ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች C-SPAN ብሄራዊ የዘጋቢ ቪድኦ ውድድር ተከፍቷል።
6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች "StudentCam" የተሰኘ C-SPAN ዓመታዊ ዘጋቢ የቪድዮ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፣ይህ ቪድኦ አዘጋጅተው የሚሣተፉበት ውድድር ተማሪዎቻችን ማህበረሰባችንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንዲያስቡ ያበረታታል።
በዚህ አመት ተማሪዎች “ለፕሬዝዳንቱ ያላችሁ መልእክት” በሚል የውድድሩ መሪ ሃሳብ ላይ ተሞርኩዘው ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ሠርተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል። ተማሪዎች በግል ወይም በቡድን መወዳደር ይችላሉ።
የማስረከቢያው ቀነ-ገደብ ሰኞ፣ ጃኑዋሪ 20, 2025 የፕሬዚደንት በዓለ ሲመት ቀን ነው። C-SPAN ምርጥ ዘጋቢ ቪድኦ አዘጋጅተው ላቀረቡ 150 ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል።
በታሪክ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በዚህ ውድድር ጥሩ አፈጻጸም እንዳላቸው ይታወቃል። ባለፈው ዓመት፣ አንድ የሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 9ኛ ክፍል ተማሪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኢስት ዲቪዝዮን ሽልማትእና በ 2023፣ሁለት የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ታላቁን ሽልማት/Grand Prize ወስደዋል።
ስለ ህይወትዎ ትንሽ ድራማ ይተውኑ!
በመካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፎል ቲያትር እና የዳንስ ፕሮዳክሽን መጋረጃዎች እየተከፈቱ ናቸው። እስከ 2025 መጀመሪያ ድረስ የሚካሄዱትን ምርጥ ትርኢቶች ለማየት አሁኑኑ ያቅዱ።
ከ"Mamma Mia" እና "A Midsummer Night's Dream" እስከ "Charlotte's Web" እና "SpongeBob the Musical" ለሁሉም የሚሆን አስደሳች እና አዝናኝ ዝግቶች ይኖራሉ። ይምጡ!
2024-2025 ፎል የቲያትር/የዳንስ ፕሮዳክሽን
መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር
በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ጽ/ቤት በ 2019 የመታሰቢያ እና እርቅ ኮሚሽን የተቋቋመው በካውንቲ ውስጥ ስለ አፍሪካውያን አሜሪካውያን ታሪክ እና ትሩፋት የተሻለ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው። MCPS ስለ መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበትን ወር ከመዋእለ ህጻናት እስጀ አሥራሁለተኛ ክፍል (K-12) ስለ አካባቢው አፍሪካን አሜሪካን ታሪክ እና የነጻነት ቀን በሚመለከት አጫጭር ታሪክ በማስተማር ማክበር ከተጀመረ ይህ ሶስተኛ አመት ነው።
ከዚህ በታች ያሉት መጪዎቹ የዚህ አመት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዝግጅቶች ናቸው፤ (ሌሎች በዓላት ወደፊት በኖቬምበር ወር ይመጣሉ)፦
በ"Button Farm Living History Center" የሚካሄድ የነጻነት ቀን ክብረ በዓል፥ አድራሻው ይሄ ነው፦ (16820 Black Rock Road, Germantown)
ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 26 ከቀትር እስከ 3 p.m.
ተማሪዎች እስከ 3 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
ሳንዲ ስፕሪንግ ስሌቭ ሙዚየም - ሜሪላንድ የነጻነት ቀን
እውነተኛው ጁንተንዝ "The Real Juneteenth" ቨርቹዋል የሚካሄድ ዝግጅት
ረቡዕ፣ ኦክቶበር 30 ከሠዓት በኋላ 6:45-8 p.m.
ተማሪዎች እስከ 1.5 SSL ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
የመመዝገቢያ አገናኝ መረብ/ሊንክ (ቨርቹዋል ስብሰባ መግቢያ/ሊንክ ለማግኘት መመዝገብ አለብዎት።)
በራሪ ጽሑፍ
በሳንዲ ስፕሪንግ ስሌቭ ሙዚየም የሚካሄድ የነጻነት ቀን ክብረ በዓል፥ አድራሻው ይሄ ነው፦ (18524 Brooke Road, Sandy Spring)
ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 2 ከቀትር እስከ 3፡20 p.m.
ተማሪዎች እስከ 3 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት (SSL) ማግኘት ይችላሉ።
የከተማ እርሻ የበጎ ፈቃደኞች ዝግጅት ኖቬምበር 9 በሎደርማን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል
የመካከለኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 9 ቀን ከጠዋት 9 am. እስከ 2 p.m. ቬተራንስ ዴይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ዝግጅቱ የሚካሄድበት አድራሻ፦ A. Mario Loiederman Middle School, 12701 Goodhill Road in Silver Spring. ተማሪዎች REACH Hub ለሚገነባው የመጀመሪያው የከተማ እርሻ የአትክልት አልጋዎችን እና አግዳሚዎችን በመሥራት ይረዳሉ እንዲሁም በዚህ ዘርፍ ከሚሠሩ ባለሙያዎች ትምህርት ያገኛሉ። SSL ሰዓት እና ምሳ ይሰጣል። ምዝገባ
የማህበረሰብ ስብሰባዎች የስድስት ትምህርት ቤቶችን የእግር ጉዞ ትምህርት/‘Walkability Studies’ እና የደህንነት ፍላጎቶችን በሚመለከት ይወያያሉ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (MCDOT) በአካል ተገናኝተው የእግር ጉዞ ጥናትና ግኝቶችን ለማቅረብና ለመወያየት ወደ ስድስት ትምህርት ቤቶች በእግር እና በብስክሌት ለሚጓዙ ተማሪዎች የእግረኛ መንገድ እና የደህንነት ፍላጎቶችን ለመወያየት በአካል ስብሰባዎችን ያካሄዳሉ። ጥናቶቹ፦ ኬንሲንግተን ፓርክውድ፣ ሌክ ሴኔካ፣ ዋተርስ ላንዲንግ፣ ሮዝመሪ ሂልስ፣ እና የሮክ ክሪክ ፎረስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን ጁንየር ትምህርት ቤቶችን ያካትታሉ። መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ስብሰባዎች የሚካሄዱባቸው ቦታዎች—
ረቡዕ፣ ኦክቶበር 23, ከምሽቱ 6: 30 P.M, በዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አድራሻ፦13737 Wisteria Drive፣ Germantown ጥናቶቹ የሚያካትቱት፦ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ሌክ ሴኔካ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና ዋተርስ ላንዲንግ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችናቸው።
ሐሙስ፣ ዲሴምበር 5 ከሠዓት በኋላ 6፡30-8፡30 p.m., አድራሻ፦ Rosemary Hills Elementary School, 2111 Porter Road, Silver Spring. የሮዝመሪ ሂልስ አንደኛ ደረጃ እና የሮክ ክሪክ ፎረስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጥናቶችን በተመለከተ የሚካሄድ ነው።
የከንሲንግተን ፓርክውድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስብሰባ ኦክቶበር 9 ተካሄዷል። የበለጠ ለማወቅ እዚህያንብቡ።
የፎል የወላጅ አካዳሚ መርሃ ግብር የጊዜ ሠሌዳ አሁን የተዘጋጀ በመሆኑ
ቤተሰቦች እና ተማሪዎች በትምህርት አመቱ በሙሉ ከወላጅ አካዳሚ TO GO ለቤተሰቦች በተዘጋጁ ተከታታይ ነፃ ቨርቹዋል ዌብናርስ መጠቀም ይችላሉ። ኦክቶበር፣ኖቬምበር እና ዲሴምበር ዌብናሮችን አሁን በወላጅ አካዳሚ ድረገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል። ርእሶቹ፥ የመኝታ ጊዜ ጭቅጭቆችን መቆጣጠር፣ የተሻለ የግንኙነት ክህሎቶችን መማር፣ እና የበላይነት ትግልን ለማምከን/ለማለስለስ የሚረዱ ዘዴዎችን መማር እና ተስፋ አስቆራጭ ክስተቶችን መቆጣጠርን ያካትታሉ። ለመመዝገብ እዚህ ይክፈቱ።
የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ወቅት ተቃርቧል!
የመጀመሪያውየፒክልቦል "pickleball"ድህረ ውድድር ሰኞ፣ ኦክቶበር 21 እና ረቡዕ፣ ኦክቶበር 23 ይካሄዳል።የግማሽ ፍፃሜ እና የፍጻሜ ጨዋታዎች ኦክቶበር 23 ቤተዝዳ በሚገኘው ዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። መርሃ ግብሩን ይመልከቱ።
የመጀመርያው የሴት ልጆች የባንዲራ እግር ኳስ/girls’ flag football የካውንቲ ሻምፒዮና ውድድር ኦክቶበር 28 እና ኖቬምበር 4 በሚውልበት ሳምንታት ይካሄዳል። የስቴት ሻምፒዮና ውድድር ዓርብ፣ኖቬምበር 8 ይካሄዳል። የውድድሮቹን መርሃ ግብር አጠቃላይ ዝርዝር ይመልከቱ።
"cheerleading, cross country, field hockey, football, golf, soccer and volleyball" በፎል የሚካሄዱ ጫወታዎች እና የውድድር መርሃ ግብሮችንእዚህይመልከቱ።
ማሳሰቢያዎች
የአእምሮ ጤና ሪሶርስ አውደ ርዕይ፦ ይህ ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ እና ለሰራተኞች ክፍት የሆነ ዝግጅት ቅዳሜ፣ኦክቶበር 26፣ከጠዋቱ 10 a.m.- 2p.m. ድረስ በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል።አድራሻው፦ Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown መጓጓዣ ይቀርባል። ይመዝገቡ/RSVP.
ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ፦ይህ ነጻ ዝግጅት 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ጥቁር ወይም አፍሪካን አሜሪካን እና ላቲኖ እና ሂስፓኒክ ወንድ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን ቅዳሜ ኦክቶበር 26 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ Montgomery College, Germantown Campus, Globe Hall, 20200 Observation Drive ተማሪዎች እና ወላጆች እዚህመመዝገብ ይችላሉ።
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን፦ Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይከታተሉ።
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org