መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 19 ቀን 2024

የበላይ ተቆጣጣሪው መግለጫዎች FY 2026 የተመከረ የስራ ማስኬጃ በጀት

ቪዲዮ ይመልከቱ

በዲሴምበር 18, የMCPS የበላይ ተቆጣጣሪ ቶማስ ቴይለር የ2026 የበጀት አመት (FY) የተመከረ የስራ ማስኬጃ የበጀት ጥያቄን ለትምህርት ቦርድ አቅርቧል። ጥያቄው MCPS የልህቀት ትሩፋቱን ለማሟላት እየወሰዳቸው ያሉ  የበርካታ-ዓመት የእርምት እርምጃዎችን ያካትታል። የዲስትሪክቱ ፍላጎቶች ሰፊ ናቸው እና ፕሮፖዛሉ በጊዜ ሂደት የተከማቹ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ግልፅ ሆኖ በሚታይ መልኩ ዕቅድን አስቀምጧል።

ዶ/ር ቴይለር የትምህርት ቤቱን ሥርዓት ለማረጋጋት እና ለተማሪ ትምህርት እና ለት/ቤት ድጋፍ ቅድሚያ ለመስጠት የተነደፈ የ3.61 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት ለ2026 የበጀት ዓመት አቅርቧል። ምክረ ሀሳቡ በቀጥታ ወደ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚያነጣጥር፣ የተማሪን ስኬት የሚደግፍ እና በስርዓቱ ውስጥ ያሉ መዋቅራዊ ጉድለቶችን የሚፈታ ''በመሠረታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር'' የሚለውን አካሄድ ያንፀባርቃል። 

በተመከረው የ2026 FY በጀት ላይ ተጨማሪ መረጃ

ሙሉ ፕረዘንቴሽኑን ይመልከቱ

የትምህርት ቦርድ አሁን በበጀቱ ላይ ህዝባዊ ውይይቶችን እና የስራ ክፍለ ጊዜዎችን ያደርጋል/ያዘጋጃል። የጊዜ መርሀ-ግብር፡

በበጀት ዝግጅት ላይ የቀረቡ መገልገያዎች/ሪሶርሶች

ሙሉው የተመከረው የ FY 2026 የስራ ማስኬጃ በጀት መጽሀፍበኦንላይንአርብ፣ ዲሲውምበር 20 ላይ ይለቀቃል።


አዲስ ድህረ ገጽ ስለ መጪው የMCPS የድንበር ጥናት ዝርዝሮች መረጃ ይሰጣል

ቪዲዮ ይመልከቱ

በ2027-2028 ለሚደረገው ለCrown High School የመክፈቻ ዝግጅት፣ ለDamascus High School ማስፋፊያ እና ለCharles W. Woodward High Schoolዳግም መከፈት ለመዘጋጀት፣ MCPS የወሰን ጥናት እያካሄደ ነው። ይህ ጥናት አዲስ የትምህርት መከታተያ ቦታዎችን ለመወሰን እና በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ መጨናነቆች ለመፍታት ይረዳል።

ዝርዝር መረጃዎችን፣ በተደጋጋሚ የሚተየቁ ጥያቄዎችን እና በሂደቱ ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ለዚያ ዓላማ የተዘጋጀውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ። እነዚህ ለውጦች የMCPS ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያደርጉ ይወቁ።


BOE የሰራተኛ የስነምግባር ጉድለት ክሶች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን በተመለከተ ለአዲስ ፖሊሲ አስተያየት ይፈልጋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የMCPS የሰራተኛ የስነ ምግባር ጉድለት ምርመራዎችን የሚመራውን የቦርዱን ዋና መርሆችን ለማቋቋም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአጠቃላይ ኢንስፔክተር ፅህፈት ቤት/Office of the Inspector General ምክረ ሃሳቦችን ለማክበር ለተዘጋጀው አዲስ ፖሊሲ ማለትም ፖሊሲ GCB፣ የሰራተኛ የስነ ምግባር ጉድለት ክሶች ምርመራ፣ የህዝብ አስተያየትን ይፈልጋል። ፖሊሲው በአሁኑ ጊዜ በመተዳደሪያ ደንቦች እና በሰራተኛ መመሪያ መጽሃፍ ውስጥ የተገለጹትን ከሰራተኞች ስነ-ምግባር ጋር ተያይዞ የሚጠበቁ ነገሮች ላይም አጽንዖት ይሰጣል።

መመሪያው ከዲሴምበር 10፣ 2024 ጀምሮ ለአስተያየት ክፍት ሆኗል፣ እና የህዝብ አስተያየት የመስጫ ጊዜው እስከ ፌብሩዋሪ 3፣ 2025 ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ረቂቅ መመሪያውን ይመልከቱ

አስተያየቶችን ያቅርቡ



አንድ ተማሪ ያድኑ/Save A Student ስብሰባ ለጃንዋሪ 4 ቀጠሮ ተይዞለታል

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቅዳሜ ጃንዋሪ 4, በWalter Johnson High School አዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ ከ10 a.m.-12:30 p.m በሚካሄደው አንድ ተማሪ ያድኑ/Save A Student ስብሰባ ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል። ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች opioid እና fentanyl መጠቀም ስለሚያስከትለው ውጤት እንዲያውቁ፣ ከመጠን በላይ የመውሰድ ድንገተኛ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ Narcanን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ስልጠና የመውሰድ፣ የNarcan ኪት የማግኘት፣ እና በቅርብ ጊዜ የተካሄድ የSpeak Up፣ Life Save A PSA ውድድር አሸናፊዎች ስለሆኑት የማወቅ/የመማር እድልን ይሰጣል። ተማሪዎች ለመሳትፏቸው ሶስት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይመዝገቡ/RSVP.

ዋልተር ጆንሰን (Walter Johnson) የሚገኝበት አድራሻ፦ 6400 Rock Spring Drive in Bethesda


ለትምህርት ፋውንዴሽን የተማሪ ስኮላርሺፕ እና ሽልማቶችን ያመልክቱ

ሲንየር ተማሪዎችን በሙሉ ይመለከታል!ለMontgomery County Public Schools Educational Foundation (MCPSEF) የተማሪ ስኮላርሺፕ እና ሽልማቶች ዛሬውኑ ያመልክቱ። ሽልማቶቹ ትምህርታዊ ግቦችን ለማሳካት ጥልቅ ስሜት ላላቸው፣ እና እነዚህ ግቦች ለማሳካት የዕድል ክፍተቶች ላጋጠማቸው ተማሪዎች ክፍት ናቸው።

ብቁ ለመሆን፣ የሚከተሉትን ማሟላት አለብዎት፡

ማመልከቻዎች እስከ ዓርብ፣ ጃንዋሪ 24, 2025 ክፍት ናቸው።ጥያቄዎች ካልዎት፣ ኢ-ሜይልእዚህ ጋር ይላኩ ወይም በ240-740-3216 ይደውሉ።


በሜሪላንድ ራሳቸውን የቻሉ ኮሌጆች፣ ዩኒቨርሲቲዎች የOpen House ጉብኝት ለማድረግ ቀጠሮ ያስይዙ።

በርካታ የሜሪላንድ ራሳቸውን የቻሉ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጃንዋሪ ላይ ይጀምራሉ ተብለው ለሚጠበቁ ተማሪዎች በራቸውን እየከፈቱ ነው። በተጨማሪም አንዳንዶቹ የካምፓስ ጉብኝቶችን እንዲያደርጉ ጥያቄ እያቀረቡ ነው። የእርስዎን የopen house ጉብኝት ቀጠሮ ማስያዝዎን እርግጠኛ ይሁኑ። ከእነዚህ ውስጥ፡ Hood College, Loyola University, Maryland Institute College of Art, Mount St. Mary’s University, Stevenson University, Goucher College, Notre Dame University of Maryland, Washington Adventist University and Washington College ይገኙበታል። 

ሙሉ ዝርዝሩን ይመልከቱ


የደቡብ እስያ አሜሪካውያን ቤተሰቦች እስከ ጃንዋሪ 31 ድረስ የዳሰሳ ጥናት እንዲያጠናቅቁ ተጋብዘዋል

በደቡብ እስያ አሜሪካ ጉዳዮች የሜሪላንድ ገዥ ኮሚሽን የደቡብ እስያ ዝርያ ያላቸው ቤተሰቦች በትምህርት ላይ ያላቸውን ልምዳቸውን እና አመለካከታቸውን በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት እንዲያጠናቅቁ ይጠይቃል። ይህ ግብረመልስ ኮሚሽኑ በደቡብ እስያ አሜሪካ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን እና አስተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ እርምጃዎችን/እቅዶችን እና ስልቶችን እንዲያዘጋጅ/እንድታዘጋጅ ይረዳዋል/ይረዳታል።

ቤተሰቦች የዳሰሳ ጥናቱን እስከ አርብ፣ ጃንዋሪ 31 ድረስ እንዲያጠናቅቁ ይጠየቃሉ።


Francis Scott Key የመካከለኛ ትምህርት ቤት ተማሪ STEMን እና የታሪክ አተራረክን በ Chemistories ውስጥ ያጣምራል።

በFrancis Scott Key የመካከለኛ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ማያ ሞርሼድ ለሳይንስ እና ለታሪክ አተራረክ ያላትን ፍቅር Chemistories በተሰኘው በመጀመርያ መጽሃፏ ውስጥ አጣምራለች። ስብስቡ ልዩ በሆኑ ስብዕናዎች እና ተግዳሮቶች የperiodic table ክፍሎችን ወደ ህይወት ያመጣል። በልጅ እድሜ ላይ ያለች የፈጠራ ደራሲ፣ ሞርሼድ ስራዋ በSociety of Young Inklings ታትሟል እና እንዲሁም ሰዓሊ ናት። በአሁኑ ጊዜ በሒሳብ ላይ ያተኮረ አዲስ መጽሐፍ ላይ እየሰራች ነው። ይበልጥ ያንብቡ።


የKID ሙዚየም ለMCPS ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ፕሮግራሞችን ያቀርባል።

የKID ሙዚየም ከትምህርት በኋላ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችን እና የበዓል እረፍት ክፍለ ጊዜያትን ጨምሮ በዚህ ዊንተር እና ስፕሪንግ ወቅት ለተማሪዎች የተለያዩ እድሎችን እያቀረበ ነው። በቀጣይ የሚካሄደው፡

አንዳንድ/የተወሰኑ ፕሮግራሞች ክፍያ አላቸው። የፋይናንስ/የገንዘብ እርዳታ በተጠየቀ ጊዜ ይቀርባል። ተጨማሪ መረጃ በበKID ሙዚየም ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)