መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 26, 2024

ቤልስ ሚልስ (Bells Mills)፣ እና ዉድፊልድ (Woodfield) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብሔራዊ የብሉ ሪባን ሽልማት አሸንፈዋል

ቤልስ ሚልስ (Bells Mills) አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና ዉድፊልድ (Woodfield) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዩ.ኤስ የትምህርት ዲፓርትመንት የ2024 ብሄራዊ የብሉ ሪባን ትምህርት ቤቶች በመባል እውቅና አግኝተዋል። በዚህ ደረጃ እውቅና ለማግኘት 44ኛው እና 45ኛው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ናቸው።

የብሔራዊ ብሉ ሪባን ትምህርት ቤቶች ሽልማት የላቀ የአካዳሚክ አፈጻጸም ያሳዩ ትምህርት ቤቶችን ወይም የውጤት ክፍተቶችን በማጥበብና በመዝጋት ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ለሚያስመዘግቡ ትምህርት ቤቶች እውቅና ይሰጣል። ሁለቱም ትምህርት ቤቶች በአገር አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን 356 ትምህርት ቤቶች እና በሜሪላንድ ውስጥ ተመሣሣይ እውቅና የተሰጣቸው 10 ትምህርት ቤቶች ጋር ይቀላቀላሉ።

ቤልስ ሚል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Bells Mill Elementary School

በፖቶማክ አካባቢ የሚገኘው ቤልስ ሚል ት/ቤት ወደ 610 የሚጠጉ ተማሪዎችን ያገለግላል። ለአካዳሚክ ልህቀት፣ለመከባበር እና ሁሉን አቃፊነት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አንጻር የት/ቤቱ ቁርጠኝነት የሚደነቅ የትምህርት ምህዳር ፈጥሯል። ከጠንካራ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከውጤታማ የማስተማር ዘይቤ እና በትብብር ከሚካሄድ የትምህርት አካባቢ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ዉድፊልድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ዉድፊልድ ከተለያየ ዳራ የሚመጡ ከ 300 በላይ ተማሪዎችን ያገለግላል። ትምህርት ቤቱ ማህበረሰባዊነት እና የባለቤትነት ስሜትን በማሳደግ ላይ የሰጠው ትኩረት አወንታዊ እና አካታች የትምህርት አካባቢን ፈጥሯል። በተማሪዎች የሚከናወን አትክልት፣ የአመራር ፕሮግራሞች፣ እና የእኩዮች አማካሪነት ጭምር ተማሪዎች በተለያዩ የት/ቤት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፋሉ።


ከካርላ ስልቨስትረ/Karla Silvestre ጋር የተካሄደ ጥያቄ እና መልስ "Q&A

ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15 የሂስፓኒክ ቅርስ ወር ይዘከራል።34 በመቶ በላይ የሚሆኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ሂስፓኒክ ወይም የሂስፓኒክ ዝርያ ያላቸው ናቸው። ይህ ወር በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያሉትን በርካታ የሂስፓኒክ ባህሎች፣ አስተዋጾ፣ እና የበለፀገ ስብጥር ለማንፀባረቅ እድል ይሰጣል። እንዲሁም የሂስፓኒክ ቅርስ የሆኑትን አንዳንድ ድንቅ ሰራተኞቻችንን እና መሪዎቻችንን እንድናከብር እድል ይሰጠናል። ከትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ካርላ ሲልቬስትረ ጋር የተደረገው ይህ ጥያቄ እና መልስ አያምልጥዎት።


ኦክቶበር 9 "የሂስፓኒክ የወላጆች ምሽት" ኮሌጅን በፋይናንስ ስለመደገፍ ይወያያል።

በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች–ሮክቪል የሂስፓኒክ ኮሌጅ አውደ ርእይ የሚካሄደው አርብ፣ ኦክቶበር 4 ከጠዋቱ 9 a.m.–12:30 p.m. ነው። የሂስፓኒክ የወላጆች ምሽት፦ ስለ ኮሌጅ ፋይናንስ የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ ከዝግጅቱ ጋር በጥምረት ይካሄዳል። የወላጆች ምሽት እሮብ፣ ኦክቶበር 9 ከምሽቱ 6–7:30 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ 15 W. Gude Drive, Third Floor, Potomac Room. (15 ዌስት ጉዴ ድራይቭ፣ ሦስተኛ ፎቅ፣ ፖቶማክ መሰብሰቢያ ክፍል)

ዝግጅቱ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) TRIO የትምህርት ዕድል ማእከል ዳይሬክተር ቤቨርሊ ኮልማን፣ እና ሮንዳ ማክላረን-ስኮት፣ የሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) የፋይናንስ ድጋፍ አገልግሎት ካውንስለር ስለ ኮሌጅ የፋይናንስ አማራጮችን ለመወያየት የቀረቡ ገለጻዎችን ያካትታል። ተሰብሳቢዎች ስለ ፌዴራል የተማሪዎች እርዳታ መታወቂያ (FSA ID) ቁጥር ​​ግንዛቤ ያገኛሉ፥ እና በአውደ ጥናቱ ወቅት የመታወቂያ ቁጥሩን የማግኘት እድል ይኖራቸዋል። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) ስፓንሽኛ ቋንቋ ተናጋሪ አስተርጓሚዎች በቦታው ይገኛሉ። 

ስለ ኮሌጅ የፋይናንስ ድጋፍ የሂስፓኒክ ወላጆች የምሽት

ስለ ኮሌጅ የፋይናንስ ድጋፍ—የሂስፓኒክ ወላጆች ምሽት

Collegiate Directions እና MCPS እንዲሁ ስለ ፋይናንስ እርዳታ "Financial Aid" የመረጃ ልውውጥ ምሽት ሐሙስ፣ኦክቶበር 3ከምሽቱ 6:30 p.m. የዙም ስብሰባ ያስተናግዳሉ።እዚህ ይመዝገቡ። ይህ ዝግጀት የሚከናወነው በስፓንሽኛ ቋንቋ ይሆናል። ከተመዘገቡ በኋላ የዙም መረጃውን እናጋራለን። ጥያቄዎችን ወደ ጂል ሰመንስ/Jill Semmens ኢሜይል ያድርጉ። 

በተጨማሪም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ነጻ የገንዘብ ድጋፍ የመረጃ ልውውጥ ምሽቶችን ያካሂዳሉ።


ማሳሰቢያ፦ እስከ ኦክቶበር 8 ድረስ ለ FARMS ያመልክቱ

ለዚህ የትምህርት አመት የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች(FARMS)ማመልከቻ ይገኛል። ምንም እንኳን ልጃቸው ባለፈው አመት የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦችን ለማግኘት ብቁ ቢሆንም/ብትሆንም FARMS ፕሮግራም በየአመቱ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቤተሰቦች እንደገና ማመልከት ይጠበቅባቸዋል። ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 8 ያለፈው የትምህርት አመት የተማሪዎች ብቁነት ማረጋገጫ ወደዚህኛ አመት የሚሸጋገርበት የመጨረሻው ቀን ነው። ከኦክቶበር 8 በኋላ፣አዲስ የብቁነት ማረጋገጫ የሌላቸው ተማሪዎች ወደ ክፍያ ስለሚመለሱ ለምግብ መክፈል ይኖርባቸዋል። ተማሪዎች/ቤተሰቦች ከማንኛውም ትምህርት ቤት የወረቀት ማመልከቻ ሊጠይቁ ይችላሉ፣ነገር ግን ሂደቱን ለማቀላጠፍ በኦንላይን ቢያመለክቱ ይፈጥናል




ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)