የሂስፓኒክ ቅርስ የሚከበርበት ወር
የሂስፓኒክ ቅርስ የሚከበርበት ወር፤ የሂስፓኒክ ማህበረሰቦችን ልዩ ልዩ ባህሎች፣ታሪኮች፣እና አስተዋጽአቸውን ለማክበር ጥሩ አጋጣሚ ነው። ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን፣ እና በአለም ዙሪያ ስፓንሽኛ ተናጋሪ ሀገራት ያከናወኑትን የተማሪዎች፣ የአስተማሪዎች፣ እና የሰራተኞች ስኬቶችን እና ወጎችን በማንፀባረቅ ይህን የበለጸገ ቅርስ ያከብራሉ።
34 ከመቶ በላይ የሚሆኑት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ስፓንሽ ወይም የሂስፓኒክ ዝርያ ያላቸው ስለሆኑ፣በዚህ ወር በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ያሉት ደማቅ ባህሎች ትርጉም ባለው መታሰቢያነት ይከበራል። በማህበረሰባችን ውስጥ የሂስፓኒክ ግለሰቦችን ልዩ አመለካከቶች እና አስተዋፆ የምናደንቅበትና የምንዘክርበት ጊዜ ነው። በዚህ ወር፣ ትምህርት ቤቶች ተደማጭነት ያላቸውን ሰዎች ታሪክና አስተዋጽኦ አጉልተው ሊያቀርቡ፣ባህላዊ ዝግጅቶችን ሊያስተናግዱ እና የሂስፓኒክ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ቅርስ እና ተሞክሮ የሚያንፀባርቁ ትረካዎችን ሊያሠራጩ ይችላሉ።
የሂስፓኒክ ቅርስ የሚዘከርበትን ወር ማክበር ስለ ተለያዩ ባህሎች ያለንን ግንዛቤ እና አድናቆት ከማበልጸግ በተጨማሪ በትምህርት አካባቢያችን ውስጥ የማህበረሰቡን የአካታችነት ስሜት ያዳብራል።
የሂስፓኒክ ቅርስን ማክበር—የሰራተኞች ትኩረት፡ ኤድጋር ፔሬዝ
ለቅዳሜ ትምህርት ቤት (Saturday School) ምዝገባ አሁን ክፍት ነው።
George B. Thomas Sr. Learning Academy, Inc. እና የቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School በመባል የሚታወቀው ት/ቤት ለ 2024–2025 የትምህርት አመት ምዝገባ ክፍት ነው። የቅዳሜ ትምህርት ቤት ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ (K–12ኛ) ክፍል በሂሳብ እና በእንግሊዝኛ/ቋንቋ ስነ ጥበብ በአካዳሚክ የድጋፍ ፕሮግራሞችን ይሰጣል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የማስጠናት እና የማስተማር ፕሮግራም ሴፕቴምበር 28 በዘጠኝ ቦታዎች ላይ ትምህርት ይጀምራል፤እንዲሁም ቨርቹዋል አማራጭም ይሰጣል። ትምህርቱ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሥርዓተ ትምህርት ጋር የተጣጣመ ከመሆኑም በላይ የሚያስተምሩት ሠርተፊኬት ያላቸው መምህራን ናቸው። ቦታዎቹ፦ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ አልበርት አንስታይን፣ ፔይንት ብራንች፣ ስፕሪንግብሩክ፣ ዊተን፣ ጌትስበርግ፣ ክላርክስበርግ፣ ሮክቪል፣ እና ኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው። ለነጻ እና ለቅናሽ ዋጋ ምግብ (FARMs) ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች ዓመታዊ ወጪ $85፣$40 ይሆናል።
ለቅዳሜ ትምህርት ቤት 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ምዝገባ እዚህ (እንግሊዝኛ) እና ስፓንሽኛ/(en Español) እዚህነው። የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ እዚህ (እንግሊዝኛ) እና ስፓንሽኛ/(en Español) እዚህይገኛል። በተጨማሪ $150 ክፍያ፣ የቅዳሜ ትምህርት ቤት ለአምስት ሳምንት ክፍለ ጊዜኮዲንግ እና ሮቦቲክስትምህርቶችን ይሰጣል፤ (እንግሊዝኛ) እናስፓንሽኛ/(en Español) እዚህይመዝገቡ።
ለአጠቃላይ መረጃ 301-287-8980 ይደውሉ።
የጣምራ-ምዝገባ ፕሮግራሞች የመረጃ ልውውጥ ምሽቶችን ያካሄዳሉ
ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጣምራ-ምዝገባ ፕሮግራምን “ታላቅ ጅምር” ብለውታል። ወላጆች ተማሪዎቻቸው ገና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እያሉ፣የአራት ዓመት የዲግሪ ፕሮግራም ውስጥ በነፃ ያገኙትን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዓመታት በቂ ገንዘብ ለማትረፍ/ለማጠራቀም ረድቶናል ይላሉ።
አንድ ወላጅ ስለ ፕሮግራሙ እንዲህ በማለት ገልፀዋል፦ “የጊዜ አያያዝን፣ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቁ ነገሮችን፣የሚወስዱትን ኮርሶች እንዴት ማንበብ እንደሚችሉ እና የኮርስ መስፈርቶችን ይማራሉ።"
የጣምራ-ምዝገባ ፕሮግራሙ በዚህ ወር እና በኦክቶበር ወር የመረጃ ክፍለ ጊዜዎችን ያካሄዳል። እነዚህ ፕሮግራሞች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያለምንም ወጪ የተወሰኑ የኮሌጅ ኮርሶችን እንዲወስዱ እድል ይሰጣቸዋል። ስለ ጣምራ-ምዝገባ ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገፁ ላይ ይገኛል፤ እና የመረጃ ክፍለ-ጊዜዎች ዝርዝር እዚህ ይገኛል።
በተማሪዎች ጥገና የተደረገላቸው ኮምፒውተሮችን ለማግኘት ለኮምፒውተር ቤተ ሙከራ አሁን ያመልክቱ፦
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF)ድርጅት በካውንቲው ለትርፍ ያልተቋቋመ አንድ ድርጅት ኮምፒተሮችን ይለግሳል። የኮምፒዩተር ቤተ-ሙከራው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን፣ጠፍጣፋ LCD ሞኒተሮችን፣ ኪቦርዶችን፣ ማውስ እና አንድ ፕሪንተር ያላቸው ስድስት ጥገና የተደረገላቸው ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮችን ያካትታል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ 501©(3) የተመዘገቡ ድርጅቶች ለኮምፒዩተር ቤተ-ሙከራ ማመልከቻ ማስገባት እና ሐሙስ፣ ኖቨምበር 21 በክላርክስበርግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በስጦታ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት መስማማት አለባቸው።
ማመልከቻዎች ዓርብ፣ ኦክቶበር 4 ተጠናቀው መቅረብ አለባቸው፣ማመልከቻዎችን በኢሜል፣በፋክስ ቁጥር 240-740-5205 ወይም በዚህ አድራሻ፦ 12501 Dalewood Drive, Room 109B, Silver Spring, MD, 20906 በፖስታ ቤት መላክ ይቻላል። ጥያቄ ካለዎት Kelly Johnson ያነጋግሩ።
በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ የምርጫ ቦርድ ተማሪዎችን ለእርዳታ መፈለግ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምርጫ ቦርድ በምርጫ ቀናት በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ የሚረዱ ተማሪ ረዳቶችን እና አምባሳደሮችን ይፈልጋል። ተማሪዎች እድሜያቸውን እና የስራ ድርሻቸው መሠረት በማድረግ ሊከፈላቸው ወይም የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶች ሊሰጣቸው ይችላል።
ዕድሜያቸው 16 አመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ በጎፈቃደኛ ተማሪዎች፡ ለእያንዳንዱ የሙሉ ቀን አገልግሎት ቢያንስ እስከ $250 ወይም 25 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአት ሊያገኙ ይችላሉ። ለማመልከት፣ይህን ድረገጽ ይጎብኙእና “New Applicants.” ስር ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ሰራተኛ
የሥራ ድርሻ መግለጫ እና የአበል ክፍያ/SSL መረጃ
ዕድሜያቸው 15 አመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ ተማሪዎች፡ የወደፊት የምርጫ አምባሳደሮች ሊሆኑ ይችላሉ፤እንዲሁም የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለተማሪዎቹ እና ለወላጆቻቸው/ለአሳዳጊዎቻቸው ስልጠና ያስፈልጋል። በስልጠናው ወቅት ዝርዝር ተግባሮች እና ከበጎ ፈቃደኞች የሚጠበቅባቸው ክንውኖች ይገለፅላቸዋል።
የወደፊት ምርጫ ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs)
መጪዎቹ የማህበረሰብ ዝግጅቶች
አርብ፣ሴፕቴምበር 27 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብሎ ለሚለቀቁበት ቀን ሁለት ነጻ የወጣቶች ብሎክ ፓርቲዎች ተዘጋጅተዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል የሆኑት ማሪሊን ባልኮምቤ/ Marilyn Balcombe ለመለስተኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 1-4 p.m. ትምህርት ቤት የመመለስ ፓርቲ/“Back-to-School Block Party” ያስተናግዳሉ። አድራሻው፦ BlackRock Center for the Arts, 12901 Town Commons Drive, Germantown. ዝግጅቱ የእግር ኳስ ክሊኒክ፣ የኪነጥበብ ስራዎችን፣ በተማሪዎች የሚቀርቡ ትርኢቶችን እና የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን የማግኘት እድልን ያካተተ ነው። ተጨማሪ መረጃ
የካውንስል ምክትል ፕሬዝዳንት ኬት ስቱዋርት/Kate Stewart “ በሚከተለው አድራሻ፦ 1 Veterans Place in downtown Silver Spring መሃል ሲልቨር ስፕሪንግ 2-6 p.m ላይ ለወጣቶች “Buckets & Beats: ሲልቨር ስፕሪንግ የወጣቶች ብሎክ ፓርቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ያስተናግዳሉ።በዚህ ዝግጅት ላይ 3 ለ 3 የቅርጫት ኳስ ውድድር፣pop-up skatepark፣ አርት፣ እና DJ ተካቷል። ተጨማሪ መረጃ
ይህንን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
ያንብቡ፦በኢሜይል እና በጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ይከታተሉ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን፦ Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይከታተሉ።
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org