የማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ ተከታታይ የስርዓተ ትምህርት ምሽቶችን ያካሄዳል
የማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ ቡድን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ማህበራዊ ጥናቶች እንዴት እንደሚሰጡ እና ስርአተ ትምህርቱ ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 11ኛ ክፍል የተለያዩ የሰው ዘሮችን እና ባህሎችን ታሪክ እንዴት በትምህርቶቹ እንደሚያካትት ለማወቅ/ለማሳወቅ ተከታታይ የስርዓተ ትምህርት/የካሪኩለም ምሽት ዌብናሮችን ያስተናግዳል። ዌብናሮቹ በሚከተሉት ቀናት 6፡30–7፡30 p.m. ይካሄዳሉ፦
ለመሳተፍ፣ ቤተሰቦች ለመሣተፍ ከላይ ባሉት የበይነመረብ ማገናኛዎች መመዝገብ አለባቸው፤ እና ዌቢናር የሚሳተፉበት ማገናኛ ይላክላቸዋል።
ከእኛ ጋር ለመቀላቀል እቅድ ያዘጋጁ!
የሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴለር የመግቢያ እቅድ አካል በመሆኑ ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ የበለጠ ለማወቅ በተቻለ መጠን ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር ይገናኛሉ። የዚህ አንዱ አካል በሦስት ትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ከማህብረሰቡ ጋር የመነጋገር እና የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎችን ያጠቃልላል። ከእነዚህ ክፍለ ጊዜዎች በአንዱ ለመሣተፍ ቀኑን ይምረጡ፡
በስፓንሽኛ የማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል።
ተጨማሪ ዝርዝሮች በቅርቡ ይወጣሉ።
ዋትኪንስ ሚል ክላስተር (Watkins Mill Cluster) ሴፕቴምበር 14 የአጎራባች አካባቢ ፓርቲ ያካሄዳል
የዋትኪንስ ሚል ክላስተር ቅዳሜ ሴፕቴምበር 14 ከቀትር እስከ 3 p.m. ለአጎራባች አካባቢ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ፓርቲ ያስተናግዳል። ተማሪዎችን ከእረፍት በኋላ ወደ ትምህርት ቤት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሲሆን በሴፕቴምበር ውስጥ ከሚከናወኑት ዝግጅቶች ይሄኛው አንዱ ብቻ ነው። ዝግጅቱ ፀሐይም ቢሆን ዝናብም ቢኖር በዚህ አድራሻ በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል፦ Watkins Mill High School, 10301 Apple Ridge Road in Gaithersburg.
ዝግጅቱ የሞንትጎመሪ ቪሌጅ እና ኔልስቪል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ጨምሮ ከዋትኪንስ ሚል፣ ስቴድዊክ፣ ዊትስተን እና ሳውዝ ሌክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ጭምር በዋትኪንስ ሚል ክላስተር ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ክፍት ነው።
በዝግጅቱ ወቅት ከ 40 በላይ የማህበረሰብ አጋሮች የተለያዩ ግብዓቶችን እና መረጃዎችን ለቤተሰቦች ይሰጣሉ። የማህበረሰብ አጋሮቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ CASA፣ Identity፣ የጌትስበርግ ከተማ የወጣቶች አገልግሎት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ መፃህፍት፣ የወላጆች ማበረታቻ ፕሮግራም፣ ስለ አካል ብቃት የሚያሰለጥኑ ቡድኖች፣ የወንዶች እና የሴት ወጣቶች ክለቦች፣ እና የጨቅላ ህፃናት እና ታዳጊዎች ኢሞሪ ግሮቭ ናቸው። በተጨማሪም ምግብ የሚያከፋፍሉ መኪናዎች፣ ሙዚቃ፣ የእቃዎች ሎተሪ/ራፍልስ እና በተማሪዎች የሚቀርቡ ትርኢቶች ይኖራሉ።
ስለ ዝግጅቱ የሚገልፅ በራሪ ጽሑፍ/ፍላየር፣ እንግሊዘኛ
ስለ ዝግጅቱ የሚገልፅ በራሪ ጽሑፍ/ፍላየር፣ ስፓንሽኛ
ስለ ዝግጅቱ የሚገልፅ በራሪ ጽሑፍ/ፍላየር፣ ፈረንሳይኛ
ትምህርት ቤት የመመለሻ ምሽት ዝግጅት እንዳያመልጥዎ!
ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ የምሽት ዝግጅቶች በሴፕቴምበር ወር ውስጥ ይከናወናሉ፣ ስለዚህ እርስዎ እስካሁን ያልተሳተፉ ከሆነ፣ የእርስዎን ት/ቤት ዝግጅት ቀን እና ሰዓት ለማወቅከዚህ መርሐግብር ይመልከቱ። እና፣ ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ ዝግጅት ላይ የሚቀርቡ የትምህርት መርጃዎችን በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይመልከቱ፣ስለ ት/ቤት የአውቶቡስ መስመር መርሃ ግብሮች፣ ስለ ትምህርት ቤት ምግቦች፣ የአትሌቲክስ እና MCPS የተማሪ የስነምግባር ህግን ያካትታል፤ ይምጡና ይሳተፉ እንዳያመልጥዎት።
ይህንን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000. ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
አንብቡበኢሜይል እና በጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ይከታተሉ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኤሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይመልከቱ።
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org