በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከት/ቤቶች መዘጋት በኋላ በትምህርት ቤት ካለንዳር/የቀን መቁጠሪያ ላይ ለውጦች ይደረጋሉ።
ሰኞ፣ ጃንዋሪ 6፣ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 7 እና ረቡዕ፣ ጃንዋሪ 8 ከባድ የአየር ሁኔታ ጋር በተያያዘ ምክንያት ት/ቤቶች ሶስት ቀናት የአደጋ ጊዜ መዝጋት ሲያጋጥም MCPS ለትምህርት አመት 2024-2025 የተያዙትን ሁለቱን የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ቀናት ተጠቅሟል። ዲስትሪክቱ ሶስተኛውን ቀን እንዴት ማካካስ እንደሚቻል የሚገልጽ ማስታወቂያ አርብ፣ ጃንዋሪ 24 ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች እናጋራለን።
ማንኛውም ተጨማሪ የአደጋ ጊዜ ት/ቤቶችን የመዝጋት ሁኔታ ካጋጠመ ዲስትሪክቱ በትምህርት አመቱ የቀን መቁጠሪያ ላይ በመጠባበቂያነት የተያዙ ቀናትን ለመጠቀም ይገደዳል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞችን እናመሰግናለን!
አስደናቂ ሰራተኞቻችን በዚህ ሳምንት ላሳዩት ከባድ የስራ ትጋት (ምናልባት በዚህ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ የማይሆን ቢመስልም) ባርኔጣችንን ከፍ አውልቀን እናመሰግናቸዋለን! የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አውቶቡሶች እንዲጓዙ እና ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለጎብኝዎች በጥሩ ሁኔታ ክፍት እንዲሆኑ ከማመቻቸታቸውም በላይ ከአስተዳደር ቢሮዎች፣ ከጥገና እና ኦፕሬሽን ክፍል እና ከትራንስፖርት መምሪያ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰራተኞች በረዶ ለማስወገድ እና የወለል ንጣፎችን ለማጽዳት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰርተዋል።
በእግረኛ መንገድ ላይ ወይም በመኪና መንገድ ላይ ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች ወይም ለአውቶቡሶች አደጋ ይፈጥራል ብለው የሚያምኑት የበረዶ ክምር ካለ፣ እባክዎን ስለነዚህ አካባቢዎች ሪፖርት ለማድረግ 311 ደውለው የሞንትጎመሪ ካውንቲ አገልግሎትን ያነጋግሩ።
ስለ ሥራ ማስኬጃ ባጀት ውይይት በሚደረግባቸው የማህበረሰብ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፉ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስለ MCPS የበጀት አሠራር ሂደት ለማስረዳት የማህበረሰብ ስብሰባዎችን እያስተናገደ ነው። ስለ 2026 የስራ ማስኬጃ በጀት እና ቦርዱ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ነገሮች መግለጫ፣ እና ጥያቄና መልስ ስለሚሰጥ የትምህርት ቦርድ ፕሬዘዳንት ጁሊ ያንግን እና ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለርን ይቀላቀሉ።
የማህበረሰብ ስብሰባዎች መርሃ ግብር፦
የትምህርት ቦርድ የስራ ማስኬጃ በጀትን በሚመለከት የማህበረሰብ ውይይት የተደረገባቸው መድረኮች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎችን ሲያካሄድ ቆይቷል። የመጨረሻው በሚከተሉት ቀናት ውስጥ ይካሄዳል።
ቦርዱ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 4 በሚያካሂደው የቢዝነስ ስብሰባ የስራ ማስኬጃ በጀቱን በጊዜያዊነት ያፀድቃል፣ የመጨረሻውን ማክሰኞ፣ ጁን 10 በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
ስለቀረበው FY 2026 በጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት በዚህ ድረገጽ ላይ ያንብቡ።
በዚህ አመት COSA ሂደት ላይ ለውጦች ይደረጋሉ
MCPS 2025-2026የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) ሽግግር ወቅት ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 3 ይከፈታል፤ እና ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 1, 2025 ይዘጋል። COSA የአሠራር ሂደቱ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የአካባቢያቸው ትምህርት ቤት (ሆም ስኩል) እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል።
ተማሪዎች በሚኖሩበት (የአካባቢ ትምህርት ቤት) ወይም ግላዊ የትምህርት መርሃ ግብራቸውን (IEP) በአካባቢያቸው በሚገኝ ት/ቤት ውስጥ መከታተል ይጠበቅባቸዋል። ስለ መስፈርቶቹ በይበልጥ ይወቁ።
ስለ መጪው COSA የማዛወር ሂደት አስፈላጊ ለውጦች፦
ጥያቄዎችን ለማቅረብ የተማሪ ፐርሶኔል እና የትምህርት ክትትል አገልግሎት ክፍል 240-740-5620 ይደውሉ።
የዊንተር የወላጅ አካዳሚ መርሃ ግብር የጊዜ ሠሌዳ አሁን ይገኛል
ቤተሰቦች እና ተማሪዎች በትምህርት አመቱ በሙሉ ከወላጅ አካዳሚ TO GO ጋር ተሳትፎ መቀጠል ይችላሉ። የጃኑዋሪ፣ የፌብሩዋሪ እና የማርች ዌብናሮች የወላጅ አካዳሚ ድረገጽ ላይ ይገኛሉ። ለመመዝገብ እዚህ ይክፈቱ።
የዋልት ዊትማን የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች እቃዎችን ለማህበረሰብ አገልግሎት ይገበያሉ።
የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቫርሲቲ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ከአትሌትነት በላይ የማህበረሰብ መሪዎች መሆናቸውን እያረጋገጡ ነው። ቡድኑ ከ ዲ.ሲ. የሾርባ ወጥቤት በጎ ፈቃደኝነት አንስቶ እስከ ምግብ ማደራጀትና ማዳረስ እውነተኛ ተጽእኖ እያደረገ ነው። ከጨዋታ ሜዳ ውጭ የአመራር ችሎታቸውን እንዴት እያዳበሩ እንደሆነ ለማወቅ ሙሉውን ታሪክ ያንብቡ።
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org