መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 9, 2025

የ MCPS እና የካውንቲ ቡድኖች ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናቀዋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አንዳንድ ጠጣር የበረዶ ግግር ያለባቸው አካባቢዎችን ችግር ለመፍታት እና የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ በትጋት እየሰሩ ቆይተዋል። አንዳንድ የተወሰኑ አካባቢዎች አሁንም ትኩረት የሚሹ መሆናቸው እውነት ነው።


ስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Springbrook HS

ጃኑዋሪ 9, 2025
5:00 am


በርንት ሚልስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Burnt Mills ES

ጃኑዋሪ 9, 2025
5:00 am

Richter Farm Rd.
Germantown

ጃኑዋሪ 9, 2025
5:00 am

211 ትምህርት ቤቶችን ያቀፈ የትምህርት ስርዓትን በሚመለከት ዘግይቶ ስለመክፈት እና/ወይም ስለመዝጋት ውሳኔ መስጠት ውስብስብ ነው፣ ምክንያቱም ብዙ ነገሮችን በጥንቃቄ ማጤን ያስፈልጋል። ውሳኔዎች በሚወሰኑበት ጊዜ ትምህርት ቤቶች የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን ከበረዶ ክምር እንዲፀዱ ማድረግ እንዳለባቸው እና ሰራተኞች በንቃት እየሰሩ የበረዶ ክምር ለማጽዳት የሚያደርጉትን ጥረቶች መገንዘብ ይገባል። በካውንቲው የተለያዩ አካባቢዎች ሁኔታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ሊለያዩ ይችላሉ፣ይህም የአሠራር ሂደቱን ውስብስብነት ይጨምራል። በተጨማሪም፣ በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን ከ100,000 ማይል በላይ የሚጓዙትን/የሚሸፍኑትን 1,300 የአውቶቡስ መስመሮች እና እንዲሁም 13,024 የአውቶቡስ ማቆሚያዎች ላይ የሚጠብቁትን ተማሪዎች ደህንነት አደገኛ ሁኔታ ላይ አለመሆናቸውን ግምት ውስጥ ማስገባትና ማጤን ይኖርብናል።

የበረዶ ክምር ያለባቸውን ቦታዎች ለማፅዳትና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተነቃናቂ ቡድኖችና ሰራተኞች የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ናቸው። አሁንም በአካባቢዎ የበረዶ ክምር ሁኔታ እያጋጠመዎት ከሆነ፣ እባክዎን በዚህ የስልክ መስመር 311 ወይም በስልክ ቁጥር 240-777-0311 ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ይደውሉ። 

እነዚህ ውሳኔዎች እንዴት እንደሚደረጉ የበለጠ መረጃ ለማግኘት MCPS አስቸኳይ ወይም አደገኛ ሁኔታ ሲያጋጥም ት/ቤቶች የሚዘጉበትን መረጃ ድረ-ገጽ ይጎብኙ፡ MCPS አስቸኳይ ወይም አደገኛ ሁኔታ ሲያጋጥም ት/ቤቶች ስለሚዘጉበት ሁኔታ

ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚደርሰዎት ለማረጋገጥ እባክዎ ParentVUE link በመጠቀም MCPS Community Tech Support ድረገጽ ላይ የእርስዎን ወቅታዊ መረጃ ያስገቡ።

ስለቀለም ኮዶች ይበልጥ ይወቁ
አስቸጋሪ/ከባድ የአየር ሁኔታ በሚያጋጥምበት ወቅት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አሠራር/MCPS Operating Status Inclement Weather, 2024-2025


ስለ ሥራ ማስኬጃ በጀት በሚካሄድ የማህበረሰብ ውይይት ላይ ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ።

ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር ለ 2026 የበጀት ዓመት $3.61 ቢሊዮን ዶላር የስራ ማስኬጃ በጀት ጥያቄ አቅርበዋል። ንድፈሃሳቡ፣ፕሮፖዛሉ በቀጥታ ወደ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚያተኩር፣ የተማሪዎችን ስኬት የሚደግፍ እና በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያሉ መዋቅራዊ ጉድለቶችን የሚፈታ ''በመሠረታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር'' የሚለውን አካሄድ ያንፀባርቃል። 

የትምህርት ቦርድ በቀረበው የበጀት ጥያቄ ላይ የሚከተሉት የህዝብ አስተያየት መቀበያ እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች ይኖሩታል።

የሥራ ማስኬጃ ባጀት ድረገጽ/Fiscal Year 2026 Operating Budget website


የተማሪዎች እድል

ለትምህርት ፋውንዴሽን የተማሪ ስኮላርሺፕ እና ሽልማቶችን ያመልክቱ

ሲንየር ተማሪዎችን በሙሉ ይመለከታል!ለMontgomery County Public Schools Educational Foundation (MCPSEF) የተማሪ ስኮላርሺፕ እና ሽልማቶች ዛሬውኑ ያመልክቱ። ሽልማቶቹ ትምህርታዊ ግቦችን ለማሳካት ጥልቅ ስሜት ላላቸው፣ እና እነዚህ ግቦች ለማሳካት የዕድል ክፍተቶች ላጋጠማቸው ተማሪዎች ክፍት ናቸው።

ብቁ ለመሆን፣ የሚከተሉትን ማሟላት አለብዎት፡

ማመልከቻዎች እስከ ዓርብ፣ ጃንዋሪ 24, 2025 ክፍት ናቸው።ጥያቄዎች ካልዎት፣ ኢ-ሜይልእዚህ ጋር ይላኩ ወይም በ240-740-3216 ይደውሉ።


ለRales-O’Neill ስኮላርሺፕ ያመልክቱ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፋውንዴሽን (MCPSEF) የሚሰጠው የ Rales-O'Neill ስኮላርሺፕ ማመልከቻዎች አሁን ላይ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲኒየሮች/የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ክፍት ናቸው። ስኮላርሺፖቹ ለወደፊት ትምህርቶች 10,000 ዶላር የሚሰጡ ሲሆን ይህም ለሁለት መቶ ተማሪዎች ይሰጣል።

ማመልከቻዎች እስከ ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 25, 2025 መቅረብ ይኖርባቸዋል። ብቁነትን እና ህጎችን በተመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት MCPSEF ድረ-ገጽን ይጎብኙ።


ለተማሪ የቦርድ አባልነት በእጩነት መወዳደሪያ ጊዜ/SMOB Candidate Filing Period

ለትምህርት ቦርድ አባልነት ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ የሆኑ የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እስከ ሐሙስ፣ ጃኑዋሪ 23 ድረስ የመመዝገቢያ ቅጾቻቸውን ማቅረብ አለባቸው። ለእጩነት የመወዳደሪያ ቅጽ SMOB የምርጫ ፕሮቶኮል ገጽ 31-32 ላይ ይገኛል። የተሞሉት ቅጾች ስካን ተደርገው ወደ፦ Shella Cherry, director, Student Leadership & Extracurricular Activities በኢሜል መላክ አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ


የማርቲን ሉተር ኪንግ ሣምንት አገልግሎት ከጃኑዋሪ 18 እስከ 26 ይካሄዳል/MLK Week of Service: Jan. 18-26, 2025

MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃደኞች ማእከል (MCVC) ጋር በመተባበር የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር አመታዊ አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት በጎ ተግባራትን እና አገልግሎቶችን ያከናውናል። የማርቲን ሉተር ኪንግ (MLK) የአገልግሎት ሳምንት፥ ጃንዋሪ 18 እስከ 26, 2025።

በአንዳንድ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፕሮጀክቶች MCPS SSL መመሪያዎችን በመከተል አገልግሎት የሚሰጡ ተማሪዎች ለተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአት ማግኘት ይችላሉ።

በተጨማሪም MCVC ጃንዋሪ 18 እና ጃንዋሪ 19 አገልግሎቶችን ያስተናግዳል። በእነዚህ እድሎች ለመጠቀም MCVC ድረ ገጽ ላይ www.montgomeryserves.org መመዝገብ ያስፈልጋል።

MCPS እና MCVC አላማቸው የ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በማክበር በጎነትን ማድረግ እና የማህበረሰብ አገልግሎትን ማበረታታት ነው።የመልካም ሥራ ተምሣሌትነቱን


መጪዎቹ ዝግጅቶች እንዳያመልጥዎት

የልዩ ትምህርት መርጃ አውደርዕይ እሮብ፣ ጃንዋሪ 15 ከቀኑ 5:30–7:30 p.m. ከዚህ ቀጥሎ ባለው አድራሻ ኦዲተሪየም ውስጥ ይካሄዳል፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville ይህ ዝግጅት ግላዊ የትምህርት ፕሮግራም (IEPs) የሚሰጣቸው ልጆች ላሏቸው ወላጆች ሁሉ ክፍት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ከትምህርት ሠዓት በኋላ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣የሠመር ፕሮግራሞች፣ እና ተጓዳኝ ስልጠናዎች ከማህበረሰብ ድርጅቶች የበለጠ መማር ይችላሉ።

ታሪካዊ የጥቁር ኮሌጆች እና ዩንቨርስቲዎች (HBCU) አውደርዕይ፦ ዓርብ፣ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ the Universities at Shady Grove (USG). ይህ ዝግጅት 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው/ለአሳዳጊዎቻቸው ከ 50 በላይ HBCU ተወካዮች ጋር ለመገናኘት እና በአውደ ጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣቸዋል። ተጨማሪ መረጃ

FAFSA/MHEC One Application Completion Event፦ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ USG ይህ ዝግጅት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)