መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 3, 2024

ከኦክቶበር 21 እስከ 26 የሚካሄድ የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት

MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች የሳይኮሎጂስቶች ማህበር ለወጣቶች እና ለቤተሰቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እንዲሰሙ እድል ለመስጠት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ከኦክቶበር 21 እስከ 26 ያስተናግዳሉ። የአእምሮ ጤና ሪሶርስ አውደ ርእይ እና የተማሪዎች መድረክ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 26 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 2 p.m. ይካሄዳል። አድራሻው በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፦ Seneca Valley High School,19401 Crystal Rock Drive in Germantown።

ዝግጅቱ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን። እና ሰራተኞችን ያካተተ ሲሆን፤ MCPS እና የማህበረሰብ አጋሮች ስለአእምሮ ጤና እና ደህንነት መረጃዎችን መለዋወጥ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ወጣቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ በተማሪዎች-የሚመራ መድረክም ይካሄዳል። በሪሶርስ (መገልገያዎች) አውደ ርእይ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ሊመዘገብላቸው ይችላል። ለበለጠ መረጃ፣የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት ድረ ገጽ ይጎብኙ።

ዋና ተናጋሪው ቨርጂኒያ የዲስትሪክት አስተዳዳሪ የሆኑ ዶ/ር ቻርልስ ኤ. ባረት/Charles A. Barrett፣Ph.D., NCSP ሲሆኑ ቀደም ሲል በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 13 ዓመታት የት/ቤት ሳይኮሎጂስት በመሆን ማገልገላቸው ይታወቃል። በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የወደፊት የትምህርት ቤት የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን/ሳይኮሎጂስቶችን በማሠልጠን በተባባሪ ሌክቸረርነት ያገለግላሉ። የዋናው ተናጋሪ መልእክት እና የተማሪዎች መድረክ ከጠዋቱ 10:30 a.m. እስከ 12:30 p.m. ይካሄዳል።

2024 የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት


ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሪጅናል/ለካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ማመልከቻ የሚቀርብበት ጊዜ ከኦክቶበር 7 ጀምሮ እስከ ኖቬምበር 1 ክፍት ይሆናል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በአካባቢያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣እንዲሁም ለሪጅናል እና ለካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ለማመልከት የተለያዩ እድሎች አሏቸው። ከሰኞ፣ኦክቶበር 7 ጀምሮ፣ የ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ParentVUE ላይ የሚገኘውን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማመልከቻ ቅጽ በመጠቀም ለሪጅናል/ለካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች የማመልከት እድል አላቸው። በተጨማሪም፣ ከ 9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በተለያዩ የካውንቲው አካባቢዎች በትርፍ ጊዜ ለሥራ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። ለከፍተኛ ክፍሎች ማመልከትም እንዲሁ ከሰኞ፣ ኦክቶበር 7 ጀምሮ ክፍት ይሆናል። ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የሚያመለክቱበት ቅጽ አገናኝ (Links) ከዚህ በታች ይገኛል፦
9ኛ ክፍል
10ኛ ክፍል
11ኛ ክፍል

ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜዎች አሁን በመካሄድ ላይ ናቸው። በልዩ ፕሮግራሞች ድረ-ገጽ ላይ ሁሉንም ቀኖች ማየት ይቻላል። 

ማመልከቻ የሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን እስከ ዓርብ፣ ኖቬምበር 1 ከቀኑ 3 p.m. ነው። ስለ ፕሮግራሞቹ፣ ብቁ ስለመሆን፣ እና ስለ ኦፐንሃውስ ቀናትከዚህ የበለጠ መረዳት ይችላሉ።


ስለመጪው የትምህርት አመት ካላንደር (የቀን መቁጠሪያ) አስተያየትዎን ያካፍሉን።

MCPS የትምህርት አመት 2025–2026 እና 2026–2027 ካላንደር (የትምህርት ቤቶች የቀን መቁጠሪያ) ለማጠናቀቅ እየሠራ ስለሆነ ከማህበረሰቡ አስተያየት ማግኘት ይፈልጋል። እባክዎ ሀሳብዎን ለማጋራት ይህን የዳሰሳ ጥናት ሞልተው ይመልሱልን

የካላንደር ዝግጅቱን ሂደት ለማዳበር የእርስዎ ግብረመልስ አስፈላጊ ነው። MCPS የመማር ፍላጎቶችን፣ የሥራ ክንውን ፍላጎቶችን፣ በስቴት ህግ የተደነገገ የትምህርት ቤቶች መዘጋትን፣ ቢያንስ ዝቅተኛውን አመታዊ የትምህርት ቀናት ብዛትን እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማክበር፣አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ የሚከሰትባቸውን ቀናት፣ እና ሌሎች ድንገተኛ ክስተቶችን፣ የሰራተኞች የሙያ ማዳበር ሥልጠና ቀናትን፣ እና ተማሪዎች በቅድሚያ የሚለቀቁባቸውን ቀናት፣ የትምህርት ፈተና ከሚሰጥባቸው መርሃ ግብሮች ጋር ማጣጣምን እና ሌሎችም አስፈላጊ ሁኔታዎችን ይመለከታል። 

2025–2026 ሁለቱም ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች (የት/ቤት ካለንደሮች) የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • 2025-2026 የትምህርት አመት ካለንደር ላይ አዲስ የተማሪዎች የሽግግር ቀን እናስተዋውቃለን። ይህ የተማሪዎች የሽግግር ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 25, 2025 በመዋዕለ ህጻናት፣ በሶስተኛ ክፍል፣ በስድስተኛ ክፍል፣እና በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ለመቀበል በድጋሚ የታሰበ የተማሪዎች ቅበላ ቀን ይሆናል።እንዲሁም ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ የሆኑ ወይም ለትምህርት ቤት አዲስ የሆኑ በማንኛውም ክፍል የተመዘገቡ ተማሪዎች፤በአለም አቀፍ የተማሪዎች ምዝገባ የተመደቡ፣ እና የልዩ ትምህርት አገልግሎት ለማግኘት፣ የቋንቋ ችሎታ የማዳበር ድጋፍ ለማግኘት፣ ወይም ለመድብለ ቋንቋ ትምህርት ለተመዘገቡ አዳዲስ ተማሪዎች መግለጫ የሚሰጥበት ቀን ይሆናል።

  • ለሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን በይፋ የሚጀመርበት ቀን ማክሰኞ፣ኦገስት 26, 2026 ይሆናል።

  • የስፕሪንግ ዕረፍት፡ ከሰኞ፣ ማርች 30, 2026፣ እስከ ሰኞ፣ኤፕሪል 6, 2026 ይሆናል።

2025-2026 የትምህርት አመት ካለንደርን በሚመለከት በሁለቱ ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች መካከል ያለው ዋና ልዩነት የክረምት ዕረፍት ቀናት ርዝመት ነው — አንደኛው የስምንት ቀን ዕረፍት ያለው ሲሆን ሁለተኛው 10 ቀን የዕረፍት ጊዜ አለው።

ኮሚቴው 2026–2027 የትምህርት አመት ቀን መቁጠሪያ በማዘጋጀት በጅምር ደረጃ ላይ ስለሆነ በሚከተሉት ላይ ግብረ መልስ ማግኘት ይፈልጋል፦

  • ትምህርት የሚጀመርበት ሳምንት።

  • የዊንተር/የክረምት እረፍት።

  • የታንክስጊቪንግ ሣምንት

የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።

በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት

Commentarios sobre el calendario escolar de MCPS (2025-2026 y 2026-2027)

MCPS 校历反馈(2025-2026 和 2026-2027)

MCPS 학교 달력 피드백(2025-2026 및 2026-2027)

Commentaires sur le calendrier scolaire du MCPS (2025-2026 et 2026-2027)

Phản hồi về Lịch học của Trường MCPS (2025-2026 và 2026-2027)

2025-2026 እና 2026-2027 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ካላንደር (የቀን መቁጠሪያ) ግብረመልስ


መምህርት እና አሰልጣኝ ስተፋኒ ሊዛማ/Steffany Lizama ላቲናዎችን በ STEM እና በስፖርት አነቃቅታለች።

ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15 የተዘከረው የሂስፓኒክ ቅርስ ወር አካል በመሆን—MCPS በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያሉትን በርካታ የሂስፓኒክ ባህሎች፣ አስተዋጾ፣ እና ብዝሃነትን ያንፀባርቃል። ስተፋኒ ሊዛማ/Steffany Lizama፣ STEM አስተማሪ እና የሴቶች ፍላግ እግር ኳስ አሰልጣኝ በቤተዝዳ-ቼቪ ቼዝ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ተማሪዎችን የተዛባ አመለካከትን እንዲቃወሙ መነቃቃት ፈጥራለች። ስለ ታሪኳ የበለጠ ያንብቡ። 


ለወጣቶች የአየር ንብረት ተቋም እስከ ኦክቶበር 4 ማመልከቻዎች መቅረብ አለባቸው።

ለአየር ንብረት ተቋም የመጀመሪያ ምረቃ ምዕራፍ ማመልከት የሚፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እስከዓርብ፣ኦክቶበር 4ማመልከቻቸውን ማቅረብ አለባቸው። ይህ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚካሄድ ፕሮግራም ስለ አየር ንብረት ሳይንስ፣ተጽእኖዎችን እና መፍትሄዎችን ለተማሪ መሪዎች ያስተምራል። ተማሪዎች ስለ ካባቢ የአየር ንብረት፣ስለ ምግብ መባከን፣እና ስለ ፈጣን ፋሽን ጭምር በተለያዩ የአየር ንብረት ርእሶች ላይ መግለጫ ይሰጣቸዋል፤እንዲሁም በፓናል ውይይቶች እና ዌብናሮች ላይ ይሳተፋሉ። በአካባቢያቸው የተነደፉ የድርጊት መርሃ ግብሮችን ለማጠናቀቅ ከአየር ንብረት ባለሙያዎች ጋር አብረው ይሰራሉ። ከኦክቶበር 15 ጀምሮ ማክሰኞ ምሽቶች ላይ በሚከተሉት አድራሻዎች ስብሰባዎች የሚካሄዱ ስለሆነ በአካል ተገኝተው መሳተፍ ይችላሉ፦ Brookside Gardens in Wheaton ወይም Lathrop E. Smith Environmental Center in Rockville

ማመልከቻው እዚህይገኛል።

ጥያቄ ካለዎት ለ፦Lee Derby ወይም Liz Bullock ኢሜይል ያድርጉ።


ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

MCPS ስለ ተማሪዎች እና ስለ ሰራተኞች ንግግር እና አገላለጽ የተሻሻለ መመሪያ አውጥቷል። እዚህ ማንበብ ይችላሉ። እንዲሁም፣የማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ ትምህርት እንዴት እንደሚሰጥ የበለጠ ለማወቅበማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ ስርአተ ትምህርት ምሽቶች ላይ ለመሳተፍ መመዝገብ እንዳለብዎት ያስታውሱ።




ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)