የማህበረሰብ ተሳትፎ በሚካሄዱባቸው ዝግጅቶች ላይ ይቀላቀሉን!
ሱፐርኢንተንደንት ቶማስ ቴለር/Superintendent Thomas Taylor በተቻለ መጠን ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ ለማወቅ ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት እንደቀጠለ ነው። ከቀጣዮቹ ሁለት የማህበረሰብ ተሳትፎ ክፍለ ጊዜያት አንዱን ቀን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፦
በስፓንሽኛ እና በአሜሪካ የምልክት ቋንቋ የማስተርጎም አገልግሎት ይሰጣል።
ክፍለ-ጊዜዎቹ ወላጆችን፣ተማሪዎችን፣ሰራተኞችን እና የማህበረሰብ አባላትን ከሱፐርኢንተንደንቱ ጋር እንዲገናኙ እና ስለ ዲስትሪክቱ ስራዎች እና የትምህርት ጉዳዮችን በሚመለከቱ ሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።
በነዚህ ክፍለጊዜያት ተሰብሳቢዎች በንግግር አስተያየት የመስጠት እድል ይኖራቸዋል። አስተያየቶቻቸውን ዲጂታል ማቅረብ የሚፈልጉ ሰዎች ይህን Google form ተጠቅመው ማቅረብ ይችላሉ።
ኤይንስታይን/Einstein የትርኢት ባንድ ኦክቶበር 19 ትርኢቶችን ያቀርባል።
በዚህ አመት 14 የትርኢት ባንዶች የሚሳተፉበት ዝግጅት ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 19 ከቀትር እስከ 3፡30 ፒ.ኤም በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ትርኢቶችን የሚያቀርቡት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባንዶች፦ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ክላርክስበርግ፣ደማስከስ፣ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ ኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር፣ኖርዝዉድ፣ፔይንት ብራንች፣ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ሮክቪል፣ሴኔካ ቫሊ፣ስፕሪንግብሩክ፣ዋትኪንስ ሚል እና አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ናቸው። በተጨማሪ ከመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጅምላ ባንድ ትርኢትም ይኖራል።
ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለህዝብ ክፍት ነው። አድራሻ፦ 11135 Newport Mill Road in Kensington. በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦች "Fine Arts X feed @MCPSArts" ላይ ይለጠፋሉ።
ለ MCPS ወላጆች እና ተንከባካቢዎች ነፃ የወላጅ ድጋፍ ይገኛል።
MCPS ከወላጆች የማበረታቻ ፕሮግራም (PEP) ጋር ያለውን አጋርነት የቀጠለ ሲሆን፣ለትርፍ ያልተቋቋመ በአካባቢያችን የሚገኝ ድርጅት ለወላጆች እና ለተንከባካቢዎች መገልገያዎችን/ሪሶርሶችን እና ድጋፎችን ይሰጣል። PEP የቤተሰብ ጥንካሬ ፕሮግራምበነፃ፣በኦንላይን የሚሰጥ የስምንት ሳምንት ፕሮግራም ሲሆን ይህም ወላጆች እና ተንከባካቢዎች የቤተሰብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር፣ የልጆችን የአእምሮ ጤንነት ለመደገፍ እና በትምህርት ቤት የተማሪዎችን ስኬት የሚያበረታቱ እውነታዎችን እንዲማሩ የሚረዳ ነው። ቢያንስ አምስት ክፍለ ጊዜዎችን በመሣተፍ እና ግምገማውን በመሙላት $50 ዶላር የስጦታ ካርድ ያገኛሉ። ዝግጅቶቹ የሚጀምሩት ኦክቶበር 14 ሲሆን በእንግሊዝኛ፣ በስፓንሽኛ፣ እና በአማርኛ ይካሄዳሉ። ይመዝገቡ/Register።
በማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የሂስፓኒክ ቅርስ ተምሣሌት
ዴይሲ ካስትሮ/Daysi Castro በማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የማስተማር ባለሙያ ስትሆን፣ ከፍተኛ ትጋት እና ፍቅር በማሳየት የተማሪዎችን እና የቤተሰቦችን ህይወት መቀየር የቻለች የትምህርት ባለሙያ ነች። የካስትሮ ታሪክ ከሂስፓኒክ ማንነት ቅርስ ጋር በጥልቅ የተሳሰረ ነው። የተወለደችው በኤል ሳልቫዶር/El Salvador ሲሆን ወደ አሜሪካ የመጣችው ገና 2 ዓመት እድሜ ላይ ነው። ወላጆቿ ጠንካራ የሥራ ትጋትን እና ለትምህርት ቁርጠኝነትን አስርፀውባታል። ታሪኳን ያንብቡ።
ኦክቶበር 26 ለሚካሄደው የጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ አሁን ይመዝገቡ
ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንሱ ቅዳሜ፣ኦክቶበር 26 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ እኩለቀን ድረስ በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ Montgomery College, Germantown Campus, Globe Hall, 20200 Observation Drive, in Germantown.
ይህ በነፃ ምክር የሚለገስበት ኮንፈረንስ ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ጥቁር ወይም አፍሪካዊያን አሜሪካዊያን እና ላቲኖ ወይም ሂስፓኒክ ወንድ ተማሪዎች ላይ ያተኮረ ነው። የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “አለም ወደፊት እየገሰገሰ ነው!/The World is Shifting Forward! ወደፊት በማተኮር ተወዳዳሪ ይሁኑ።
የወላጆች አውደጥናት ከጠዋት a.m., ጀምሮ በየግማሽ ሰዓቱ ይካሄዳል፤የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ 11፡30 a.m. ላይ ይካሄዳል።
“ተፎካካሪ መሆን ጨዋታ ቀያሪ ነው፤ አሸናፊ ለመሆን እና የወደፊት ዕጣ ፈንታህ(ሽ)ን ለመወሰን እንዴት ትወዳደራለህ/ትወዳደሪያለሽ?” በሚለው የኮንፈረንሱ ጭብጥ ሃሳብ ላይ በመሰረት ተማሪዎች 300 ቃላት ድርሰት ጽፈው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ድርሰቶቹ ሰኞ፣ ኦክቶበር 21 በኢሜይል መቅረብ አለባቸው።
ለተጨማሪ መረጃ፦ ዶ/ር ኤቨርት ዴቪስ/Dr. Everett Davis፣የተማሪዎች፣የቤተሰብ እና የትምህርት ቤቶች አገልግሎት ዳይሬክተር፣ወይም ዶ/ር ኬረን ዲ. ክረውስ/Dr. Karen D. Crews፣የተማሪዎች ደህንነት እና ስኬት ዳይሬክተር ያነጋግሩ።
ተማሪዎች እና ወላጆች እዚህመመዝገብ ይችላሉ።
ለተማሪዎች የተለያዩ እድሎች አሉ
ለተማሪዎች የሚከተሉት የአመራር እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚከናወኑ እድሎች ይኖራሉ፦
ስለ ጤና ትምህርት አቀንቃኝነት፦MCPS ውስጥ በተማሪዎች ጤና እና ደህንነት ላይ ለውጥ ማምጣት ይፈልጋሉ? ስለ አዲሱ ካውንቲ አቀፍ በተማሪዎች-የሚመራ የትምህርት ቤቶች የጤና ካውንስል የበለጠ ለማወቅ እሮብ፣ ኦክቶበር 16 ከሠዓት በኋላ 6:30–7 p.m. በሚካሄደው ዙም ስብሰባ ይሳተፉ። ተጨማሪ መረጃ
ጥያቄ ካለዎት፣ወደ Dr. Cara Grant ቅድመ መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የጤና እና አካል ማደበር ትምህርት ሱፐርቫይዘር ኢሜል ያድርጉ።
መከባበርን መምረጥ የተማሪዎች አማካሪ ካውንስል፦ የፍቅር ውሎ ላይ ጥቃትን መከላከል ካውንስል ውስጥ ተመርጠው ማገልገል ለሚፈልጉ ተማሪዎች ማመልከቻ ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው። የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን ሰኞ፣ ኦክቶበር 14 ነው። እዚህ ያመልክቱ። ጥያቄ ካለዎት፣ ለAshley Noy ኢሜይል ያድርጉ።
በግልጽ ይናገሩ፣ህይወት ያድኑ፦የስቴት አቃቤ ህግ ቢሮ“Speak Up, Save a Life” በሚል ርዕስ የመወዳደርያ ቪዲዮ PSA በማዘጋጀት/በማቅረብ ተማሪዎች እንዲወዳደሩየመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ተጋብዘዋል። ቪዲዮዎቹ አደንዛዥ እጾችን፣ኦፒዮይድስ፣እና ፌንታኒል የመጠቀም አደጋዎች ላይ ማተኮር አለባቸው። የሚሳተፉ ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፤ ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ዶላር ነው። የመወዳደሪያ ግብአቶች አርብ፣ ኖቬምበር 8 እስከ እኩለ ሌሊት መቅረብ አለባቸው። የውድድር ግብአቶች ጥያቄ ካለዎት፣ኢሜልይላኩ።
KID ሙዚየም ለቤተሰቦች ሁለት እድሎችን አዘጋጅቷል፦
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰሪት ምሽት/Middle School Maker Night፡ ዓርብ፣ ኦክቶበር 18፣ከሠዓት በኋላ 5-8 ፒ.ኤም ይካሄዳል እዚህ ይመዝገቡ።
ሰኞ፣ኖቬምበር 4 ትምህርት ቤት ዝግ ሲሆን ሙዚየሙ 2ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች 9 a.m.–4 p.m. ክፍት ይሆናል።እዚህ ይመዝገቡ። ስኮላርሺፖች ይኖራሉ።
ለአንድ ቀን የካውንስል አባል ለመሆን አመልክት(ቺ)
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክርቤት አባል ዊል ጃዋንዶ/Will Jawando ሁሉም የመለስተኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ዲጂታል ታሪኮችን በማጋራት ለተሻለ ማህበረሰብ ያላቸውን ራዕይ በማካፈል 9ኛው አመታዊ የምክር ቤት አባል ቀን ተግዳሮትላይ እንዲሳተፉ ያበረታታሉ። የቪዲዮ ድርሰት ማቅረቢያው ሀሙስ፣ ኖቬምበር 7 ነው። አሸናፊው በምክር ቤት ይሸለማል/ትሸለማለች፣ እና ለአንድ ቀን የምክር ቤቱ የክብር አባል በመሆን ያገለግላል/ታገለግላለች። እዚህ ያቅርቡ።
2025 የዜጎች ክብር ሽልማት እጩዎችን ለመጠቆም አሁን ክፍት ነው።
"Congressional Medal of Honor Society" ለ 2025 ሽልማቶች እጩዎች እንዲጠቆሙ ይፈልጋል—ሁለቱ ለወጣቶች የተዘጋጁ ሽልማቶች ናቸው።
የማመልከቻው ቀነ-ገደብ እሑድ፣ ዲሴምበር 1 ነው፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት የሚካሄደው ማክሰኞ፣ ማርች 25, 2025 በዋሽንግተን ዲ.ሲ. ነው።
በጌትስበርግ እና ሮክቪል ለሚገኙ ተማሪዎች ካጋን ሴናተርያል ስኮላርሺፕ/Kagan Senatorial Scholarships አሁን ለማመልከት ክፍት ነው።
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለስፕሪንግ 2025 የሜሪላንድ ስቴት ሴናተር ቼሪል ካጋን/Maryland State Senator Cheryl Kagan የህግ አውጭ ስኮላርሺፕ "legislative scholarships" አሁን ማመልከት ይችላሉ። ስኮላርሺፑ የሚሰጠው ፍላጎትን እና ተገቢነትን መሠረት ያደረገ ነው። ተማሪዎች የዲስትሪክት 17 (ጌትስበርግ ወይም ሮክቪል) ነዋሪዎች መሆን አለባቸው። ማመልከቻዎች ሐሙስ፣ኦክቶበር 24 ከቀኑ 5 ፒ.ኤም በፊት መቅረብ አለባቸው ። እዚህ ያመልክቱ። ጥያቄዎችን እዚህ ማቅረብ ይችላሉ።
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን፦ Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይከታተሉ።
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org