የMCPS ትምህርት ቤቶች በNICHE የደረጃዎች ዝርዝር የላቀ ውጤት አምጥተዋል
ሶስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) በNiche (ብሄራዊ የትምህርት ቤት እና የኮሌጅ መፈለጊያ መድረክ) በተሰጠው ደረጃ መሰረት በሜሪላንድ ውስጥ ከሁሉም የላቁ ትምህርት ቤቶች የሚል እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በቅርብ ጊዜ በNiche በተሰጡ ደረጃዎች ላይ፣ ተጨማሪ 18 የMCPS ትምህርት ቤቶች- በአንደኛ ደረጃ፣ በመካከለኛ ደረጃ፣ እና በሁለተኛ ደረጃ- ለ2025 በሜሪላንድ ውስጥ ያሉ ምርጥ የህዝብ ትምህርት ቤቶች በሚለው ስር በምርጥ 10 ዝርዝር ውስጥ ተቀምጠዋል።
Poolesville ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሜሪላንድ ውስጥ ቁጥር አንድ የሕዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተብሎ ተመርጧል። Walt Whitman, Winston Churchill, Thomas S. Wootton, Richard Montgomery እና Bethesda-Chevy Chase ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከPoolesville ጋር በምርጥ 10 ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል። i Northwest, Montgomery Blair, Quince Orchard, Clarksburg እና Sherwood ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በምርጥ 25 ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል።
Cabin John መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስቴቱ ውስጥ ቁጥር አንድ መካለለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተብሎ ተለይቷል። Thomas W. Pyle, Robert Frost, Herbert Hoover እና North Bethesda መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም በዚህ ደረጃ በምርጥ 10 የትምህርት ቤቶች ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል። በምርጥ 25 ዝርዝር ውስጥ የገቡት Takoma Park, Westland, John Poole, Lakelands Park, Hallie Wells and Tilden መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው።
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃ፣ ዘጠኝ የMCPS ትምህርት ቤቶች በምርጥ አስር ደረጃዎች ውስጥ እውቅና አግኝተዋል፣ Westbrook የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ተብሎ ተሰይሟል። በተከታይነት የተቀመጡት Stone Mill, Seven Locks, Wayside, Ritchie Park, Carderock Springs, Cold Spring, Diamond እና Burning Tree የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው። ምርጥ 25 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተብለው ከተሰየሙት ውስጥ Bells Mill, Chevy Chase, Potomac, Wyngate, Kensington Parkwood, Bradley Hills, Bannockburn, Fallsmead, Wood Acres, Lakewood እና Travilah የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል።
በአጠቃላይ፣ MCPS በሜሪላንድ ሁለተኛው ምርጥ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት እና በሜሪላንድ ውስጥ ላሉ አትሌቶች ሁለተኛ ምርጥ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ተብሎ እውቅና ተሰጥቶታል።
እንደ ኒቼ ከሆነ፣ እነዚህ ደረጃዎች የአካደሚክ አፈጻጸምን፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጪ ለሆነ ተግባር/እንቅስቃሴ ያሉ እድሎችን፣ እንደ U.S. Department of Education ካሉ ምንጮች የተገኙ መረጃዎችን እና አሁን ካሉ ተማሪዎች፣ ከቀድሞ ተማሪዎች እና ከወላጆች የተገኙ የተጠቃሚ ግብዓትን ጨምሮ በNiche በተተነተኑ በበርካታ ነገሮች ዙሪያ የMCPን’ ልዩ/ወደር የሌለው አፈጻጸም ያንጸባርቃሉ።
በደረጃዎቹ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሚቀጥለውን ይጎብኙ፡Niche።
የMCPS ቺርሊደሮች በ36ኛው ዓመታዊ የቺርሊዲንግ ውድድር ላይ ደምቀው ታይተዋል
ኦክቶበር 26 በMontgomery Blair ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው 36ኛው ዓመታዊ የቺርሊዲንግ ውድድር ላይ ከ25 የMCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ቡድኖች አስደናቂ ትርዒቶችን አሳይተዋል። ቡድኖቹ በክብደት ደረጃ፣ በቴክኒክ እና በአፈጻጸም ላይ ተገምግመዋል። ውድድሩ የቡድኖቹን ተሰጥዖ ያሳየ ሲሆን ደጋፊዎችም ቡድኖቹን እንዲደግፉ እድል ሰጥቷቸዋል።
በMCPS የቺርሊዲንግ ቻምፒዮንሺፕ ላይ የላቀ ውጤት ባመጡት እና የእነሱን ተሰጥዖ ባሳዩት በተማሪ-አትሌቶቻችን በጣም እንኮራለን” ሲሉ የስርአት አቀፍ የአትሌቲክስ ዳይሬክተር/Systemwide Athletics Director ጄፍሪ ሱሊቫን ተናግረዋል። ''የስታንት ትርዒታቸው፣ አክሮባቲክ እንቅስቃሴዎቻቸው እና በንቁ ስሜት የተሞላው እንቅስቃሴዎቻቸው የእኛን በንቁ ስሜት የተሞላ የR.A.I.S.E. መሰረታዊ ዕሴቶች ያሳያሉ። ለሶስቱ ዲቪዚዮን አሸናፊዎቻችን - Winston Churchill, Bethesda-Chevy Chase, and John F. Kennedy ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። በሚቀጥሉት ሳምንታት ብዙ ቡድኖቻችን በክልል እና በስቴት ደረጃዎች ሲወዳደሩ ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን!
የእነዚህ ጎበዝ ወጣት አትሌቶች ትጋትና ጥልቅ ስሜት ስላከበረው ውድድር ተጨማሪ ያንብቡ!
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክልላዊ/ካውንቲ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች ለማመልከት አንድ ቀን ብቻ ቀረው
የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች አዳምጡ! በParentVUE ላይ የሚገኘውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጋራ ማመልከቻ በመጠቀም ለክልላዊ/ካውንቲ አቀፍ አቀፍ ልዩ ፕሮግራሞች አመልክቱ። ከ9-11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ለሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ።
ለተማሪዎች እና ለወላጆች የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች ይኖራሉ። ለዝርዝ መረጃዎች የልዩ ፕሮግራሞች/Special Programs ድረ-ገጽን ይጎብኙ።
ማመልከቻ የሚገባበት የመጨረሻው ቀን፡ አርብ፣ ኖቬምበር 1።
Programs At A Glance፣ብቁነት፣ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች/ FAQs እና አጠቃላይ እይታ የሚያገኙበት ቪዲዮ በልዩ ፕሮግራሞች/Special Programs ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።
ቀኑን ያስታውሱ፡ የስራ ማስኬጃ የበጀት ውይይት መድረኮች
MCPS በ2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ ለመወያየት በተከታታይ በሚካሄዱ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። እያንዳንዱ ዶላር በትምህርት ቤት ስርዓት ውስጥ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለማሰስ፣ ስለቀጣይ ለውጦች ለማወቅ/ለመማር፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ግንዛቤዎን ለማካፈል የMCPSን አመራር ቡድንን ይቀላቀሉ። የእርስዎ ድምጽ ዋጋ አለው!
በትምህርት ቤት ካላንደር (ቀን መቁጠሪያ) ላይ ግብረ መልስ እንዲሰጡ የቀረበ የመጨረሻ ጥሪ!
MCPS የ2025–2026 መደበኛ የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ በማዘጋጀት ላይ ስለሆነ ዲስትሪክቱ ከሰራተኞች፣ ከቤተሰቦች፣ ከተማሪዎች እና ከማህበረሰብ አባላት ተጨማሪ ግብረመልስ ይፈልጋል። ጥቂት ጊዜ ወስደው ግብረ መልስዎን በዳሰሳ ጥናቱ Round 2 ላይ ይስጡን። የዳሰሳ ጥናቱ እሁድ ዲሴምበር 1 ይዘጋል። የትምህርት ቦርድ/ Board of Education የ2025-2026 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያን ዲሴምበር 5 በሚካሄደው የቢዝነስ ስብሰባው ላይ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሁለቱ የቀን መቁጠሪያ አማራጮች መካከል ያሉት ዋና ዋና ልዩነቶች የሚከተሉት ናቸው፡
የዊንተር ዕረፍት ርዝመት (ስምንት ቀናት ወይም 10 ቀናት)።
የተማሪዎች የመጨረሻ የትምህርት ቀን (ረቡዕ፣ ጁን 17, 2026 ወይም ሰኞ፣ ጁን 22, 2026)።
እዚህ ጋር ይጫኑ ወይም የዳሰሳ ጥናቱን ለማግኘት ከታች ያለውን የQR ኮድ ስካን ያድርጉ።
በቅርብ ቀን፡ የዊንተር ስፖርቶች ጊዜ/Winter Sports Season
የ2024-2025 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዊንተር አትሌቲክስ የኦንላይን ምዝገባ በParentVUE ፖርታል በኩል ይገኛል። በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ተደራሽ እንዲሆን የተደረገው ይህ ፖርታል ሁሉንም አስፈላጊ ቅጾች እና ሰነዶች ለተጠቃሚ ምቹ በሆነ በኢንተርኔት ላይ በተመሠረተ መድረክ ላይ ያጠምራል። ምዝገባውን ለማጠናቀቅ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ፖርታሉ መግባት ይችላሉ። በተጨማሪም፣ የተማሪያቸውን የአካል ምርመራ ሰነዶች ስካን አድርጎ የመጫን/አፕሎድ የማድረግ አማራጭ አላቸው። እባክዎን የቅድመ-ተሳትፎ አካላዊ ምርመራዎች ለ 13 ወራት የሚቆዩ መሆናቸውን ይገንዘቡ። ተጨማሪ መረጃ በMCPS አትሌቲክስ ድህረ ገጽ የመመዝገቢያ ገጽ ላይ ይገኛል።
መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር
MCPS መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበትን ወር ከመዋእለ ህጻናት እስከ አሥራሁለተኛ ክፍል (K-12) ስለ አካባቢው አፍሪካን አሜሪካን ታሪክ እና የነጻነት ቀን በሚመለከት ግዴታ የሆነ አጫጭር ታሪክን በማስተማር ያከብራል። የመታሰቢያ እና የእርቅ ኮሚሽኑ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ የተቋቋመው በ 2019 ነው።
ከዚህ በታች ያሉት መጪዎቹ የዚህ ዓመት የMCPS የነጻነት ቀን ዝግጅቶች ናቸው፡
የSandy Spring የባሪያ ሙዚየም/ Slave Museum እና የአፍሪካ ስነ-ጥበብ ጋለሪ የሜሪላንድ የነጻነት ቀን ክብረ በዓል
ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 2 ከቀትር እስከ 3፡20 p.m.
Brooke Road, Sandy Spring, Md. 20860
ብራውን vs የትምህርት ቦርድ MCPS ላይ ያለው ተጽእኖ
ረቡዕ፣ ኖቨምበር 6፣ 7-8 p.m.
የዌቢናር ዙም ምዝገባ፣ለህዝብ ክፍት ተደርጓል
አመታዊ ጨዋታ ቀያሪ አውደ ጥናት
ሐሙስ፣ ኖቬምበር 14, 6:30-8 ፒ.ኤም
ተማሪዎች እስከ ሁለት የሚደርሱ የSSL ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ።
ዙም የዌቢናር ምዝገባ አገናኝ/Link
የተማሪ እድሎች
በቦታው ላይ የሚደረጉ ምዝገባዎች፡ በርካታ የአካባቢ እና የክልል ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ለMCPS ሲኒየሮች በSeneca Valley የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረቡዕ፣ ኖቬምበር 13፣ ከ6–8 p.m. እና በRichard Montgomery የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማክሰሞ ዲሴምበር 3፣ ከ3-6 p.m. በቦታው ላይ የሚደረጉ ምዝገባዎችን እያቀረቡ ነው። ተሰብሳቢዎች/ተሳታፊዎች የFAFSA ድጋፍንም ያገኛሉ እና ስለ Montgomery College የማመልከቻ ሂደትም ይማራሉ።
የሴኔካ ቫሊ አድራሻ፡19401 Crystal Rock Drive in Germantown
Richard Montgomery የሚገኘው በ250 Richard Montgomery Drive Rockville ነው።
በግልጽ ይናገሩ፣ህይወት ያድኑ፦የስቴት አቃቤ ህግ ቢሮ“Speak Up, Save a Life” በሚል ርዕስ የመወዳደርያ ቪዲዮ PSA በማዘጋጀት/በማቅረብ ተማሪዎች እንዲወዳደሩየመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ተጋብዘዋል። ቪዲዮዎቹ አደንዛዥ እጾችን፣ኦፒዮይድስ፣እና ፌንታኒል የመጠቀም አደጋዎች ላይ ማተኮር አለባቸው። የሚሳተፉ ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፤ ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ዶላር ነው። የመወዳደሪያ ግብአቶች አርብ፣ ኖቬምበር 12 እስከ እኩለ ሌሊት መቅረብ አለባቸው። የውድድር ግብአቶች ጥያቄ ካለዎት፣ኢሜልይላኩ።
ብሄራዊ የC-SPAN የዶክመንተሪ ውድድር፡ ከ6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በC-SPAN ዓመታዊ የቪድዮ ዶክመንተሪ StudentCam ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፣ ይህም ማህበረሰባችን ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ ጉዳዮች በጥልቀት እንዲያስቡ ያበረታታል። በዚህ አመት ተማሪዎች “ለፕሬዝዳንቱ ያላችሁ መልእክት” በሚል የውድድሩ መሪ ሃሳብ ላይ ተሞርኩዘው ከአምስት እስከ ስድስት ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ ሠርተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል። ተማሪዎች በግል ወይም በቡድን መወዳደር ይችላሉ። የማስረከቢያው ቀነ-ገደብ ሰኞ፣ ጃኑዋሪ 20, 2025 የፕሬዚደንት በዓለ ሲመት ቀን ነው። C-SPAN ምርጥ ዘጋቢ ቪድኦ አዘጋጅተው ላቀረቡ 150 ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል። ተጨማሪ ዝርዝሮችን እዚህ ያገኛሉ።
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን፦ Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org