ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ምሽት እንዳያመልጥዎት!
በመጪዎቹ ሳምንታት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ምሽቶችን ያካሂዳሉ። ይህ ከልጆችዎ አስተማሪዎች እና ሰራተኞች ጋር ለመገናኘት፣የእርስዎ ተማሪ በክፍል ውስጥ ምን እንደሚማር/እንደምትማር የበለጠ ለማወቅ፣ እና ለበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ለመመዝገብ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። የትምህርት ቤትዎን የዝግጅት ቀን እና ሰዓት ይመልከቱ።
ስለ ሱፐርኢንተንደንት የፎል ወቅት የማህበረሰብ ተሳትፎ መርኃግብሮች የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ
የሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴለር የመግቢያ እቅድ አካል እንደመሆኑ፤ ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ የበለጠ ለማወቅ እና ዘላቂ ግንኙነቶችን ለመገንባት በተቻለ መጠን ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር ይገናኛሉ። የዚህ አንዱ አካል በሦስት ትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ከማህብረሰቡ ጋር የመነጋገር እና የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎችን ያጠቃልላል። የሚካሄዱባቸው ቀኖች እና ቦታዎች፦
ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 16፣ ፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 7–8 ፒ.ኤም
እሮብ፣ ሴፕቴምበር 18፣ ሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 7–8 ፒ.ኤም
ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 23፣ ሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 7-8 ፒ.ኤም
ተጨማሪ ዝርዝሮች በቅርቡ ይወጣሉ።
ለ 2024-2025 የትምህርት አመት ተማሪዎችን መቀበል
MCPS ለ 2024–2025 የትምህርት አመት ኦገስት 26 ላይ ከ160,000 በላይ ተማሪዎችን በሩን ከፍቶ ተቀብሏል። ከአዲሱ ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴለር መምጣት ጋር ይህ አመት አስደሳችና አዲስ ምዕራፍ ነው። ከትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀንዎ ብዙ ምርጥ ፎቶዎችን ስለላኩ እናመሰግናለን፣ ካላዩት የእኛን የፎቶ ክምችት/ጋለሪ ይመልከቱ።
በቀን መቁጠርያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ!የሴቶች ልጆች የባንዲራ እግር ኳስ/Flag Football የመክፈቻ ቀን
የሴቶች ልጆች የባንዲራ እግር ኳስ/Flag Football ወቅት የመክፈቻ ቀን ሴፕቴምበር 4 ነው! 25 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሁሉም በቡድን ተሰልፈው በካውንቲው ውስጥ በአራት ቦታዎች በሚካሄዱ የመክፈቻ ቀን በዓላት ላይ ይሳተፋሉ። የባልቲሞር ሬቨንስ እና የዋሽንግተን ኮማንደሮችን የመደገፍ ሥነ ሥርዓቶች ይከናወናሉ። የጊዜ ሰሌዳው እና ቦታው ከዚህ በታች ተገልጿል።
የሚካሄድባቸው ቦታዎች |
Richard Montgomery HS ሪቻርድ ሞንጎሞሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት |
ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Wootton HS |
3:30 - የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ/Game #1 |
ሮክቪል ከሼርውድ ጋር/Sherwood at Rockville |
ዋልተር ጆንሰን ከፑልስቪል ጋር/Poolesville at Walter Johnson |
5:00 - የመክፈቻ ቀን ሥነ ሥርዓት |
||
5:45 - ሁለተኛ ዙር ጨዋታ/Game #2 |
ስፕሪንግብሩክ ከአይንስታይን ጋር/Springbrook at Einstein |
ኖርዝዌስት ከኩዊንስ ኦርቻርድ ጋር/Northwest at Quince Orchard |
7:00 - ሦስተኛ ዙር ጨዋታ/Game #3 |
ጌትስበርግ ከሪቻርድ ሞንትጎመሪ ጋር/Gaithersburg at RM |
ክላርክስበርግ ከውተን ጋር/Clarksburg at Wootton |
የሚካሄድባቸው ቦታዎች |
ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Paint Branch HS) |
ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Seneca Valley HS) |
3:30 - የመጀመርያ ዙር ጨዋታ/Game #1 |
ኬኔዲ ከብሌክ ጋር/Kennedy at Blake |
ቤተዝዳ ቼቪ ቼዝ ከደማስከስ ጋር/B-CC at Damascus |
5:00 - ሁለተኛ ዙር ጨዋታ/Game #2 |
ዊተን ከማግሩደር ጋር/Wheaton at Magruder |
ዋይትማን ከዋትኪንስ ሚል ጋር/Whitman at Watkins Mill |
6:15 - የመክፈቻ ቀን ሥነ ሥርዓት |
||
7:00 -ሦስተኛ ዙር ጨዋታ/Game #3 |
ብሌር ከፔይንት ብራንች ጋር/Blair at Paint Branch |
ቸርችል ከሴኔካ ቫሊ ጋር/Churchill at Seneca Valley |
ተጨማሪ መረጃ "Girls’ Flag Football" ድረገጽ ላይ ይገኛል።አጠቃላይ እይታ የወቅቱን መርኃግብሮች ዝርዝርጨምሮ
ሴፕቴምበር 5 ላይ ከሚከፈተው የፎል ወቅት የስፖርት ምሽት በፊት ስለ ደህንነት የተሻሻሉ አቅጣጫዎችን ይገንዘቡ
MCPS ተማሪ-አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ ተመልካቾች እና ማህበረሰባችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ አካባቢን ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው። የፎል ወቅት ስፖርት የመክፈቻ ምሽት ሀሙስ፣ ሴፕቴምበር 5 ይካሄዳል። የአትሌቲክስ ውድድሮችና ዝግጅቶች በሚካሄዱበት ወቅት MCPS የአትሌቲክስ ደህንነት እቅዱን ተግባራዊ ይደረጋል። የውድድር ወቅቱን ለመጀመር ሁሉም የቫርሲቲ እግር ኳስ ጨዋታዎች እና ሌሎች ትልልቅ ዝግጅቶች በደህንነት እቅድ ደረጃ 1 መሠረት ይከናወናሉ። የደረጃ 1 እርምጃዎች (Tier 1 actions) የሚከተሉት ናቸው፦
ለወቅቱ ለመዘጋጀትና ተማሪዎች ወደ ጨዋታዎች ለመግባት የተማሪ መታወቂያቸውን ወይም StudentVue እንዳላቸው ማረጋገጥ አለባቸው። የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና (ከተሣታፊ ትምህርት ቤቶች ያልሆኑ) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከአዋቂዎች ጋር አብረው መሆን አለባቸው፣ ይሄውም በጨዋታው ለሚቆዩበት ጊዜ አብረዋቸው ያሉት አዋቂዎች ተማሪዎችን መከታተል እና መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።
ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህንን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000. ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
በኢሜይል እና አጫጭር ጽሁፍ የሚተላለፉ መልዕክቶችን እና የ MCPS ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኤሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይመልከቱ።
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org