መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 24, 2024

"Google እና Discovery Education" ኖቬምበር 9 ነፃ STEM የቤተሰብ ቀን ያስተናግዳሉ።

Google እና Discovery Education ነፃ STEM የቤተሰብ ቀን የሚካሄደው ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 9 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m.-4 p.m. ጀርመንታወን በሚገኘው የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ካምፓስ ነው።(Montgomery College, Germantown Campus)

ዝግጅቱ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ክፍት ሲሆን፣አይነተኛ በተግባር ላይ የሚውሉ STEM ተግዳሮቶችን እና እንቅስቃሴዎችን እና የዲጂታል ትምህርት ተሞክሮዎችን ከነባራዊ እውነታ አፕሊኬሽኖች ጋር ያቀርባል። እንዲሁም በመኪና የሚቀርቡ ምግቦች፣ ጨዋታዎች፣ እና ራፍሎች ይኖራሉ።

ዝግጅቱ የሚከናወንበት ቦታ አድራሻው ይህ ነው፦ High Technology and Science Center on Germantown Campus, 20200 Observation Drive in Germantown. ይመዝገቡ/Register.

STEM የቤተሰብ ቀን 2024


ስለ FY26 ካፒታል በጀት እና 2025-30 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም የባጀት ማሻሻያዎችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)የሱፐርኢንተንደንቱFY 2026 ካፒታል በጀት እና FY 2025–2030 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የትምህርት ቦርድ ቀርቧል።

የካፒታል በጀት በተዘጋጀበት ወቅት፣ MCPS ለቻርለስ ኢ ዉድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ከስቴት ድጋፍ ለመጠየቅ በተያዘው የካፒታል በጀት ላይ $39.3 ሚሊዮን ዶላር የበጀት እጥረት መኖሩን ተገንዝበናል። ከ 2021 ጀምሮ፣ MCPS በተለያዩ የፕሮጀክት አፈጻፀም ደረጃዎች የምንዳ ክፍያዎችን እና የጨረታ ዋጋዎችን በሚመለከት የተሳሳተ ስሌት ተደርጓል። ይህ ስህተት ሙሉ በሙሉ የ MCPS ነው። ዲስትሪክቱ ከተጠናቀቁት የካፒታል ፕሮጀክቶች ወጪ ያልተደረጉ ገንዘቦችን በማፈላለግ የበጀት ክፍተቱን ለመቅረፍ በንቃት እየሰራ ነው። እነዚህ የበጀት ማቀናነስ ሥራዎች የነዚያን የታቀዱ ፕሮጀክቶችን ማሻሻያዎች ወይም የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎችን አይነኩም።

ዲስትሪክቱ ያቀረበውን ያንብቡ
ከትምህርት ቦርድ የተሰጠውን መግለጫ ያንብቡ። 


መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር

MCPS መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበትን ወር ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ ክፍል (K-12) ስለ አካባቢው አፍሪካን አሜሪካን ታሪክ እና የነጻነት ቀን በሚመለከት አጫጭር ታሪክን በማስተማር ማክበር ከጀመረ ይህ ሶስተኛ አመቱ ነው። የመታሰቢያ እና የእርቅ ኮሚሽኑ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ የተቋቋመው በ 2019 ነው።

MCPS መጪዎቹን የዚህ ዓመት ዝግጅቶች ከዚህ በታች አቅርቧል።

ሳንዲ ስፕሪንግ የባርነት ሙዚየም እና የአፍሪካ አርት ጋለሪ የሜሪላንድ የነጻነት ቀን ክብረ በዓል በሚከተለው አድራሻ ላይ ይካሄዳል፦ (18524 Brooke Road, Sandy Spring)
ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 2 ከቀትር እስከ 3፡20 p.m.
በራሪ ጽሑፍ

ብራውን vs የትምህርት ቦርድ MCPS ላይ ያለው ተጽእኖ
ረቡዕ፣ ኖቨምበር 6፣ 7-8 p.m.
የዌቢናር ዙም ምዝገባ፣ለህዝብ ክፍት ተደርጓል
ትሬሲ ኦሊቨር-ጋሪ/Tracy Oliver-Gary ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) የማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ ሱፐር ቫይዘር፣ MCPS ለብራውን vs. የትምህርት ቦርድ ውሳኔን እንዴት ምላሽ እንደሰጠ ንግግር ያደርጋሉ።

አመታዊ ጨዋታ ቀያሪ አውደ ጥናት
ሐሙስ፣ ኖቬምበር 14, 6:30-8 ፒ.ኤም
ተማሪዎች እስከ 2 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት (SSL) ማግኘት ይችላሉ።
ዙም የዌቢናር ምዝገባ አገናኝ/Link
በራሪ ጽሑፍ
ዋና ተናጋሪው(ዋ) ኢላና ትራችትማን/Ilana Trachtman የዘጋቢ ፊልሙ ዳይሬክተር፣Ain't No Back to a Merry-Go-Round፣የግሌን ኢኮ/Glen Echo መዝናኛ ፓርክ ነጻ መሆንን የሚያሳይ ፊልም ነው።


KID ሙዚየም ከትምህርት በኋላ፣ የአገሬው ተወላጅ አሜሪካውያን የመታሰቢያ ቅርስ ወር ፕሮግራሞችን ያቀርባል

KID ሙዚየም የሚከተሉት ከትምህርት በኋላ 3 ቤተዝዳ ሜትሮ ሴንተር/3 Bethesda Metro Center እና ዴቪስ ላይብረሪ (Davis Library) የሚካሄዱ ፕሮግራሞች አሉት። ጥያቄ ከቀረበ ስኮላርሺፖች ይኖራሉ። 

ከመዋእለ ህጻናት እስከ 1ኛ ክፍል፡ የፈጠራ ጥበብ ቤተ ሙከራ
ከ 2ኛ እስከ 4ኛ ክፍል፡ ውድድር ይኖራል!
ከ 5ኛ እስከ 7ኛ ክፍሎች፡ Fab Lab Skills ክህሎትን መገንባት
ተጨማሪ መረጃ እና ምዝገባ

የአገሬው ተወላጅ አሜሪካውያን የቅርስ መዘከሪያ ክብረበዓል

እሑድ፣ ኖቬምበር 3, 10 a.m.-4 p.m.
"hoop dance" ዳንስ ቤተሰብን በሙሉ የሚያካትቱ አውደ ጥናቶች፣ የቁሳቁስ አውደ ርእዮች እና አስደሳች እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፉ። ተጨማሪ መረጃ


የዊንተር (የክረምት) ጃኬት እርዳታ በመሰብሰብ ላይ ነው

የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ቢሮዎች ለተቸገሩ ተማሪዎች አዳዲስ ጃኬቶችን እንዲለግሱ እየጠየቁ ነው። ለትናንሽ ልጆች ኮፍያ፣ ጓንት፣ እና ቦት ጫማዎች ያስፈልጋቸዋል። በልካቸው 5, 6, 7, እና 8 የሆኑ ጃኬቶች ለወንዶች እና ለሴቶች ልጆች በጣም አስፈላጊ ናቸው። በእርዳታ የሚሰጡ እቃዎችን በዚህ አድራሻ ማቅረብ ይችላሉ፦ Rocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 141, Rockville, Md., 20852. ከሰኞ እስከ አርብ 9 a.m.–5 p.m., ድረስ በአካል ማምጣት ወይም በኦንላይን ማዘዝ እና እቃዎቹ ወደ ሮኪንግ ሆርስ ሮድ ሴንተር እንዲደርሱ ማድረግ ይችላሉ።

ጥያቄ ካለዎት በስልክ ቁጥር 240-550-2615 ደውለው Lisa Conlonያነጋግሩ።


የስፖርት አፍቃሪዎች እንዳያመልጥዎ!

የመጀመርያው የሴት ልጆች የባንዲራ እግር ኳስ/girls’ flag football የካውንቲ ሻምፒዮና ውድድር ኦክቶበር 28 እና ኖቬምበር 4 በሚውልበት ሳምንታት ይካሄዳል። የስቴት ሻምፒዮና ውድድር ዓርብ፣ኖቬምበር 8 ይካሄዳል። የውድድሮቹን መርሃ ግብር አጠቃላይ ዝርዝር ይመልከቱ።

"cheerleading, cross country, field hockey, football, golf, soccer and volleyball" በፎል የሚካሄዱ ጫወታዎች እና የውድድር መርሃ ግብሮችንእዚህይመልከቱ።


ማሳሰቢያዎች

የአእምሮ ጤና ሪሶርስ አውደ ርዕይ፦ ይህ ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ እና ለሰራተኞች ክፍት የሆነ ዝግጅት ቅዳሜ፣ኦክቶበር 26፣ከጠዋቱ 10 a.m.- 2p.m. ድረስ በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል።አድራሻው፦ Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown መጓጓዣ ይቀርባል። ይመዝገቡ/RSVP. ይህ ዝግጅት በቀጥታ የሚተላለፍ ስለሆነ እዚህ (እንግሊዝኛ/English) እና እዚህ (በስፓንሽኛ/en Español)ይመልከቱ። 

ለአርበኞች ቀን ክብረ በዓል በበጎ ፈቃደኝነት የማገልገል እድል፦የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 9 ከጠዋቱ 9 a.m.- 2 p.m. A. Mario Loiderman Middle School,12701 Goodhill Road, Silver Spring ተገኝተው አገልግሎት መስጠት ይችላሉ። ተማሪዎች፥ REACH (Resilience, Education, Action, Climate, Habitat) Hub at Loiederman ለሚሠራው የመጀመሪያው የከተማ እርሻ የአትክልት አልጋዎችን እና ወንበሮችን በመገንባት ይረዳሉ። SSL ሰዓት እና ምሳ ይኖራል።ምዝገባ


የራሳቸውን ከበሮ እየደለቁ ሰልፍ መውጣት

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በአንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተደረገው የማርች ባንድ ትርኢት ላይ አስራ አራት የመካከለኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንዶች ተሳትፈዋል። የፎተፍራፍ ክምችት ይመልከቱ!




ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)