስረት ለነጻ ወይም ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪ፥ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ፕሮግራም (SNAP)፣ ጊዜያዊ የገንዘብ ድጋፍ (TCA)፣ ወይም የሜዲኬይድ ጥቅማ ጥቅሞችን እያገኙ ከሆነ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
ባለፈው አመት ምንም እንኳን ልጃቸው ብቁ ቢሆንም/ብትሆንም ቤተሰቦች በየትምህርት አመቱ FARMS ማመልከቻቸውን ማደስ ይጠበቅባቸዋል።
ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በነጻ ይመገባሉ። ለማመልከት MySchoolApps.com ይጎብኙ (ተተርጉሞ የተዘጋጀ ቅጽ ይኖራል)።
እስከ ኦገስት አጋማሽ ድረስ የሠመር ምግቦችን ያገኛሉ
ዕድሜያቸው እስከ 18 ዓመት የሆኑ ልጆች ጤናማ እና ገንቢ የምሳ ምግብ ለማግኘት ከሰኞ እስከ አርብ ወደ የትኛውም የሠመር ምግብ የሚታደልባቸው ቦታዎች መጥተው መመገብ ይችላሉ። የሠመር ምግብ ፕሮግራም እስከ 18 አመት ለሆኑ ልጆች ያለ ምንም ወጪ የተመጣጠነ ምግብ ለማቅረብ የተነደፈ ፕሮግራም ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሠመር ምግብ ፕሮግራም የተነደፈው ትምህርት ቤቶች ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ “የአመጋገብ ክፍተትን” በመሙላት ረገድ ድልድይ እንዲሆን ነው።
2024 የሠመር ምግብ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ጣቢያዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ። ምንም ቀጠሮ አያስፈልግም። ምግቦቹን በቦታው ላይ መብላት አለባቸው።
የሠመር ምግቦች ዝርዝር፦
ሠመር 2024 በቦርሳ የተዘጋጁ ምግቦች የሚቀርቡበት ጣቢያዎች ዝርዝር
የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሠመር ፕሮግራም ድረ ገጽ ይጎብኙ።
ነፃ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን ከ "Annual Drive for Supplies" ይውሰዱ
አመታዊው "Drive for Spplies" የት/ቤት ቁሳቁሶች ስርጭት በፓርክላንድ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Parkland Middle School) አርብ፣ ጁላይ 19 ከጥዋት 9 a.m.–2 p.m.፣ ቁሳቁሶቹ እስከሚያልቁ ድረስ ይከናወናል።
የሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች አዳዲስ እና ያገለገሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን መጥተው መውሰድ ይችላሉ። ቁሳቁሶቹ የተገኙት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሰራተኞች በትምህርት አመቱ መጨረሻ ላይ መቆለፊያ ሳጥኖቻቸውን/ሎከሮቻቸውን፣ጠረጴዛዎችን እና ቁምሳጥኖችን ሲያፀዱ በልግስና ስለሰጡ የተሰበሰቡ ናቸው። አድራሻው የሚከተለው ነው፦ Parkland is located at 4610 West Frankfort Drive in Rockville.
የትምህርት ቦርድ ለስነምግባር ፓነል (Ethics Panel) ክፍት የስራ ቦታ አመልካቾችን ይፈልጋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አምስት አባላት ባሉት የስነምግባር ፓነል ክፍት የስራ መደብ አመልካቾችን ይፈልጋል። ክፍት የሥራ ቦታው እስከ ጁን 30 ቀን 2027 ድረስ ለሚቆይ የአገልግሎት ጊዜ ነው። አባላት የሚያገለግሉት በነፃ ነው። በቦርድ ፖሊሲ BBB ሥነምግባር ላይ እንደተገለጸው፣ ከፓነሉ ኃላፊነቶች መካከል፡ የፋይናንስ መግለጫ ቅጾችን ማጽደቅ፣ የትምህርት ቦርድን የሥነ-ምግባር ፖሊሲ መተርጎም እና አተገባበሩን በሚመለከት ምክረሃሳብ መስጠት፣ እና የስነምግባር ጥሰትን በሚመለከት በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ የቅሬታ ሰሚ ችሎቶችን ማካሄድ ይገኝበታል።
ሠመር የኮሌጅ ዝግጁነት አውደጥናቶች (ወርክሾፖች) 2024
MCPS በሠመር ወቅት ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች ስለ ኮሌጅ ዝግጁነት በነጻ አውደ ጥናቶችን ይሰጣል። የሚከተሉት በርካታ ዝርዝሮች ያሉበት፦ የኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት፣ SAT እና ACT፣ የኮሌጅ አትሌቲክስ፣ የጥናት እና የጊዜ አጠቃቀም ጭምር ቨርቹዋል እና በአካል የሚካሄዱ ወርክሾፖችን ዝርዝር ይመልከቱ።
ለተጨማሪ መረጃ የኮሌጅ እና የሙያ ስራ መስክ ድረገጽ ይጎብኙ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትራንስፖርት ቡድንን ይቀላቀሉ!
MCPS ሐሙስ፣ ጁላይ 25 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m.–1 p.m. ለአውቶቡስ ሾፌርነት፣ ለአውቶቡስ ረዳትነት እና ለመካኒክነት ለስራ ፈላጊዎች አውደ ርዕይ ያዘጋጃል። አውደ ርዕዩ የሚካሄደው በሼዲ ግሮቭ ትራንስፖርት ዴፖ ሲሆን አድራሻው የሚከተለው ነው፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
"GIVE Backpacks" ዘመቻ እየተካሄደ ስለሆነ ዛሬውኑ ይለግሱ
13ኛው አመታዊ GIVE BACKpacks ዘመቻ በመካሄድ ላይ ስለሆነ፥ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በጀርባ የሚያዝ የደብተር/የመጻህፍት ቦርሳዎችን እና የት/ቤት ቁሳቁሶችን በመግዛት የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው። እስከ $20 ዶላር ቢለግሱ ወረቀቶች/ደብተሮች፣ እርሳሶች፣ እስክሪብቶዎች፣ ከለሮች፣ የእርሳስ መቅረጫ፣ የደብተርና መጽሐፍት ማያያዣዎች፣ እና ፎልደሮችን ጭምር የመማሪያ ቁሳቁስ በተማሪ ቦርሳ ሞልተው መስጠት ይችላሉ።
መልካም ዜና
አስራ ሶስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በኮሌጅ ስፖንሰር የሚደረግ ብሄራዊ ስኮላርሺፕ አግኝተዋል
ተጨማሪ 13 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከብሔራዊ ሜሪት ስኮላርሺፕ ኮርፖሬሽን በተደረገ የመጨረሻው ዙር ሽልማት በኮሌጅ እና በዩኒቨርሲቲ የሚደገፍ ብሄራዊ ስኮላርሺፕ አግኝተዋል። ይበልጥ ያንብቡ።
Summer RISE 2024 ተሳታፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
MCPS Summer RISE ፕሮግራም ላይ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ከ1,000 በላይ ተማሪዎች በመረጡት መስኮች ላይ በመሣተፍ ትምህርታዊ ልምምዶች እና በዋጋ ሊተመን የማይችል እውቀት አግኝተዋል። ሠመር ራይዝ (ተማሪዎች ስለ ፈጠራ ልምድ የሚያሰላስሉበት) ከቢዝነስ፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጠቃሚ ልምድ የሚቀስሙበት ተነሳሽነት ነው። መርሃግብሩ ለታዳጊ ወጣቶች እና ለሲንየር ተማሪዎች በሠመር ወቅት በሙያ ላይ የተመሰረተ የትምህርት እድል ላይ እንዲሳተፉ የተነደፈ ነው። የዚህ አመት ተሳታፊዎች ጁላይ 25 በማጠቃለያ ስነ-ስርዓት ያጠናቅቃሉ።
በዚህ ሠመር ይቃኙ
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org