መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ኖቨምበር 7 2024

የስራ ማስኬጃ በጀት ፎረሞች RSVP

MCPS የ2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ ለመወያየትበተከታታይ በሚካሄዱ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች እያስተናገደ ነው። እያንዳንዱ ዶላር በትምህርት ቤት ስርዓት ውስጥ እንዴት እንደሚመደብ ለማሰስ፣ ስለቀጣይ ለውጦች ለማወቅ/ለመማር፣ እና ግንዛቤዎን ለማካፈል የMCPS አመራርን ይቀላቀሉ።

የእርስዎ ድምጽ ዋጋ አለው እና ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እና በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ እናበረታታዎታለን። የፎረሞቹ RSVP፡ 

  • ሰኞ፣ ኖቬምበር 11, ከ 6:30–8 p.m.፣ James Hubert Blake ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 300 Norwood Road Silver Spring። ይመዝገቡ/RSVP

  • ሰኞ፣ ኖቬምበር 18 ከ6:30–7:30 p.m.,፣ የስፓኒሽኛ ክፍለ ጊዜ ቀጥታ በፌስቡክ/በFacebook Live በMCPS en Español Facebook 

  • ሀሙስ፣ ኖቬምበር 21, ከ6:30–8 p.m.፣ Clarksburg ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 22500 Wims Road Clarksburg። ይመዝገቡ/RSVP


የMontgomery Blair ተማሪዎች በNPR ፖድካስት ውድድር ላይ ደምቀው ታይተዋል

የMontgomery Blair ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች Riley MacArthur እና Lila Shaw በዘንድሮው የNPR ፖድካስት ውድድር ላይ 10 ምርጥ የመጨረሻ ዙር ተወዳዳሪዎች ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፣ ወደ 2,000 ከሚጠጉ ተወዳዳሪዎች "Paper Dolls" በሚለው ፖድካስታቸው ከሁሉም የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል። ይህ ዓመታዊ ውድድር የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የፈጠራ ችሎታቸውን እና ታሪክ የመንገር ክህሎታቸውን እንዲያሳዩ ይጋብዛል።

"Riley እና Lila ከሁሉም ተማሪዎች ጋር ተሳትፎ ለማድረግ ባሳዩት ድፍረት እንዲሁም ስለ ተማሪ ፋሽን እና ራስን ስለመግለጽ ፖድካስት በማዘጋጀት ረገድ ባሳዩት የፈጠራ ችሎታ ኩራት ይሰማኛል።" በማለት የMontgomery Blair HS ርዕሰ መምህር Kevin Yates ተናግረዋል።  

በተጨማሪም፣ ሌሎች ሶስት የMontgomery Blair ፖድካስቶች የክብር ስያሜዎችን አግኝተዋል። የትኞቹ እንደሆኑ ይወቁ እናፖድካስቶቹን ያዳምጡ። 


የተማሪ እድሎች

የRales-O’Neill Scholarship/የነጻ ትምህርት እድል ማመልከቻው አሁን ክፍት ነው።

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲኒየሮች/የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች አሁን በMontgomery County Public Schools Educational Foundation (MCPSEF) ለሚሰጠው ለ Rales-O'Neill ስኮላርሺፕ/የነጻ ትምህርት እድል ማመልከት ይችላሉ፣ ይህም ስኮላርሺፕ ለወደፊቱ ጥናቶች $10,000 ይሰጣል። ሁለት መቶ ተማሪዎች ይመረጣሉ።

አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው፡

  • አጠቃላይ ድምር ውጤት GPA 4.8 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ፣

  • በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኮሌጅ / ዩኒቨርሲቲ ለመግባት እቅድ ካሎዎት.

የማመልከቻው ጊዜው ከኖቬምበር 1, 2024, እስከ ጃንዋሪ 25, 2025 ክፍት ነው። ስለ ብቁነት እና ስለ ህጎች/ደንቦች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጹን ይጎብኙ።


Youth Town Hall ከMontgomery County የካውንስል አባላት ጋር

የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች Youth Town Hall ከMontgomery County የካውንስል አባላት ጋር በተሰኘው ዝግጅት ላይ ረቡዕ ኖቬምበር 20 ከ6-8፡30 p.m የመሳተፍ እድል አላቸው። ይህ ዝግጅት ተማሪዎች ወጣቶችን ባማከሉ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ፣ ጥያቄዎችን እና ስጋቶችን እንዲያካፍሉ/እንዲያጋሩ፣ እና ከካውንቲ አመራር ጋር እንዲነጋገሩ ያስችላቸዋል።

ተማሪዎች በአካል ወይም በZoom መከታተል ይችላሉ፣ እና በዝግጁቱ ላይ በመገኘታቸው የSSL ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። RSVP አስፈላጊ ነው።

RSVP እዚህ ይመዝገቡ.


የላቲን ዳንስ ውድድር ትኬቶች አሁን በሽያጭ ላይ ናቸው

በዓመታዊው የAfter School Dance Fund/Baila4Life የላቲን ዳንስ ውድድር ላይ ለመሳተፍ እድሉ እንዳያመልጥዎ! ይህ ዝግጅት ሰኞ ኖቬምበር 25 በ6፡30 p.m በStrathmore በሚገኘው የሙዚቃ ማዕከል ይካሄዳል። ትኬትዎን ይግዙ።


የMaryland STEM ፌስቲቫል 2024

የሜሪላንድ STEM ፌስቲቫል በስቴቱ ውስጥ ዝግጅቶችን እያሳየ ነው። በሁሉም የእድሜ ክልል ላሉ ተማሪዎች የተዘጋጁ የSTEM ተግባሮች የሚካሄዱበትን ቀን እና ቦታን የሚያካትተውን ድረ ገጽ በመጎብኘት በአቅራቢያዎ ያሉትን ዝግጅቶች ያግኙ።




ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)