የመዋለ ህፃናት ምዝገባ ለ 2025–2026 የትምህርት ዘመን ክፍት ነው
የመዋለ ህፃናት ምዝገባ ለ 2025–2026 የትምህርት ዘመን የሚከፈተው ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 3 ነው። ሴፕቴምበር 1፣ 2025 ላይ 5 አመት የሚሆናቸው ልጆች ለምዝገባ ብቁ ናቸው። ምዝገባው ParentVUE ፖርታል ላይ በኦንላይን ይካሄዳል። ቤተሰብዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ከሆኑ፣ እዚህ PreentVue አካውንት መፍጠር ያስፈልግዎታል። ስለ ብቁነት እና የምዝገባ ሂደት የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ MCPS የመዋለ ህፃናት ምዝገባ ድረ-ገጽ ይጎብኙ ወይም የአካባቢዎን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያነጋግሩ።
ቅድመ መዋለ ህፃናት እና ቀድሞ ጅማሬ ምዝገባ ማርች 3 ላይ ይከፈታል
ቅድመ መዋለ ህፃናት እና ቀድሞ ጅማሬ ምዝገባ ሰኞ፣ ማርች 3 ላይ፣ ለ 2025–2026 የትምህርት ዘመን ይጀምራል። እነዚህ ፕሮግራሞች የሚመዘግቡት ሴፕቴምበር 1፣ 2025 ላይ ወይም ከዛ በፊት 4 አመት የሚሆናቸው ልጆችን፣ እንዲሁም ውስን ክፍት ቦታዎችን ሴፕቴምበር 1፣ 2025 ላይ ወይም ከዛ በፊት 3 አመት የሚሆናቸው ልጆችን ነው። ቤተሰቦች ለማመልከት በገቢ-ብቁ መሆን አለባቸው እና ልጆቻቸውን በኦንላይን ማስመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪም በአካል ተገኝቶ የማስመዝገብ ድጋፍም በ በርካታ ቦታዎች ይገኛል።
ልጅዎ ሴፕቴምበር 1፣ 2024 ላይ ወይም ከዛ በፊት 4 አመት ከሞላቸው፣ ለቅድመ መዋለ ህፃናት/ቀድሞ ጅማሬ በዚህ አመት ለቀሪው የትምህርት አመት ማስመዝገብ ይችላሉ።
እንዴት ማስመዝገብ እንደሚቻል ለማወቅ እዚህ ጠቅ/ይጫኑ።
ስለ ብቁነት መመሪያ፣ ስለ አስፈላጊ ሰነዶች፣ ወይም በኦንላይን እንዴት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ለበለጠ መረጃ፣ በስልክ ቁጥር 240-740-4530 ይደውሉ፤ ወይም MCPS ድረ ገጽ ይጎብኙ።
የጥቁር ታሪክ ወርን ማክበር
ከዚህ በታች ያለው ዝግጅት ለተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። ተማሪዎች በመሳተፍ እስከ ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአታት ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
የወኪልነት ጎዳና፦ የአፍሪካ አሜሪካውያንን ታሪክ መሰረዝ ለማስቆም የሪቨር ሮድ ማህበረሰብ ትግል፣ ከቤተሳዳ ሴሚተሪ ኮኦሊሽን ጋር በመተባበር
ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 6, 6-7፡30 ፒ.ኤም
ዙም ዌቢናር ምዝገባ ሊንክ
የወኪልነት ጎዳና፣ ፌብሩዋሪ 6
የኢሚግሬሽን/ስደተኞች ህግ ማስፈፀም ወደ MCPS ት/ቤት የሚመጣ ከሆነ ደህንነትን ማረጋገጥ
የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ት/ቤታችንን የሚጎበኙ ከሆነ የተማሪዎቻችንን ደህንነት ላማረጋገጥ MCPS ግልፅ አሰራሮች አስቀምጧል እነዚህ የአሰራር ቅደም ተከተሎች የተማሪዎችን ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት በተገቢው መንገድ ምላሽ ይሰጣሉ፦
ለተጨማሪ መረጃ እና በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች፣ የ MCPS ኢሚግሬሽን ድጋፎች ገፅን ይጎብኙ።
የዳንስ ትርዒት ለፌብሩዋሪ 7 ተዘጋጅቷል
ከቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 1 ጀምሮ፣ ለ 11ኛው አመታዊ MCPS የዳንስ ትርዒት ነፃ ትኬቶችን ያግኙ፣ የሚካሄደውም አርብ 7 p.m. ላይ በጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ 300 ኖርዉድ ሮድ በሲልቨር ስፕሪንግ ነው። የበረዶ ቀን ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 10 ነው።
ከሚከተሉት ት/ቤቶች የመጡ ተማሪዎች በዝግጅቱ እንዲሳተፉ ይጠበቃል—ኪንግስቪው፣ ኤ. ማሪዎ ሎኢደርማን፣ እና ዋይት ኦክ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና በተሳዳ-ቼቩ ቼስ፣ ብሌክ፣ አልበርት አንስታይን፣ ጆን ኤፍ. ኬኔዲ፣ ኖርዝዉድ እና ሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች። እንዲሁም ከመላው ካውንቲ ዳንስ ቡድን ትርኢት ይኖራል።
ትኬቶችዎን እዚህ ቅድሚያ ያስይዙ።
ቀኑን ያስታውሱ፦ ያገለገሉ መኪናዎች እና፣ ኮምፒውተሮች አመታዊ ሽያጭ ፌብሩወሪ 22 ይካሄዳል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች አውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን (ATF) እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF) ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እድሳት ያደረጉባቸውን ያገለገሉ መኪናዎችን እና ኮምፒውተሮችን ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 22፣ ከ 9-11 a.m. ደማስከስ ውስጥ በ 25921 Ridge Rd በሚገኘው በደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይሸጣሉ። መኪናዎቹ እና ኮምፒውተሮቹ የክፍል እና የላቦራቶሪ ጥናት አካል ሆነው በተማሪዎች ጥገና ተደርጎላቸዋል።
ለሽያጭ የቀረቡ መኪናዎችን ዝርዝር ለማግኘት፣ የአውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን ድረገፅን ፌብሩዋሪ 22 ሲቃረብ ይጎብኙ።
የ ITF የኮምፒውተር ሽያጮች ላፕቶፖችን እና ዴስክቶፖችን ያካትታሉ። ለተጨማሪ መረጃ፣ የፋውንዴሽኑን ቢሮ በ 240-740-2050 ያግኙ።
የተማሪዎች እድል
ታሪካዊ የጥቁር ኮሌጆች እና ዩንቨርስቲዎች (HBCU) አውደርዕይ፦ ዓርብ፣ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ the Universities at Shady Grove (USG). ይህ ዝግጅት 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው/ለአሳዳጊዎቻቸው ከ 50 በላይ HBCU ተወካዮች ጋር ለመገናኘት እድል ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም በቦታው ላይ የሚሰጥ የስኮላርሺፕ እድሎች ለተመራቂ ተማሪዎች ይኖራል (የቀረበውም በብሔራዊ ፓን-ሄለኒክ ካውንስል ሲሆን፣ በኮሌጅ ህይወት የፓናል ውይይት እና የተለያዩ ወርክሾፖች ነው። ተጨማሪ መረጃ
MCPS HBCU አውደ ርዕይ፣ ፌብሩዋሪ 14፣ 2025
FAFSA/MHEC One Application Completion Event፦ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ USG ይህ ዝግጅት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። ከሜሪላንድ ከፍተኛ ትምህርት ኮፒሽን (MHEC)፣ ከሞንትጎመሪ የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽነት ቢሮ እና TRiO የትምህርት ዕድል ማዕከል የመጡ ተወካዮች በ FAFSA እና MHEC አንድ ማመመልከቻዎች ላይ መረጃዎችን ያጋራሉ። በስፓንሽኛ ቋንቋ አስተርጓሚዎች ይኖራሉ። ተጨማሪ መረጃ
FAFSA, MHEC ማጠናቀቅ ዝግጅት በራሪ ወረቀት፣ ፌብሩዋሪ 14፣ 2025
ሰመር RISE 2025 ተማሪ ምዝገባ፦ የሰመር RISE ፕሮግራም አሁን ላይ ሶፍሞር ወይም ጁንየር ሆነው የትክክለኛውን አለም ተሞክሮ በሰመር ወቅት ማግኘት ለሚሹ ክፍት ነው። ተሳታፊ ተማሪዎች ከጁን 23 - ጁላይ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 50 ሰአታት በአካል፣ ቨርቹዋል፣ ወይም ሁለቱንም አጣምረው በኢንዱስትሪ ምርጫዎቻቸው መሰረት የሙያ ልምድ ወደሚሰጧቸው ተቋማት ጋር ይመደባሉ። ምዝገባ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 18 ይዘጋል።
ማህበርን ምረጡ 2025፦ በቪድዮ ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ ዕሁድ፣ ፌብሩዋሪ 16 ድረስ መወዳደሪያቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ቪድዮዎቹ የ 60 ሰከንዶች እርዝማኔ ያላቸው ሆነው ከፍቅር ግንኙነት ጥቃቶች/ትንኮሳ፣ ስምምነት፣ ወይም ከባድ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኝ ጓደኛን እንዴት መርዳት እንደሚቻል ከሚያሳይ መልክት ጋር መቅረብ አለባቸው። ተማሪዎች የ SSL ሰአታት ማግኘት እና እስከ $1,000 ያህል ማሸነፍ ይችላሉ። በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
ለስፕሪንግ የሴቶች ከኢምፓክት ጋር ፕሮግራም ጋር ምዝገባ አሁን ክፍት ነው
የስፕሪንግ መርሃ ግብሩ የሴቶች ከኢምፓክት ጋር (GWI) አሁን ለምዝገባ ክፍት ነው። GWI የሚያቀበውም ነፃ የ 10-ሳምንት ኢንተርፕርነርሺፕ ፕሮግራምን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በ MCPS ነው። ይህ ፕሮግራም የሚያተኩረው ወሳኝ የቢዝነስ እና መሪነት ክህሎቶችን የቢዝነስ ዕቅድ፣ ማርኬቲንግ እና ፋይናንሺያል እውቀትን ጨምሮ ሌሎች ርዕሶችን በሚያካትት በትግበራ ስርዓተ ትምህርት በመጠቀም ነው። የስፕሪንግ ፕሮግራሙ የማርች 3 ሳምንት ላይ ይጀምራል።በተጨማሪ ተማሩና ኣመልክቱ።
መልካም ዜና
MCPS ተመራቂ/ሲንየር ተማሪዎች ሙሉ-ትምህርት ስኮላርሺፖችን ከ QuestBridge አግኝተዋል፣ ይህም ብሔራዊ ለትርፍ ያልተቋቋመ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከዝቅተኛ ግቢ ቤተሰብ የመጡ የሁለተኛ ደረጃ ተመራቂዎችን ከ 50 በላይ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚያገናኝ ነው። ሙሉ ታሪኩን ያንብቡ።
ማስኮችን በት/ቤት የጤና ክፍሎች ውስጥ ማድረግ ይበረታታል።
ከመተንፈሻ እና ከቫይራል በሽታዎች (COVID-19, ኢንፍሉዌንዛ እና RSV) በቅርቡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ እና በሜሪላንድ ስቴት መጨመር ጋር ተያይዞ፣ ከሜሪላንድ የጤና ድፓርትመት ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ጎብኚዎች የት/ቤቶችን የጤና ክፍል በሚጎበኙበት ወቅት ማስኮችን/የፊት መሸፈኛዎችን እንዲያደርጉ MCPS መመሪያ ወስዷል። ማስክ ማድረግ ግዴታ ባይሆንም፣ የበሽታ መስፋፋትን ለመቀነስ እንዲረዳ ይበረታታል። በጤና ክፍሎች ጉብኝት ወቅት ልጅዎ ማስክ ከሌለው፣ ት/ቤቱ ያቀርባል።
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org