ከእኛ ጋር ለመቀላቀል እቅድ ያዘጋጁ!
የሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴለር የመግቢያ እቅድ አካል በመሆኑ ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ የበለጠ ለማወቅ በተቻለ መጠን ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር ይገናኛሉ። የዚህ አንዱ አካል በአራት ትምህርት ቤቶች የሚደረጉ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎችን ያካትታል። ከእነዚህ ክፍለ ጊዜዎች በአንዱ ለመሣተፍ ቀኑን ይምረጡ፡
በእያንዳንዱ ክፍለጊዜ በስፓኒሽኛ የማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል።
መጪው የማህበረሰብ ተሳትፎ ክፍለ ጊዜ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና የማህበረሰብ አባላት የዲስትሪክቱን ተግባራት እና አካደሚክስን በሚመለከቱ ሁለት ቁልፍ ርዕሰጉዳዮች ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲያካፍሉ እድል ይኖራቸዋል።
በነዚህ ክፍለጊዜያት ተሰብሳቢዎች በንግግር አስተያየት የመስጠት እድል ይኖራቸዋል። አስተያየቶቻቸውን በዲጂታል ማቅረብ የሚፈልጉ ሰዎች ይህንን Google form ተጠቅመው ማቅረብ ይችላሉ።
የሠመር SSL ሰዓቶች እስከ ሴፕቴምበር 27 ድረስ መቅረብ አለባቸው
በሠመር ወቅት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአት (SSL) ያጠናቀቁ ተማሪዎች የሠሩበትን ማረጋገጫ ቅጾቻቸውን ለትምህርት ቤቶቻቸው SSL አስተባባሪ እስከ አርብ፣ ሴፕቴምበር 27 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶች ማስመዝገብ አለባቸው። ከ 6ኛ ክፍል በኋላ በ MCPS የተመዘገቡ ተማሪዎች የ SSL መስፈርትን በማጣጣት የሚያካክስ/ እፎይታ ያገኛሉ።
በአካል እና ቨርቹዋል SSL አገልግሎት ለመስጠት ያሉት እድሎች፣ማሳሰቢያዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች በሙሉ SSL ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ለሁሉም ክፍሎች የትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝር በሁሉም ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል።
2024–2025 ወቅታዊ የትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝር ከቅድመ መዋዕለ ህጻናት/ሄድ ስታርት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድረስ—ለሁሉም ክፍሎች ተዘጋጅቷል። የተማሪዎችን ምርጫ እና የቬጀቴሪያን አማራጮችን የሚያካትተው የምግብ ዝርዝር በእንግሊዝኛ፣ ስፓንሽኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ቻይንኛ፣ ፖርቹጋልኛ፣ ኮሪያንኛ፣ ቬትናምኛ እና በአማርኛ ይገኛል።
በተጨማሪም፣ ለዚህ የትምህርት አመት የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች (FARMS)ማመልከቻይገኛል። ምንም እንኳን ልጃቸው ባለፈው አመት የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦችን ለማግኘት ብቁ ቢሆንም/ብትሆንም FARMS ፕሮግራም በየአመቱ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቤተሰቦች እንደገና ማመልከት አለባቸው። ተማሪዎች/ቤተሰቦች ከማንኛውም ትምህርት ቤት የወረቀት ማመልከቻ ሊጠይቁ ይችላሉ፣ነገር ግን ሂደቱን ለማቀላጠፍ በኦንላይን ቢያመለክቱ ይፈጥናል።
ለረጅም ጊዜ በሕክምና ለቆዩ ተማሪዎች የተቀናጀ የትምህርት ፕሮግራም ወቅታዊ የጊዜ ሠሌዳ
MCPS አዲስ ረዥም ጊዜ በህክምና ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የተቀናጀ የትምህርት ፕሮግራም የጊዜ ሠሌዳ እያዘጋጀ ነው። ይህ ፕሮግራም የህክምና ክትትል ላለባቸው ተማሪዎች ለአንድ አመት ትምህርት ቤት አካባቢ በአካል በመገኘት መማር እንደማይችል/እንደማትችል ፈቃድ ባለው የህክምና ባለሙያ የተረጋገጠ ከሆነ፤ በተመሳሳይ እና በተለያየ ቨርቹዋል የትምህርት አገልግሎት ወጥነት ያለው እና አጠቃላይ ትምህርታዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
ለፕሮግራሙ ማመልከቻ ለማቅረብ ከኦክቶበር 1, 2024 ጀምሮ በኦንላይን ይገኛል።ፕሮግራሙ ኖቬምበር 6, 2024 በይፋ ይጀመራል። ሂደቱን በጠበቀ መልኩ ስለ ፕሮግራሙ አቅርቦት/ሎጂስቲክስ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ይወጣል።
"Remind App" የተሰኘ መተግበርያ አሁን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይገኛል።
"Remind" መተግበርያ በዚህ አመት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኝ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች፣በመምህራን፣በተማሪዎች እና በወላጆች መካከል ለሚደረጉ ግንኙነቶች የተዘጋጀ የመልእክት ማስተላለፊያ ነው። የት/ቤት ሰራተኞች፣የማእከላዊ ቢሮ ሰራተኞች፣ተማሪዎች፣ እና ወላጆች ሁሉም የጽሁፍ መልእክት፣ኢሜል ወይም የስልክ ጥሪ በመረጡት ቋንቋ የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም መልዕክቶችን መላክ እና/ወይም መቀበል የሚያስችል የመልክት ማስተላለፊያ አካውንት ነው።
ወላጆች መልዕክቶች እንዲደርሳቸው "Remind" መመዝገብ ወይም መተግበሪያ ማውረድ የለባቸውም። መልእክቶች በትምህርት ቤቱ በተመዘገበው ኢሜል እና ስልክ ቁጥር ይላካሉ፤እና ወላጆች ወዲያውኑ መልእክቱ ይደርሳቸዋል። ወላጆች ለሚደርሳቸው መልእክት ምላሽ መስጠት ከፈለጉ መተግበሪያውን ማውረድ ወይም በይነመረብ ላይ አካውንት መክፈት አለባቸው። መተግበሪያውን እንዴት ማውረድ እንደሚችሉ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ስለ"Remind" አጠቃቀም የሚገልፅ ዩቲዩብ/YouTube ቪዲዮ
የወላጅ ፈጣን መመሪያ
እንግሊዝኛ፣ስፓንሽኛ፣ፈረንሳይኛ፣ኮርያንኛ፣ቻይንኛ፣ቬትናምኛ፣ፖርቹጋልኛ፣አማርኛ
ለአውቶቡስ ሹፌርነት የስራ ፈላጊዎች ሴፕቴምበር 17 አውደ ርእይ ተዘጋጅቷል።
MCPS ማክሰኞ፣ሴፕቴምበር 17 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ ቀትር ድረስ ለአውቶቡስ ሾፌርነት የስራ ፈላጊዎች አውደ ርዕይ እያዘጋጀ ነው። አውደ ርዕዩ የሚካድበት ቦታና አድራሻ፡ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ይካሄዳል።
የአውቶቡስ ሹፌር ለመሆን መሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፦
ፍላጎት ያላቸው እጩዎች MCPS Careers portal ላይ ስለራሳቸው መግለጫ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። በዝግጅቱ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ።
የተማሪ አመራር እና SSL እድሎች
ለተማሪዎች የሚከተሉት የአመራር እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች እድሎችይገኛሉ። አንዳንዶቹ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችንም ይሰጣሉ። ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶች ማስመዝገብ አለባቸው።
ለመካከለኛ ደረጃ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች"The Association for Safe International Road Travel" እና "Montgomery County Regional Student Government Association" በመንገድ ደህንነት እና ተማሪዎችን እና ሌሎች ተጓዦችን በመንገድ ላይ ደህንነታቸውን መጠበቅ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውድድር እያዘጋጁ ናቸው። የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ (PSA) የውድድር መስፈርቶችን አሟልተው ያቀረቡ ተሳታፊዎች 10 SSL ሰአት ያገኛሉ፣ እና የአማዞን የስጦታ ካርዶችን የማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል። የመወዳደሪያ ግብአቶች እስከ እሁድ፣ ኦክቶበር 6 መቅረብ አለባቸው። የበለጠ ለመረዳት ከዚህ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጃገረዶች ክፍት የሆነ "Girls With Impact" ስለ ንግድ እና አመራር ነጻ የ 10-ሳምንት ኮርስ ይሰጣል። ይህ ፕሮግራም MBAs ባላቸው ባለሙያ አሰልጣኞች ኦንላይን ኮርሶችን ይሰጣል። የበለጠ ይወቁ እና እስከአርብ፣ ኦክቶበር 45 p.m. ድረስ ይመዝገቡ።
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS ውስጥ ሶስት ታይትል I ትምህርት ቤቶች በዲስትሪክቱ የመጀመሪያ ንባብ እና ሮብስ ተነሳሽነት ላይ ተሳትፈዋል፣ የሜሪላንድ ስቴት ዳኞች ስለ ፍትህ እና ስለ ፍትሃዊነት መሪ ሃሳቦችን ለተማሪዎች አጉልተው ገልፀዋል። ይመልከቱት.
ይህንን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
አንብቡበኢሜይል እና በጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ይከታተሉ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኤሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይመልከቱ።
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org